ፈልግ

መተማመን በተባበረ እጅ ሲገለጽ መተማመን በተባበረ እጅ ሲገለጽ  

ር.ሊ.ጳ ሊዮ 'የሰው ልጅ ወንድማማችነት፣ ጊዜ ያለፈበት ቅዤት ሳይሆን በጣም አስፈላጊ ነው' አሉ!

ለዓለም የሰው ልጅ ወንድማማችነት ቀን እና የዛይድ ሽልማት አቀራቢዎች ባስተላለፉት መልእክት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ወንድማማችነትን ከግጭቶች፣ ልዩነቶች እና ውጥረቶች የበለጠ ጠንካራ የሆነ ነገር በመሆኑ የተነሳ እጅግ በጣም አስፈላጊ አድርገው ሲገልጹት፣ በሃሳብ ዓለም ውስጥ ብቻ ተወስኖ እንዳይቀር ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ሰላምን ብዙውን ጊዜ እንደ ጊዜው ያለፈበት ፋሽን ወይም ቅዤት እና የወንድማማችነት መንፈስ ወደ ረቂቅ ሀሳብ በሚቀንስበት ዓለም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የሰው ልጅ ወንድማማችነት ጽንሰ ሐሳብ ሳይሆን በአስቸኳይ አስፈላጊ መሆኑን አጥብቀው ይናገራሉ። ይህ የካቲት 27/2018 ዓ.ም ለዓለም የሰው ልጅ ወንድማማችነት ቀን እና የዛይድ ሽልማት አቀራቢ የታተመው ጽሑፍ ማዕከላዊ መልእክት ነው፣ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከግጭቶች፣ ልዩነቶች እና ውጥረቶች የበለጠ ጠንካራ የወንድማማችነት መንፈስ እንዲጠናከር ጥሪ አቅርበዋል።

አስቸኳይ የወንድማማችነት መንፈስ አስፈላጊነት

የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እና ታላቁ ኢማም አህመድ አል-ታይብ የዓለም ሰላም እና አብሮ የመኖር ሰብአዊ ወንድማማችነት ሰነድ የተፈረሙበትን ሰባተኛ ዓመት እየታወሰ ሲሆን - ይህ በዓል "በሰብአዊነታችን ውስጥ እጅግ ውድ እና ሁሉን አቀፍ የሆነውን፣ ወንድማማችነታችንን፣ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረውን እያንዳንዱን ሰው የሚያስተሳስረውን የማይበጠስ ትስስር" ለማክበር የሚያስችል አጋጣሚ ነው።

"ዛሬ፣ የዚህ ወንድማማችነት አስፈላጊነት የሩቅ ሀሳብ ሳይሆን በአስቸኳይ አስፈላጊ ነው" ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ።

ወንድማማችነት፣ የግጭቶች የመጀመሪያ ሰለባ

ቅዱስ አባታችን ዛሬ በአመፅ እና በጦርነት አሰቃቂ ሁኔታ የሚሰቃዩትን ብዙ - "በጣም ብዙ" ወንድሞች እና እህቶችን ይጠቅሳሉ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በጣሊያነኛ ቋንቋ "ፍራቴሊ ቱቲ" (ሁላችንም ወንድማማቾች ነን) በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ የጠቀሱትን ቃል ያስታውሳሉ፡- "የእያንዳንዱ ጦርነት የመጀመሪያ ሰለባ የሰው ልጅ ቤተሰብ ለወንድማማችነት ያለው ተፈጥሯዊ ጥሪ ነው" ሲሉ በድጋሚ አስታውሰዋል።

“ሰላምን በጋራ የመገንባት ህልም ብዙውን ጊዜ ‘ያረጀ የቅዤት ሐሳብ’ ነው ተብሎ በሚታሰብበት በዚህ ወቅት፣ የሰው ልጅ ወንድማማችነት ሕያው እውነታ መሆኑን፣ ከሁሉም ግጭቶች፣ ልዩነቶች እና ውጥረቶች የበለጠ ጠንካራ መሆኑን በፅኑ እምነት መግለጽ አለብን” ሲሉ ቅዱስነታቸው ያስረዱ ሲሆን ይህም “በየቀኑ፣ በተጨባጭ ለማክበር፣ ለመጋራት እና ለርህራሄ” ቁርጠኝነትን በመውሰድ መከናወን አለበት ብለዋል።

