ፈልግ

የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝደንት አቶ አንቶኒዮ ኮስታ የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝደንት አቶ አንቶኒዮ ኮስታ   (ANSA)

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ከአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ከአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጋር በስልክ መወያየታቸውን የቅድስት መንበር መግለጫ ክፍል አስታወቀ። በቅርቡ በአፍሪካ አኅጉር ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉዞ በማጤን በተለይም በመካከለኛው ምሥራቅ ስላለው ሁኔታ፣ ስለ ዌስት ባንክ እና ስለ ደቡባዊ ሊባኖስ ክርስቲያኖች ሁኔታ ተወያይተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፥ ረቡዕ ሚያዚያ 21-2018 ዓ. ም. ከሰዓት በኋላ ከአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ከአቶ አንቶኒዮ ኮስታ ጋር በስልክ መወያየታቸውን የቅድስት መንበር መግለጫ ክፍል ዘግቧል።

መግለጫው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ እና የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በመካከለኛው ምሥራቅ ስላለው ሁኔታ፣ በተለይም በፍልስጤም ግዛት ውስጥ ስለ ዌስት ባንክ እና በደቡባዊ ሊባኖስ የሚገኙ ክርስቲያኖች ሁኔታ ላይ ትኩረት በመስጠት መወያየታቸውን አስታውቋል።

የቅድስት መንበር መግለጫ በተጨማሪም ቅዱስነታቸው በቅርቡ ወደ አልጄሪያ፣ ካሜሩን፣ አንጎላ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ባደረጓቸው የአፍሪካ ሐዋርያዊ ጉዞዎች ላይ አስተያየት መስጠታቸውን አስታውቋል።

“ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በስልክ ግንኙነታቸው፥ በሃይማኖቶች መካከል ስለሚደረግ ውይይት፣ ሰላምን ለማስፋፋት የሚደረግ ጥረት እና በአኅጉሪቱ ውስጥ እጅግ ለተቸገሩ ማኅበረሰቦች ድጋፍ በመስጠት አስፈላጊነት ላይ አፅንዖት ሰጥተዋል” ሲል መግለጫው አክሏል።

30 Apr 2026, 08:22