ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ሊዮ 14ኛ እና "ከችግር ወደ እንክብካቤ፡ የካቶሊክ እርምጃ ለህፃናት" በሚል ርዕስ ለተቋቋመው የዝግጅት ኮሚቴ ጋር በቫቲካን ር.ሊ.ጳ ሊዮ 14ኛ እና "ከችግር ወደ እንክብካቤ፡ የካቶሊክ እርምጃ ለህፃናት" በሚል ርዕስ ለተቋቋመው የዝግጅት ኮሚቴ ጋር በቫቲካን  (@Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የህፃናትን መብቶች ማክበር እና ከአደጋ መጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን በድጋሚ ገለጹ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ህጻናትን በዓለም አቀፍ ስጋት ማዕከል ውስጥ ለማስቀመጥ የቤተክርስቲያኒቱን ጥሪ አድሰዋል፣ ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳኖች ቢኖሩም፣ የዓለማችን ታናናሽ ልጆች ሁኔታ በጣም አሳሳቢ እንደሆነ አስጠንቅቀዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

"ከችግር ወደ እንክብካቤ፡ የካቶሊክ እርምጃ ለህፃናት" በሚል ርዕስ ለተቋቋመው የዝግጅት ኮሚቴ ንግግር ሲያደርጉ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሐሙስ ዕለት ጥር 28/2018 ዓ.ም ተሳታፊዎችን አበረታተዋል፣ ባለፈው ዓመት በተካሄደው ዓለም አቀፍ የህፃናት መብቶች ጉባኤ ላይ የተጀመረውን ሥራ ሲቀጥሉ በዚህ ረገድ የምያደርጉትን ጥረት እና ለሕጻናት ሊዩ እንክብካቤ እንዲደረግ ለምያደርጉት ጥረት ቅዱስነታቸው ምስጋናቸውን በድጋሚ አረጋግጠዋል።

የካቶሊክ እርምጃ ለህፃናት ተነሳሽነት የህፃናትን መብቶች፣ ክብር እና ደህንነት ለመጠበቅ ከተሰጠው ምላሽ የተወሰደው በቅድስት መንበር ተቋማት እና የገዳማዊያን/ዊያት ማህበራት ሲሆን የታዳጊዎችን ጥበቃ የጳጳሳዊ ኮሚሽን እና የተለያዩ መንፈሳዊ ማሕበራት እና የሊቃነ ጳጳሳት ባለሙያዎች ተሳትፎ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።

በአምስት አህጉራት ውስጥ ካሉ ልጆች እና ቤተሰቦች ጋር በቀጥታ በመስራት፣ የቤተክርስቲያን መሪዎችን፣ ማህበረሰቦችን እና አጋሮችን ለመደገፍ የህዝብ የድርጊት እቅድ ለማውጣት ያለመ ሲሆን፣ እያንዳንዱ ሕጻን በጠንካራ እና በተቀናጀ ስርዓቶች በተደገፈ ደህንነቱ በተጠበቀ እና እንክብካቤ በሚደረግለት የቤተሰብ አባል  ውስጥ እንዲያድግ ያረጋግጣል።

ዛሬ ብዙ ልጆች የሚያጋጥሟቸው አሳዛኝ እውነታዎች

የድርጅቱ አባላት በቫቲካን በተገኙበት ወቅት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ዛሬ ልጆችና ወጣቶች ለሚያጋጥሟቸው እውነታዎች ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል፣ “ወደ ኢየሱስ ሊመጡ የፈለጉት የዓለማችን ልጆችና ወጣቶች ብዙውን ጊዜ እንክብካቤና የሕይወትን አስፈላጊ ነገሮች የማግኘት እድላቸው በጣም አናሳ መሆኑ” አሳዛኝ ክስተት ሲሉ ገልጸውታል። ብዙውን ጊዜ “እግዚአብሔር የሰጣቸውን አቅም ለማሳካት ጥቂት እድሎች” እንኳን እንደማይሰጣቸው አክለው የገለጹት እቅዱስነታቸው፣ እናም ባለፈው ጊዜ የነበረው የሕጻናት  ሁኔታ ​​እንዳልተሻሻለ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል፣ አክለውም “ልጆችን ከአደጋ በመጠበቅ ረገድ እድገት አለመኖሩን ማወቅ በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው” ብለዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች በጣም ተጋላጭ ከሆኑ ልጆች ወደ ሌላ ፍላጎት መቀየሩን በተመለከተ ሲጠይቁ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ለዘላቂ ልማት ዓለም አቀፍ ቁርጠኝነት ተቀምጧል” የሚለውን ጥያቄ አነሱ፣ “በከፍተኛ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ፣ በደል የሚደርስባቸው፣ በግዳጅ የሚፈናቀሉ እና ትምህርት የሌላቸው ብዙ ልጆች “ከቤተሰቦቻቸው የተለዩ” መሆናቸውን ስንመለከት ጉዳዩ እጅግ በጣም አሳዛኝ እና አስጨናቂ ነው ብለዋል። የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን ትምህርት በማስታወስ፣ የቤተሰብን አስፈላጊነት አረጋግጠዋል፣ የልጆችን “ከእናትና ከአባት ፍቅር የማግኘት መብት፤ ሁለቱም ለልጁ ውህድና ተስማሚ እድገት አስፈላጊ ናቸው" ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

