ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የአፍሪካ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን ፈጽመው ተሰናበቱ
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በውጭ አገራት የጀመሩትን ሦስተኛውን ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት በኢኳቶሪያል ጊኒ ፈጽመዋል።
በአፍሪካ አኅጉር ደማቅ አቀባበል እና መስተንጎዶ የተደረገላቸው ቅዱስነታቸው በአኅጉሪቱ ውስጥ ለአሥራ አንድ ቀናት ያደረጓቸውን የአራት አገራት ሐዋርያዊ ጉብኝት በኢኳቶሪያል ጊኒ ሲፈጽሙ የክብር አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል።
በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ ስምንት ሰዓት ገደማ ወደ ሮም የሚያደርጉትን በረራ ከመጀመራቸው በፊት በማላቦ አየር ማረፊያ ከአገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ሰላምታ ተለዋውጠዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከሚያዝያ 5-15/2018 ዓ. ም. ድረስ ያደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ሦስተኛው ዓለም አቀፍ ጉብኝት ሲሆን በዚህም አልጄሪያን፣ ካሜሩንን፣ አንጎላን እና ኢኳቶሪያል ጊኒን ጎብኝተዋል። የሰላም መልዕክተኛ ሆነው በተጓዙባቸው አገራት ሁሉ ታሪካቸውን በማስታወስ አሁን እና ወደፊት ሊገጥሟቸው በሚችሉ ተግዳሮቶች ላይ በማሰላሰል ለዜጎች የማበረታቻ ንግግር አድርገው ለመሪዎቻቸውም የፍትህን አስፈላጊነት ገልጸዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ወደ ሮም የሚደርሱት ሐሙስ ሚያዝያ 15 በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ እንደሚሆን የተገመተ ሲሆን፥ በበረራ ወቅት ለጋዜጠኞች መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።
