ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ “የሰው ልጅ ክብር በምንም መንገድ ሊጠፋ አይችልም” ሲሉ ተናገሩ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በዩናይትድ ስቴትስ እና በዓለም ዙሪያ የሞት ቅጣት ለማስቀረት ጥረት ለሚያደርጉት ግለሰቦች እና ማኅበራት ያላቸውን ድጋፍ፥ ሚያዝያ 16/2018 ዓ. ም. ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክታቸው ገልጸዋል። ቅዱስነታቸው በመልዕክታቸው፥ አንድ ሰው ከባድ ወንጀሎችን የፈጸበ እንኳ ቢሆን ሰብዓዊ ክብሩ በምንም መንገድ ሊጠፋ እንደማይችል ተናግረው፥ ሰብዓዊ ክብርን መጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን አጥብቀው ተናግረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ “እጅግ ከባድ ወንጀሎች ከተፈጸሙ በኋላም ቢሆን የሰው ልጅ ክብር የማይጠፋ መሆኑን ቤተ ክርስቲያን ታረጋግጣለች” ሲሉ፥ የሞት ቅጣት የተሻረበትን 15ኛ ዓመት ለማክበር በዩናይትድ ስቴትስ ኢሊኖይ ግዛት በሚገኝ ዴፖል ዩኒቨርሲቲ ዓርብ ሚያዝያ 16/2018 ዓ. ም. ለተሰበሰቡት ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት ተናግረዋል።

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2011 ዓ. ም. የተደረገውን ይህን ታሪካዊ ውሳኔ ለማስታወስ በዩኒቨርሲቲው ከተገኙት ጋር በመተባበር፥ በዩናይትድ ስቴሪካ እና በዓለም ዙሪያ የሞት ቅጣት ለማስቀረት ለሚጥሩት ድጋፍ እንደሚሰጡ ገልጸዋል።

“ጥረታችሁ የእያንዳንዱ ሰው ክብር የበለጠ እውቅና እንዲያገኝ እና ሌሎችም ለተመሳሳይ ፍትሃዊ ዓላማ ለመሥራት እንዲያነሳሳቸው እጸልያለሁ” ብለዋል።

ፍትህ ያለ ገንዘብ ቅጣት ሊገኝ ይችላል

“ዜጎችን የሚጠብቁ ውጤታማ የሆኑ የእርማት ሥርዓቶች ሊዳብሩ ይችላሉ” ያሉት ቅዱስነታቸው፥ ይህም ዕድሉ ላላቸው ምሕረትን ከማግኘት ሙሉ በሙሉ አያግዳቸውም” ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።

ነፍስሔር ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እና የቅርብ ጊዜ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት፥ የጋራ ጥቅም ሊከበር እንደሚችል እና የፍትህ መስፈርቶች ያለ ሞት ቅጣት ሊሟሉ እንደሚችሉ ደጋግመው አጥብቀው የጠየቁት ለዚህም ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ በመጥቀስ፥ “የሞት ቅጣት በሰው ልጅ የማይጣስ ክብር ላይ የሚሰነዘር ጥቃት በመሆኑ ተቀባይነት የለውም” በማለት ቤተ ክርስቲያን የምታስተምር መሆኑን አስረድተዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ “ሕይወትን ከተጸነሰበት ጊዜ እስከ ተፈጥሯዊ ሞት ድረስ መጠበቅ አስፈላጊ ነው” የሚለውን የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮን በመድገም፥ የሕይወት መብት የሌሎች ሰብዓዊ መብቶች በሙሉ መሠረት እንደሆነ አስረድተው፥ ማበብ እና መበልጸግ የሚችለውም አንድ ማኅበረሰብ የሰውን ሕይወት ቅድስና ሲጠብቅ ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል።

 

25 Apr 2026, 16:07