ፈልግ

የሊባኖስ-እስራኤል-ኢራን-የአሜሪካ ጦርነት ብዙ ሰው አፈናቅሏል የሊባኖስ-እስራኤል-ኢራን-የአሜሪካ ጦርነት ብዙ ሰው አፈናቅሏል  (AFP or licensors)

ር.ሊ.ጳ ሊዮ በመካከለኛው ምስራቅ፡- 'የሚሰቃዩ ሰዎች ጉዳት የሁሉም ሰው ሰብዓዊ ጉዳት ነው" አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እሁድ መጋቢት 13/2018 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከጸለዩ በኋላ በዓለም ዙሪያ የሚፈጸመው የዓመፅ እና የጦርነት ግጭት እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፣ “በእነዚህ ግጭቶች ንፁሃን ሰዎች ሰለባዎች ሲሆኑ እና በብዙ ሰዎች ላይ ስቃይ ሲደርስባቸው ዝም ማለት አንችልም” ሲሉ ሁሉም ሰው በጸሎት እንዲጸና አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ከጸሎቱ በኋላ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመካከለኛው ምስራቅ እንዲሁም በሌሎች የዓለም ክፍሎች “በጦርነትና በዓመፅ በተበታተኑ” ለሚታየው ቀጣይ ሁኔታ ያላቸውን ጥልቅ ስጋት ገልጸዋል። “በእነዚህ ግጭቶች ንፁሃን ሰለባዎች እንዳሉ እና ብዙ ሰዎች ስቃይ ሲደርስባቸው ዝም ማለት አንችልም” ሲሉ አፅንዖት ሰጥተው በመልእክታቸው ተናግረዋል።

ይህ ቀጣይነት ያለው ዓመፅ ሁሉንም ሰው ያቆስላል - “በዚያ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚሰቃዩ ሰዎች፣ ጉዳት የእኛም የሁላችንም የሰው ልጆች ጉዳት ነው" ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በእነዚህ ጦርነቶች ምክንያት የሚመጣው ህመም፣ ሞት እና ስቃይ “ለመላው የሰው ልጅ ቤተሰብ ክፉ ምሳሌ እና በእግዚአብሔር ፊት ጩኸት ናቸው” ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ከዚያም “ጠላትነት እንዲቆምና በቅንነት ውይይትና ለእያንዳንዱ ሰው ሰብዓዊ ክብር አክብሮት በተሞላበት መንገድ ላይ የተመሠረተ የሰላም መንገዶች በመጨረሻ እንዲከፈቱ” ሁሉም ሰው በጸሎቱ እንዲጸና አበረታተዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህንን ጥሪ ሲያቀርቡ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እየጨመረ የመጣውን የሟቾች ቁጥር የሚገልጹ ዘገባዎች ብቅ ማለታቸው ቀጥለዋል፣ ይህም ዓመፅ እና ጦርነት ወደ 24ኛው ቀን እየተቃረበ በመጣበት በአሁኑ ወቅት ነው። እሁድ ጠዋት በእስራኤል ከተሞች ላይ በኢራን የሚሳኤል ጥቃቶች ከተፈጸመ በኋላ በእስራኤል በሊባኖስ ላይ በተከፈተው ጥቃት የተነሳ ከ1,000 በላይ ሰዎች እንደተገደሉ፣ ቢያንስ 160 ሰዎች እንደቆሰሉ ይታመናል፣ እና በባህረ ሰላጤው አከባቢ፣ ሳውዲ አረቢያ እና ባህሬን በርካታ ድሮኖች እና ሚሳኤሎች በአየር ክልላቸው ውስጥ እንደገቡ ሪፖርት አድርገዋል። በኢራን፣ የሟቾች ቁጥር ወደ 1,444 እንደሚጠጋ እና ከ18,000 በላይ መቁሰላቸውም ተዘግቧል።

23 Mar 2026, 13:46