ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ወደ ቱርክ እና ሊባኖስ የሰላም መልዕክት ይዘው በሄዱበት ወቅት  ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ወደ ቱርክ እና ሊባኖስ የሰላም መልዕክት ይዘው በሄዱበት ወቅት   (ANSA)

ቫቲካን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የአፍሪካ ሐዋርያዊ ጉብኝት መሪ ጭብጦችን እና ዓርማዎችን ይፋ አደረገ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከሚያዝያ 5-15/2018 ዓ. ም. ድረስ በአራት የአፍሪካ አገራት እነርሱም አልጄሪያ፣ ካሜሩን፣ አንጎላ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ የሚያደርጉት የሐዋርያዊ ጉብኝት መርሃ ግብር የቅድስት መንበር መግለጫ ክፍል ይፋ አድርጓል። መግለጫው በተጨማርም ኦፊሴላዊ የሐዋርያዊ ጉብኝት ዓርማዎችን እና መሪ ቃላትንም አክሏል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የቅድስት መንበር መግለጫ ክፍል ሰኞ መጋቢት 7/2018 ዓ. ም. ይፋ ባደረገው መግለጫ ላይ ቅዱስነታቸው በአራቱ የአፍሪካ አገራት ማለትም በአልጄሪ፣ በካሜሩ፣ በአንጎላ እና በኢኳቶሪያል ጊኒ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደሩ ገልጾ ለጉብኝታቸው የመረጧቸውን ዓርማዎችን እና መሪ ቃላትን ይፋ አድርጓል።

በአልጄሪያ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በአልጄሪያ የሚያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማሳየት የተዘጋጀው ዓርማ የሰላም እና የኅብረት ምልክት የሆኑ ሁለት እርግቦች ጥንታዊ ቅርስ ከሆነው ዋንጫ ሲጠጡ የሚያሳይ ሲሆን ክርስቲያናዊ ዓርማው ደግሞ የክርስቶስን ስም፣ ድል እና ትንሳኤውን የሚገልጹ ሁለት የግሪክ ፊደላትን “X” እና “P” ከአልጄሪያ ካርታ ጋር አጣምሮ የያዘ እንደሆነ ተመልክቷል።

በዓርማው ላይ የሚታዩ አረንጓዴ፣ ቀይ እና ነጭ ቀለማት የአልጄሪያን ባንዲራ የሚያስታውሱ ሲሆን ቢጫ ቀለም ደግሞ ቫቲካንን ለማስታውስ ተመልክቷል። በመሃል እና ከታች በአረብኛ ጽሑፍ በአማዚግ እና በፈረንሳይኛ ቋንቋዎች የተጻፉ መሪ ቃላት “ላ ፓይክስ ሶይት አቬክ ቮስ” (“ሰላም ለእናንተ ይሁን”)፣ በአረብኛ “አሰላሙ አለይኮም” በሚሉ የሰላምታ ቃላት መዘጋጀቱ ተመልክቷል።

ዓርማው በክርስቲያኖች እና በሙስሊሞች መካከል የሚደረገውን የጋራ ውይይት እና መልካም የእርስ በርስ ግንኙነትን የሚገልጽ ሲሆን፥ የሁለቱ ሃይማኖቶች ተከታዮች በሰላም፣ በወንድማማችነት እና በመግባባት አብረው እንዲኖሩ ለማሳስብ የሚረዳ ዓለም አቀፍ ግብዣን የሚያቀርብ እንደሆነ ተገልጿል።

ቅዱስነታቸው በአንጎላ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ዓርማ
ቅዱስነታቸው በአንጎላ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ዓርማ

በካሜሩን የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በካሜሩን ለሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት የተዘጋጀው ዓርማ ለክርስትና ሕይወት መሠረት የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚገኝበት ሲሆን፥ በተጨማሪም የአገሪቱን ገጽታ የሚያሳይ መስመር፣ ብሔራዊ ባንዲራዋን የሚያሳታውሱ አረንጓዴ፣ ቀይ እና ቢጫ ቀለማትም የታከሉበት እንደሆነ ተመልክቷል።

በስተግራ በኩል የወንጌል ምስክርነትን የሚገልጽ የመስቀል ምልክት የሚታይ ሲሆን ከሥሩ ደግሞ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም የመጀመሪያ ፊደል “M” ይታያል። በመሃል የመንፈስ ቅዱስ ተግባር እና የምሥራቹ ቃል በመላው የአገሪቱ ክፍሎች መስፋፋቱን የሚወክል እና ከርግብ ምስል የሚወጡ  የብርሃን ጨረሮች የሚፈነጥቁበት እንደሆነ ተመልክቷል። በስተቀኝ በኩል ርዕሠ ሊቃነ ጳጳስ ሊዮ 14ኛ በጸሎት ላይ እንዳሉ የሚያሳይ ሲሆን ይህም ሐዋርያዊ እረኝነትን እና ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ያላቸውን ኅብረት እና እንክብካቤን የሚገልጽ ምልክት እንደሆነ ታውቋል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ላይ ከዮሐ. 17:21 የተወሰደ “Que tous soient un” / “ሁሉም አንድ እንዲሆኑ” የሚለው እና በኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኝ አንድነት “In Illo uno unum” የሚለው ጭብጥ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የሐዋርያዊ እረኝነት ስልጣን መሪ ቃል ጋር የተገናኙ እንደሆነ ታውቋል።

