ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን ለመጀመር ሞናኮ ደርሰዋል

ቅዱስነታቸው ቅዳሜ መጋቢት 19/2018 ዓ. ም. በአገሩ የሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት በኋላ ብዙም ሳይቆይ ወደ ሄሊኮፕተር ማረፊያ ደርሰዋል። ቅዱስነታቸው ወደ ሥፍራው ሲደርሱ ልዑል አልበርት ዳግማዊ እና ልዕልት ቻርሊን ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱት ሊዮ 14ኛ ወደ ሞናኮ የሄሊፕተር ማረፊያ ሲደርሱ ልዑል አልበርት ዳግማዊ እና ልዕልት ቻርሊን የተቀበሏቸው ሲሆን፥ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሁለተኛውን ሐዋርያዊ ጉዞ የሚጀምሩባት ሞናኮ በዓለም ውስጥ ካሉት ጥንታዊ ግዛቶች መካከል አንዷ እና ከቫቲካን ቀጥላ ሁለተኛዋ ትንሿ አገር እንደሆነች ተነግሯል።

ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የክብር አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በኋላ 21 ጊዜ መድፍ የተተኮሰ ሲሆን፥ ቀጥሎ ልዑል አልበርት ልዑካኖቻቸውን ካስተዋወቁ በኋላ ለኦፊሴላዊ አቀባበል ወደ ንጉሣዊው ቤተ መንግሥት አምርተዋል።

ይህ ሥነ-ሥርዓት የሐዋርያዊ ጉብኝታቸው የመጀመሪያው ክፍል ሲሆን ጠዋት በነበራቸው ዝግጅት ከከተማው ካቶሊካዊ ማኅበረሰብ ጋር በቅድስት ዴቮት ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ባለው አደባባይ ከወጣቶች እና ከንዑሰ ክርስቲያን ጋር ከተሰበሰቡ በኋላ ከሰዓት በሉዊስ ዳግማዊ ስታዲየም የተዘጋጀውን የመስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ-ሥርዓት እንደሚመሩ ታውቋል።

28 Mar 2026, 16:37