ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በሮም ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው በካስተል ጋንዳልፎ ከጋዜጠኞች ጋር ቃለመጠይቅ ባደረጉበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በሮም ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው በካስተል ጋንዳልፎ ከጋዜጠኞች ጋር ቃለመጠይቅ ባደረጉበት ወቅት   (@VaticanNews)

ር.ሊ.ጳ ሊዮ ባለሥልጣናት የተኩስ አቁም ስምምነትን እና ሰላምን በውይይት መፈታት አለባቸው አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ እርሳቸው ሳምንታዊ እረፍ በምያደርጉበት በሮም ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ካስቴል ጋንዶልፎ በመባል በሚታወቀው ሥፍራ ለጋዜጠኞች አጭር መግለጫ ሰጥተዋል፣ “በጦር መሳሪያ ሳይሆን ለሰላም እንሰራለን” የሚለውን ጥሪ አድሰው፣ የጥላቻ፣ የዓመፅ እና የሞት መጨመርን አውግዘዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

“የተኩስ አቁም ስምምነትን ለማደስ፣ ለሰላም እንሰራለን፣ ነገር ግን በጦር መሳሪያ ሳይሆን - በውይይት፣ ለሁሉም ሰው በእውነት መፍትሄ እንፈልጋለን” ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ማክሰኞ ምሽት መጋቢት 15/2018 ዓ.ም በካስቴል ጋንዶልፎ በሚገኘው ቪላ ባርበሪኒ አቅራቢያ ለጋዜጠኞች ቡድን ባደረጉት አጭር መግለጫ የሰላም ጥሪውን አድሰዋል።

ዓለም አቀፍ ሁኔታን በማስታወስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ጥላቻ እየጨመረ ነው፣ ዓመፅ እየባሰ ይሄዳል፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተገልለዋል፣ እና በጣም ብዙ ሞተዋል” በማለት በቁጭት የተናገሩት ቅዱስነታቸው “ለሰላም መጸለይ እንፈልጋለን፣ ነገር ግን ሁሉም ባለስልጣናት ችግሮችን ለመፍታት በውይይት በእውነት እንዲሰሩ አጥብቄ እጠይቃለሁ” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተናግረዋል።

በተናጠል፣ እሑድ ዕለት መጋቢት 13/2018 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በመካከለኛው ምስራቅ እና በሌሎች የዓለም ክልሎች “በጦርነት እና በዓመፅ በተበታተኑ” ሁኔታ “አሳዛኝ” መሆናቸውን ገልጸው እንደ ነበረ ይታወሳል።

“በእነዚህ ግጭቶች ሰለባ የሆኑ ብዙ መከላከያ የሌላቸው ሰዎች ስቃይ ሲደርስባቸው ዝም ማለት አንችልም” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዚያ ወቅት ተናግረዋል። “የሚጎዳቸው ሁሉንም የሰው ልጅ ይጎዳል። በእነዚህ ጦርነቶች ምክንያት የሚደርሰው ሞት እና ስቃይ ለመላው የሰው ልጅ ቤተሰብ መጥፎ ምሳሌ እና ወደ እግዚአብሔር የሚወጣ ጩኸት ነው!” ማለታቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ቀጥለው፣ “በጸሎት ለመጽናት ያለኝን ጥሪ አጥብቄ እደግማለሁ፣ ይህም ጥላቻ እንዲቆም እና የሰላም መንገዶች በመጨረሻ እንዲከፈቱ፣ በቅንነት ውይይት እና ለእያንዳንዱ የሰው ልጅ ክብር አክብሮት ላይ የተመሠረተ ጸሎት እንዲደረግ ጥሪ አቅርባለሁ" ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን ማጠናቀቃቸው ይታወሳል።

25 Mar 2026, 15:34