ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በካስቴል ጋንዶልፎ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምልሽ ሲስጡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በካስቴል ጋንዶልፎ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምልሽ ሲስጡ 

ር.ሊ.ጳ ሊዮ 14ኛ፣ “ለሰላም ሥሩ፣ ያለ ጦር መሳሪያ ለግጭቶች መፍትሄ ፈልጉ” ማለታቸው ተገለጸ

ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከቪላ ባርቤሪኒ መኖሪያ ውጭ በሚገኘው በካስቴል ጋንዶልፎ ለሚገኙ ጋዜጠኞች አጭር መግለጫ በየካቲት 24/2018 ዓ.ም መስጠታቸው የተገለጸ ሲሆን “ለሰላም ስሩ፣ ውይይትን አበረታቱ” የሚለውን ከዚህ ቀደም ቅዱስነታቸው ያቀረቡትን ጥሪ በድጋሚ አድሰዋል።

“ለሰላም ጸልዩ፣ ለሰላም ስሩ እና ጥላቻን ቀንሱ። በዓለም ላይ ያለው ጥላቻ ያለማቋረጥ እየጨመረ ነው” ይህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከቪላ ባርቤሪኒ ለጋዜጠኞች ቡድን፣ ከትናንት እስከ ዛሬ ባለው ጊዜ ውስጥ የተለመደውን የእረፍት እና የስራ ቀን ያሳለፉበት በካስቴል ጋንዶልፎ መኖሪያ ቤት ውስጥ ያቀረቡት ጥሪ ነው።

በመካከለኛው ምስራቅ ጥቃቶች እየጨመሩ ሲሄዱ እና በዓለም ዙሪያ ፍርሃት እና ውጥረት እየጨመረ ሲሄድ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሰላምን ግብ ለማሳካት ሥራ እንዲሰራ አሳስበዋል። በተመሳሳይ ጊዜ፣ ሁሉም ሰው “ውይይትን ለማበረታታት በእውነት ጥረት እንዲያደርጉ” እና “ችግሮችን ለመፍታት ያለ ጦር መሳሪያ መፍትሄዎችን እንዲፈልጉ” ጥሪ አቅርበዋል።

እነዚህ ቃላት ባለፈው እሁድ የካቲት 22/2018 ዓ.ም ቅዱስነታቸው በቫቲካን ለተሰበሰቡ ምዕመናን ያስተላለፉትን መልእክት በድጋሚ ያስተጋባሉ፤ በዚህ ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ አሜሪካ እና እስራኤል፣ በኢራን እና ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ በርካታ አካባቢዎች ላይ ባደረሱት የቦምብ ጥቃት ላይ ስለፈጸሙት ጥቃት ሲናገሩ፣ ቅዱስነታቸው በቁጭት እንዲህ ብለዋል፣ “መረጋጋት እና ሰላም የሚገኘው በጋራ ማስፈራሪያዎች ወይም ጥፋትን፣ መከራን እና ሞትን በሚዘሩ የጦር መሳሪያዎች አጠቃቀም ሳይሆን ምክንያታዊ፣ ቅን እና ኃላፊነት በሚሰማው ውይይት ብቻ ነው” ማለታቸው ተዘግቧል።

04 Mar 2026, 15:33