የተዋሃደ አቀራረብ አስፈላጊነት

ወደ ኮሚቴው ሥራ ሲመለሱ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በጉባኤው ላይ ለተነሱት ስጋቶች ተጨባጭ ምላሾችን ለማዘጋጀት ላሳዩት ቁርጠኝነት አድናቆታቸውን ገልጸዋል፣ እና ለተልእኳቸው ሁለት አስፈላጊ ነጥቦችን ለይተዋል።

በመጀመሪያ፣ “ድምፅ ለሌላቸው ሰዎች እየተናገሩ ናቸው” ብለው የተናገሩ ሲሆን እናም ተስፋ መቁረጥ፣ ያልተሳኩ ተነሳሽነቶች ወይም ግድየለሽነት ሲያጋጥም ጽናት እንዲኖራቸው አበረታተዋል።

የኮሚሽኑ አባላት “እያደረጉት ያለው መልካም ነገር ወደፊት እንዲራመድ ፍቀዱለት" ያሉ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “የልጆችን ተሻጋሪ ፍላጎቶች” መፍታት አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፣ እንክብካቤ በአንድ አካባቢ ብቻ የተወሰነ ሲሆን እነዚህ ችላ ሊባሉ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።

በቤተክርስቲያን መዋቅሮች እና በካቶሊክ ድርጅቶች ውስጥ ያሉትን የተለያዩ መንፈሳዊ ተነሳሽነቶችን እና ልዩ ሙያዎች እንዳሉ አምነዋል፣ ነገር ግን ልጆች “በሚዛናዊ” እና “ለአካላዊ፣ ለሥነ ልቦናዊ እና ለመንፈሳዊ ደህንነታቸው” ትኩረት የሚሰጥ እንክብካቤ እንዲያገኙ የበለጠ ስምምነት እና ትብብር እንዲኖር አሳስበዋል።

ልጆችን ያዳምጡ!

በቫቲካን የተዋሃደ የሰብአዊ ልማትን ለማበረታታት የሚሰራው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት፣ የጳጳሳዊ የህይወት አካዳሚ እና የካቶሊክ ገዳማት/ዊያት የበላይ አለቆች ሕብረት ያቀረቡትን ሐሳብ በመደገፍ፣ እነዚህን የጋራ ኃላፊነቶች ለመወጣት “የተጨባጭ እርምጃዎች እና የድርጊት ዕቅዶች” እንዲዘጋጁ ጥሪ አቅርበዋል።

ከሁሉም በላይ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ባለፈው ዓመት ጉባኤ ላይ የቀረቡላቸውን መልእክት በመጥቀስ፣ የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሕጻናትን ለማዳመጥ የነበራቸውን ጽናት አስታውሰው አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡- “ከእናንተ ጋር በመሆን ዓለምን ከመጥፎ ነገሮች ማጽዳት፣ በወዳጅነት እና በአክብሮት መቀባት እና ለሁሉም ሰው ውብ የወደፊት ሕይወት መገንባት እንፈልጋለን!” ብለው መናገራቸውን አስታውሰዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ “የጌታን ቡራኬ በሁላችሁ ላይ ይሆን ዘንድ እንጠይቃለን፣ እና በተለይም ልጆችን በተለይም የሚሰቃዩትን እና ለመኖር መሰረታዊ ፍላጎቶች የሌላቸውን በጸሎት እናስታውሳለን” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን ደምድመዋል።

06 Feb 2026, 15:08