ፈልግ

ሊቀ ጳጳሳት ሉዊስ ማሪን ደ ሳን ማርቲን ሊቀ ጳጳሳት ሉዊስ ማሪን ደ ሳን ማርቲን 

ር.ሊ.ጳ ሊዮ አዲስ የጳጳስ አቃበ ነዋይ መሾማቸው ተገለጸ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሊቀ ጳጳሳት ሉዊስ ማሪን ደ ሳን ማርቲንን የጳጳስ አቃበ ነዋይ በመባል የሚታወቀውን የበጎ አድራጎት አገልግሎት ጽኃፈት ቤት ዋና ኃላፊ አድርገው መሾማቸው የተገጸሰ ሲሆን፣ ካርዲናል ኮንራድ ክራጄውስኪን በፖላንድ የሉዶን ሜትሮፖሊታን ሊቀ ጳጳስ አድርገው መሾማቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ሐሙስ ዕለት መጋቢት 03/2018 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሊቀ ጳጳስ ሉዊስ ማሪን ደ ሳን ማርቲንን የቫቲካን የቅድስት መንበር የበጎ አድራጎት አገልግሎት ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አድርገው መሾማቸው የተገለጸ ሲሆን አክለውም የሊቀ ጳጳስ ክብር ሹመት ሰጥተዋቸዋል።

ሊቀ ጳጳስ ማሪን ደ ሳን ማርቲን እ.አ.አ ከ2021 ዓ.ም ጀምሮ የሲኖዶሱ ሴክሬታሪያት ምክትል ጸሐፊ ሆነው አገልግለዋል። በተመሳሳይ ጊዜ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አሁን የበጎ አድራጎት አገልግሎት ጽ/ቤት ዋና ጸኃፊ የነበሩት ካርዲናል ኮንራድ ክራጄውስኪን የትውልድ ቦታቸው ፖላንድ ውስጥ በሚገኘው የሉዶዝ የሜትሮፖሊታን ሊቀ ጳጳስ አድርገው ሾሟቸዋል።

ካርዲናል ክራጄውስኪ እ.አ.አ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ የጳጳስ አቃበ ነዋይ ሆነው አገልግለዋል። የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እ.አ.አ ሰኔ 28/2018 ካርዲናል አድርገው ሾሟቸዋል፣ እናም በሐዋርያዊ መመሪያ በላቲን ቋንቋ "ፕራዲኬቴ ኢቫንጀሊየም" (ወንጌልን ስበኩ) ካርዲናል ክራጄውስኪ አዲስ በተቋቋመው የበጎ አድራጎት አገልግሎት ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አድርገው መሾማቸው ይታወሳል።

ከሹመት በኋላ ለቫቲካን ዜና ተቋም ሲናገሩ ካርዲናል ክራጄውስኪ በቫቲካን ለ28 ዓመታት ላሳለፉት አገልግሎት እግዚአብሔርን አመስግነዋል።

በሮም የሥርዓተ አምልኮ ሥነ-መለኮትን ሲማሩ፣ በወቅቱ አባ ክራጄውስኪ ለጳጳስ ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የሥርዓተ አምልኮ መምህር ሆኑ፣ እንዲሁም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛን በጵጵስና ሥልጣናቸው በሙሉ እና ከዚያም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን ለ10 ወራት አገልግለዋል።

“እያንዳንዱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለቤተክርስቲያኒቱ አዲስ ነገር ስለሰጡ፣ እያንዳንዱም የተለየ ትኩረት ስለሰጣቸው የተለያዩ ነገሮችን አጋጥሞኛል” ሲሉ መናግራቸውም ይታወሳል።

የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጳጳስ አቃበ ነዋይ እንዲሆኑ ሲጠይቋቸው፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እ.አ.አ በ2013 ለዓለም ወጣቶች ቀን ወደ ሪዮ ዴ ጄኔሮ በረራ ከማድረጋቸው በፊት ለሁለት ሰዓታት ከካርዲናል ክራጄቭስኪ ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸው ይታወሳል።

"እንደ አቃበ ነዋይ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አስረድተውኛል" ሲሉ ካርዲናል ክራጄቭስኪ ተናግረዋል። "ከድሆች አጠገብ እንድተኛ፣ ከቫቲካን እንድወጣ እና ሁልጊዜም በቀኑ መጨረሻ የባንክ አካውንቱ ባዶ እንዲሆን ጠየቁኝ ፣ምክንያቱም ሁሉም ነገር ለበጎ አድራጎት ስራዎች የታሰበ ነበር። ነገር ግን ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር የቆየ አንድ ነገር አለ፡- 'ምን ማድረግ እንዳለብህ የማታውቅ ከሆነ ሁልጊዜ ጌታን ጠይቅ፣ እና በአንተ ቦታ ምን እንደሚያደርግ ጠይቅ" የሚለው አነጋገራቸው ሁልጊዜም ቢሆን አብሯቸው የሚቆይ ሀሳብ መሆኑን አስረድተዋል።

በስልጣን ዘመናቸው ካርዲናሉ በሊቀ ጳጳሱ ስም 10 ተልእኮዎችን ወደ ዩክሬን አከናውነዋል፣ ለመከራ ለተጋለጡት ሰዎች አምቡላንሶችን እና ሌሎች የአደጋ ጊዜ እርዳታ የተጫኑ ተሽከርካሪዎችን በማሽከርከር ጭምር እንደ ሆነም አክለው ገልጸዋል።

የሉዶ ሊቀ ጳጳስ ሆነው ስለተሾሙበት ሁኔታ ሲጠየቁ፣ ካርዲናል ክራጄቭስኪ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በአለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ልብ ውስጥ የተገኙትን ልምዶች ሁሉ ወደ አካባቢው ቤተክርስቲያን ማምጣት ይፈልጉ እንደሆነ አስበዋል።

“በፈቃደኝነት ተቀብያለሁ፣ ምክንያቱም የቤተክርስቲያኒቱ መልካምነት ከታማኞች ቅርበት የተወለደ ነው” ብለዋል ካርዲናሉ። “ሀገረ ስብከቴ ሰፊ ነው፤ ሁለት ሚሊዮን ተኩል ነዋሪዎች አሏት፤ ለማገልገል ዝግጁ ነኝ” ሲሉ ተናግረዋል። በቫቲካን ውስጥ ለዓመታት ያገለገሉ ቢሆንም፣ ካርዲናል ክራጄውስኪ ወደ ፖላንድ እና ወደ ትውልድ ከተማቸው ለመመለስ ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል። “ፖላንድን በፍጹም አልለቅም” ብለው አምነዋል፣ “ሁልጊዜም በሕዝቡ መካከል ኖሬያለሁ፣ እና ትንሽም ናፍቆት ነበረኝ” ሲሉ ተናግረዋል።

13 Mar 2026, 11:45