በሮም ከተማ ውስጥ የሚገኘው ኮሌሰዩም በመባልል የሚታወቀው ሥፍራ ውስጥ እ.አ.አ 2025 ዓ.ም የመስቀል መንገድ ጸሎት ሲከናወን በሮም ከተማ ውስጥ የሚገኘው ኮሌሰዩም በመባልል የሚታወቀው ሥፍራ ውስጥ እ.አ.አ 2025 ዓ.ም የመስቀል መንገድ ጸሎት ሲከናወን  (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ሊዮ 14ኛ አርብ የመስቀል መንገድ ጸሎት ላይ መስቀል ተሸክመው ጸሎት እንደሚመሩ ተገለጸ

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ምሕበረሰቦች ዘንድ በመጪው አርብ መጋቢት 25/2018 ዓ.ም ስለእኛ ብሎ እራሱን አሳልፎ የሰጠው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት ቀን በታላቅ መንፈሳዊነት እንደሚከበር ይጠበቃል። በዚህ የስቅለተ አርብ ቀን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በመጋቢት 25/2018 ዓ.ም በሮም ከተማ ውስጥ በሚገኘው ኮሎሲየም በመባል በሚታወቀው ስፍራ በሚከናወነው የመስቀል መንገድ ጸሎት እንደሚመሩ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ኢየሱስን ወደ ጎልጎታ ያደረገውን ጉዞ የሚያስታውስ በስቅለተ አርብ ቀን በሚከናወነው የመስቀል መንገድ ጸሎት ላይ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ምዕመናን ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በሮም ኮሎሲየም በሚገኘው ሥፍራ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በስቅለተ አርብ ቀን የተጓዛቸውን አስራ አራት የመስቀል መንገድ ጉዞዎች የምያስታወሰውን ምስጢር በጸሎት ይመራሉ፤ በመስቀል መንገድ ጸሎት ሥነ-ሥርዓት ላይ ሁሉ መስቀሉን ተሸክመው ጸሎት የምያደርጉ ሲሆን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን 267ኛ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡ በኋላ ቅዱስነታቸው በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ደረጃ የምያደርጉት የመጀመሪያ የስቅለተ አርብ ክብረ በዓል ይሆናል።

የዘንድሮው የመስቀል መንገድ ሥነ ሥርዓት የማሰላሰያ ጸሎቶች እ.አ.አ ከ2016 እስከ 2025 ዓ.ም ድረስ የቅድስት ምድር ጠባቂ ሆነው ላገለገሉት ለፍራንችስካዊያን ማሕበር ካህን አባ ፍራንችስኮ ፓተን እንዲያዘጋጁ አለፊነት ተሰጥቷቸዋል። የቅድስት መንበር የፕሬስ ጽሕፈት ቤት የመስቀል መንገድ ሥነ ሥርዓት የማሰላሰያ ጸሎቶች ጽሑፎቹ አርብ ጠዋት ሚያዝያ 25/2018 ዓ.ም፣ እኩለ ቀን አካባቢ እንደሚታተም አስታውቋል።

ብዙውን ጊዜ በዮርዳኖስ ውስጥ ከሚገኘው ከኔቦ ተራራ የሚጽፉት አባ ፓተን፣ በተለይም በአሁኑ ወቅት በግጭት እና አለመረጋጋት በተሞላው በዚህ ወቅት ለመካከለኛው ምስራቅ ሕዝብ ስቃይ በተደጋጋሚ ድምጽ ሰጥተዋል።

ባለፈው ዓመት፣ ልክ እንደ 2024 ዓ.ም፣ የመስቀል መንገድ ሥነ ሥርዓት የማሰላሰያ ጸሎቶች ያዘጋጁት በሮም በሚገኘው የጂሜሊ ሆስፒታል ውስጥ ለረጅም ጊዜ ሆስፒታል ከቆዩ በኋላ ወደ  ቅድስት ማርታ የጳጳስ ቤት ከተመለሱ በኋላ የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የመስቀል መንገድ ሥነ ሥርዓት የማሰላሰያ ጸሎቶች መጻፋቸው ይታወሳል።

01 Apr 2026, 13:02