ፈልግ

የሳህል ቀጠና የሳህል ቀጠና   (AFP or licensors)

ለሳህል ሀገራት፣ የቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ድርጅት አዲስ ውል

ርዕሰ ሊቃነ ሊዮ አሥራ አራተኛ እ.አ.አ በ1984 ዓ.ም በዚህ በሳህል አገራት ክልል ውስጥ የሚኖሩትን እና በድርቅ፣ በበረሃማነት እና በረሃብ የተጎዱትን ሰዎች ስቃይ ለማስታገስ የተቋቋመውን የቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ድርጅት አዲስ ውል አጽድቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

እ.አ.አ በጥር 29/ 2018 ዓ.ም የቫቲካን ዋና ጸኃፊ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ጋር ባደረጉት ንግግር፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ “የሳህል የቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ድርጅት” የተሻሻለውን ውል አጽድቀዋል፣ ይህም ቀኖናዊ ሁኔታውን ከሮማ ኩሪያ ጋር ለተያያዙ የሕግ ሰዎች አሁን ካለው የቁጥጥር ማዕቀፍ እና ከቅድስት መንበር ሐዋርያዊው የባለቤትነት መብት ደንቦች ጋር በማጣጣም ነው።

ይህ ሐሙስ ጥር 28/2018 ዓ.ም በቅድስት መንበር የፕሬስ ጽ/ቤት በታተመው መግለጫ ላይ ዜናው ታውጇል።

የድርጅቱ ታሪክ

የድርጅቱ ታሪክ የሚጀምረው በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.አ.አ በግንቦት 10/1980 ዓ.ም በኡጋዱጉ የተናገራቸው ቃላት ናቸው፣ ይህም ስሙን የያዘው የሳህል ድርጅት እንዲፈጠር ምክንያት ሆነ።

ከፍተኛ የውሃና የምግብ እጥረት እና እየጨመረ የመጣውን የበረሃማነት አደጋ ለደረሰበት ክልል ለተከሰቱት ችግሮች ምላሽ በመስጠት፣ የፖላንድ ተወላጅ የሆኑት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እራሳቸውን “ድምፅ የሌላቸው ሰዎች ድምፅ፤ ውሃና ዳቦ ስለሌላቸው የሞቱት ንፁሃን ሰዎች ድምፅ፤ ልጆቻቸው ለምን እንደሞቱ ሳይረዱ የሞቱት አባቶችና እናቶች ድምፅ” በማድረግ መላው ዓለም እርምጃ እንዲወስድ በወቅቱ አጥብቀው ጥሪ አቅርበው ነበር።

የሳህል የዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ድርጅት በጳጳሱ እ.አ.አ የካቲት 22/1984 ዓ.ም ተቋቋመ፣ ይህም እርሳቸው በወቅቱ ያቀረቡት የርዳታ ጥሪ ተግባራዊ እንዲሆን እና በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ላሉ ወንድሞችና እህቶች ያላቸውን ፍቅር የሚያሳይ ውጤታማ ምልክት እንዲሆን ነበር።

ህጉ ድርጅቱ በቫቲካን የተቀናጀ የሰው ልጅ ልማትን ለማስተዋወቅ የሚሰራው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት ዋና አካል ሲሆን በቫቲካን ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ ለሚገኙ የሕግ ሰዎች በሚተገበር ሕገ ቀኖና እና በቫቲካን የሲቪል ሕግ የሚተዳደር ነው።

የድርጅቱ ሕጋዊ ዋና መሥሪያ ቤት በቫቲካን ሲሆን የሥራ ማስኬጃ ዋና መሥሪያ ቤቱ ደግሞ ቡርኪና ፋሶ ዋና ከተማ በኡጋዱጉ ይገኛል።