በ“የሃሳቦች ዓለም” ውስጥ አለመቆየት

“ቃላት በቂ አይደሉም” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ባለፈው ታህሳስ ወር የዛይድ ሽልማት ኮሚቴ አባላትን ባነጋገሩበት ወቅት ቀደም ብለው መናገራቸው ይምታወስ ሲሆን በዚህ መልእክት ውስጥ የሚያቀርቡት ጥሪ፣ ጥልቅ እምነታችን “በሚጨበጥ ጥረት የማያቋርጥ እድገት” እንደሚያስፈልግ በማስታወስ ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መጀመሪያ የጻፉትን ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ በላቲን ቋንቋ "ዲሌክሲ ቴ"ን (ወደድኳችሁ) በመጥቀስ  በዚህ ጽሑፍ ውስጥ “በሀሳቦች እና በንድፈ ሐሳቦች ዓለም ውስጥ መቆየት፣ በተደጋጋሚ እና ተግባራዊ በሆነ የበጎ አድራጎት ተግባራት አማካኝነት መግለጫ መስጠት አለመቻል፣ በመጨረሻ በጣም የምንወዳቸውን ተስፋዎች እና ምኞቶች እንኳን እንዲዳከሙ እና እንዲጠፉ ያደርጋል” ሲሉ ጽፈው እንደ ነበረ አስታውሰው ከዚያም ወደ "ፍራቴሊ ቱቲ" (ሁላችንም ወንድማማቾች ነን) ሐሳባቸውን በመመለስ  እንደ ወንድማማቾች እና እህቶች፣ ሁላችንም ከዳር እስከ ዳር እንድንወጣ እና “በጋራ የመተባበር ስሜት እንድንሰባሰብ” ተጠርተናል ብለዋል።

የሽልማት ተቀባዮቹ “የተስፋ ዘሪዎች” ናቸው

ቅዱስ አባታችን በመቀጠል የዛይድ ሽልማት እነዚህን እሴቶች ወደ “የሰው ልጅ ደግነት እና የበጎ አድራጎት እውነተኛ ምስክርነቶች” ለተረጎሙት ሰዎች ክብር ይሰጣል በማለት የጻፉ ሲሆን የሽልማቱ ተቀባዮቹን በቀጥታ ሲያነጋግሩ - የአዘርባጃን ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭ፤ የአርሜኒያ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሺንያን፤ የፍልስጤም ድርጅት ታዎን ዋና ጸኃፊ ወ/ሮ ዘርቃ ያፍታሊ፤ ተሸላሚዎች እንደሚሆኑ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የጠቆሙ ሲሆን “ብዙ ጊዜ ድልድዮችን ከመገንባት ይልቅ ግድግዳዎችን በሚገነባ ዓለም ውስጥ የተስፋ የመልካም ዘር ዘሪዎች” ብለው ይገልጿቸዋል።

ከቀላል የግዴለሽነት ጎዳና ይልቅ አስቸጋሪ የሆነውን የአንድነት መንገድ በመምረጥ፣ በጣም ጥልቅ የሆኑ ክፍፍሎች እንኳን በተጨባጭ እርምጃ ሊፈወሱ እንደሚችሉ አሳይተዋል። ስራቸው የወንድማማችነት ብርሃን በወንድማማችነት ጨለማ ላይ ማሸነፍ እንደሚችል ያላቸውን እምነት ይመሰክራል ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

ጎረቤቶቻችን ከእንግዲህ እንደ እንግዳ ወይም እንደ ስጋት እንዳይታዩ ያድርጉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ መልእክታቸውን የሚያጠቃልሉት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ለተነሳሽነቱ ጽኑ ድጋፍ እንዲሁም ለዛይድ ኮሚቴ “ራዕይ እና የሞራል እምነት” ላሳዩት ትብብር ምስጋናቸውን በመግለጽ ነው።

በመጨረሻም፣ “የወንድማማችነት ፍቅር ተለዋዋጭነት የሁሉም ሰው የጋራ መንገድ እንዲሆን እና ‘ሌላው’ እንደ እንግዳ ወይም እንደ ስጋት እንዳይታይ፣ ነገር ግን እንደ ወንድም ወይም እህት እንዲታወቅ አብረን መስራታችንን እንቀጥል” ብለዋል።

05 Feb 2026, 13:49