ቅዱስነታቸው በአንጎላ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ዓርማ
ቅዱስነታቸው በአንጎላ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ዓርማ

በአንጎላ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በአንጎላ ለሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት የተዘጋጀው ዓርማ የአገሪቱን ካርታ በሚገልጽ ቀይ መስመር የተገለጸ ሲሆን ይህም በአገሪቱ ውስጥ የፈሰሰውን ደም የሚያስታውስ እና ካርታውም በጥቁር ቀለም የሞገድ ምልክት የተከበበ እና በረከትን የሚያመላክት እንደሆነ ተመልክቷል። ይህም አፍሪካዊ ማንነትን የሚገልጽ ከመሆኑ በተጨማሪ በአገሪቱ ሕዝቦች ላይ መለኮታዊ ጥበቃ እንደሚመጣ የሚያመላክት እንደሆነ ተገልጿል። በዓርማው መሃለኛው ክፍል በአበባ ምስል የተገለጸው ከፊል ቢጫ ክብ ቅርጽ የሥራን ክብር እና ብሔራዊ ባንዲራን የሚያመላክት ሲሆን ከመስቀል ምልክት ጋር ሲጣመር ቅዱስ ቁርባንን እንደሚወክል ተገልጿል።

አበባዎቹ የአገሪቱን ምሳሌያዊ ዛፍ “ሙሌምባ”ን የሚያስታውሱ ሲሆን፥ ሰማያዊ መስመሮች ደግሞ የአገሪቱን ወንዞች ሲወክሉ በአጠቃላይ ዓርማው በእግዚአብሔር የተባረከች እና በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የምትመራ፥ በሰላም፣ በክብር እና በአዲስ ተስፋ ወደፊት የምትጓዝ አንጎላን ለማመላከት እንደሆነ ታውቋል። ከታች በስተቀኝ በኩል በተጻፈው መሪ ቃል አማካይነት የተስፋ፣ የእርቅ እና የሰላም ተጓዥ የሆኑት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ አንጎላን መባረካቸውን ይገልጻል።

ቅዱስነታቸው በአንጎላ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ዓርማ
ቅዱስነታቸው በአንጎላ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ዓርማ

በኢኳቶሪያል ጊኒ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት

በመጨረሻም ቅዱስነታቸው በኢኳቶሪያል ጊኒ የሚያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት በሚገልጽ ዓርማ ውስጥ በጉልህ የሚታየው ወርቃማ መስቀል ከሞት የተነሣውን ኢየሱስ ክርስቶስን እና የክርስትና እምነትን የሚያሳይ ምልክት እንደሆነ ታውቋል።

በዓርማው መሃለኛው ክፍል ከሚታየው የአገሪቱ ካርታ እና ባንዲራ ጋር አባት፣ እናት እና ልጅ በአንድነት የሚገኙበት የቤተሰብ ምስል የተገለጸ ሲሆን፥ በታች በኩል አንድ ሰው ጀልባ ላይ ሆኖ መጽሐፍ ሲያነብ የሚያሳየው ደግሞ ከ170 ዓመታት በፊት የመጀመሪያዎቹ ወንጌላውያን ባሕርን አቋርጠው ወደ  ኢኳቶሪያል ጊኒ መምጣታቸውን የሚያስታውስ እንደሆነ ተገልጿል።

በቅደም ተከተል የሚታዩ ወርቅማ፣ አረንጓዴ፣ ነጭ እና ቀይ ቀለማት የኢየሱስ ክርስቶስን ብርሃን፣ ምድሪቱን፣ ሰላምን እና የነፃነትን ትግልን የሚያስታውሱ መሆናቸው ተገልጿል። “የኢኳቶሪያል ጊኒ ብርሃን የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ እና የወደፊት ተስፋ” የሚለው መሪ ቃሉም የአገሪቱን ያለፈውን ታሪክ ከማስታወስ በተጨማሪ በእምነት እና በተስፋ መንገድ ላይ ያለውን እምነት የሚገልጽ እንደሆነ ተገልጿል።

ቅዱስነታቸው በኢኳቶሪያን ጊኒ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ዓርማ
ቅዱስነታቸው በኢኳቶሪያን ጊኒ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ዓርማ

 

17 Mar 2026, 11:59