አዲሱ ሕግ፣ የረጅም እና የጋራ የተሃድሶ ሂደት ውጤት

በአቋም መግለጫው፣ በቫቲካን የተዋሃደ የሰው ልጅ ልማትን የሚያበረታታው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት አዲሱ ሕግ በመታተሙ ያገኘውን እርካታ ገልጾ “የድርጅቱ ረጅም እና የጋራ የተቋማዊ ተሃድሶ ሂደት ውጤት” ሲል ገልጾታል።

እ.አ.አ በታህሳስ እ.አ.አ 2024 ዓ.ም የጳጳሳዊ ልዑካን ጳጳስ ፍሎሬንት ሃሳ ኮኔ (የሳን፣ ማሊ ጳጳስ፣ የፋውንዴሽኑ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል) ሹመት “የዚህ ሂደት የመጨረሻ ደረጃዎችን ከቅድስት መንበር ጋር በተከታታይ በመነጋገር ለማጀብ ታስቦ” የተደረገ ነበር ሲል መግለጫው ያስረዳል።

መግለጫው ይህ ሂደት በቫቲካን የተዋሃደ የሰው ልጅ ልማትን የሚያበረታታው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት ከቅድስት መንበር ዋና ጸኃፊ፣ ከኢኮኖሚ ሴክሬታሪያት እና ከቫቲካን ገዥው አስተዳደር ጋር በመተባበር እንዴት እንደተከናወነ አጎልቶ ያሳያል።

በአዲሱ ደንብ፣ መግለጫው “ድርጅቱ ወደ አካባቢው ቤተክርስቲያን የበለጠ ቅርብ ይሆናል፣ ሂደቶችን ወደ ፈጣን እና የበለጠ ዘላቂ እድገት እና ግዛቱ ለሚያጋጥሙት ብዙ ተግዳሮቶች በተቀናጀ መንገድ ምላሽ ይሰጣል” ሲል ያረጋግጣል።

በተዋሃደ የሰው ልጅ እድገት መንፈስ ውስጥ መሥራት

ድርጅቱ ከሳህል ክልል የተውጣጡ ዘጠኝ አገሮችን ያጠቃልላል፤ ቡርኪናፋሶ፣ ኬፕ ቨርዴ፣ ጋምቢያ፣ ጊኒ-ቢሳው፣ ማሊ፣ ሞሪታኒያ፣ ኒጀር፣ ሴኔጋል እና ቻድ ናቸው።

"የድርጅቱ ዋና ዓላማ አገራቸውን እና ሌሎች ሰዎችን ያለምንም አድልዎ ለማገልገል፣ በተዋሃደ የሰው ልጅ እድገት እና አንድነት መንፈስ፣ በረሃማነትን እና መንስኤዎቹን ለመዋጋት እና በሳህል አገሮች ውስጥ ለድርቅ ተጎጂዎች እፎይታ ለመስጠት ራሳቸውን የወሰኑ ግለሰቦችን ማሰልጠን ነው" ሲል መግለጫው አክሎ ገልጿል።

ስለዚህ ድርጅቱ የአካባቢ አመቻቾችን እና ባለሙያዎችን ማሰልጠን እንዲሁም በሚከተሉት ዘርፎች ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ ማድረግን ቅድሚያ ይሰጣል፡ የቴክኒክ ልማት፣ ማህበራዊ-ጤና አጠባበቅ፣ ማህበራዊ-ግብርና፣ ማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ፣ የተቀናጀ ልማት እና አካባቢ ጥበቃ የተመለከቱ ተግባራት ይደግፋል።

ጳጳሱ በዓለም ዙሪያ ካሉ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ከተዋጣው የገንዘብ ስብስቦች የሚገኘውን ገቢ ለድርጅቱ ለሳህል ጥቅም ያዘጋጃሉ።

የድርጅቱ የአስተዳደር አካላት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣ ፕሬዝዳንት፣ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ ዋና ፀሐፊ፣ ኦዲተር እና ገንዘብ ያዥ ናቸው። በየካቲት ወር አጋማሽ የዳይሬክተሮች ቦርድ ስብሰባ በሴኔጋል ዳካር ይካሄዳል።

 

06 Feb 2026, 15:13