ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከሊቀ ጳጳሳቱ ዓለም አቀፍ የጸሎት አውታረ መረብ አመራርና አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከሊቀ ጳጳሳቱ ዓለም አቀፍ የጸሎት አውታረ መረብ አመራርና አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት   (@Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡ ወጣቶች፣ ለዓለም ፍላጎቶች የሚቀጥለው ትውልድ ሸምጋዮች ሁኑ አሉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከሊቀ ጳጳሳቱ ዓለም አቀፍ የጸሎት አውታረ መረብ አመራርና አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት ለሥራቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ተልእኳቸውን እንዲቀጥሉ ያበረታቱ ሲሆን እንዲሁም ወጣቶች በዚህ ተልእኮ በንቃት እንዲሳተፉ ይጋብዛሉ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ለሊቀ ጳጳሳቱ ዓለም አቀፍ የጸሎት አውታረ መረብ አመራርና አባላት፣ ላከናወኑት ተግባር ምስጋናቸውን አቅርበዋል፣ ወጣቶችንም ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርቡ አበረታተዋል። “በተለይ ወጣቶች ለመላው ዓለም ፍላጎቶች ከሚቀጥለው ትውልድ ጋር የአሸማጋይነት ሚናቸውን እንዲወጡ እና እንዲመሰርቱ መጋበዝ በጣም አስፈላጊ ነው” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አርብ፣ ጥር 23/2018 ዓ.ም በቫቲካን ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል።

ብዙ ወጣቶች “ከሙታን ከተነሳው ኢየሱስ ጋር የበለጠ ጥልቅ እና የግል ግንኙነት እየፈለጉ ስለሆነ፣ የቅዱስ ቁርባን ወጣቶች ንቅናቄ ማሕበር ከጌታችን ጋር የበለጠ ጥልቅ ቅርበት እንዲፈጥሩ ለመርዳት በተለይ ፍሬያማ መንገድ ሊሆን ይችላል” ሲሉ አፅንዖት ሰጥተው ገልጸዋል።

ተሳታፊዎቹ "በዚህ ኔትወርክ ወይም የትሥሥር መረብ ውስጥ የበለጠ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፣ ይህም የተለያዩ ባህሎችን፣ ቋንቋዎችን እና መንፈሳዊ ፀጋዎችን በጋራ ተልዕኮ ውስጥ የሚያጣምር ነው" ብለዋል።

የሊቀ ጳጳሱ ዓለም አቀፍ የጸሎት አውታረ መረብ ለኢየሱሳዊያን ማኅበር በኃላፊነት የተሰጠ ተግባር ነው። በየወሩ አውታረ መረቡ የሊቀ ጳጳሱን የጸሎት ዓላማ ይለቃል፣ ይህም በሰው ልጅ እና በቤተክርስቲያን ፊት በሚገጥሟቸው ተግዳሮቶች ላይ ያተኩራል። አውታረ መረቡ የተመሠረተው በኢየሱስ ልብ መንፈሳዊነት ላይ ነው፣ በተለይም በ"የልብ መንገድ" የመመስረቻ መርሃ ግብር አማካኝነት የተቋቋመ ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህ መንፈሳዊነት ለአውታረ መረቡ እና አባላቱ "ጌታችንን በቅርበት እንዲያውቁ እና የበለጠ ርኅሩኅ እና ማሐሪ እንዲሆኑ" እንዴት እንደሚፈቅድ አጉልተው ገልጸዋል፣ ምክንያቱም "ለችግረኞች የጸሎት ድጋፍ" ያደርጋል ብለዋል።

"በሐዋርያዊ አገልግሎታችሁ የተጠመቁ ሰዎች የክርስቶስ ወዳጆች እና ሐዋርያት መሆናቸውን እንዲረዱ መርዳት እንደምትቀጥሉ ተስፋ አደርጋለሁ" ሲሉ አፅንዖት ሰጥተው ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

ጸሎት የቤተክርስቲያኒቱ ዋና አካል ነው

ከዚያም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "በዚህ ዓለም አቀፍ አውታረ መረብ ውስጥ በየቀኑ እነዚህን የጸሎት ሐሳቦች በእግዚአብሔር ፊት ለሚያቀርቡ ለአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች" የጸሎት ዓላማቸውን "ለማሰራጨት ላደረጉት ጥረት" ለተገኙት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

“እንዲህ ዓይነቱ ጸሎት የክርስቶስ አካል የወንጌላዊነት ሥራ ውጫዊ አካል አይደለም፣ ነገር ግን የእሱ ዋና አካል ነው” ሲሉ የተናገሩት ቅዱስነታቸው በተለይ የኔትወርኩን ዓለም አቀፍ ዳይሬክተር አባ ክሪስቶባል ፎኔስን እንዲሁም ምክትል ዳይሬክተሮች ቤቲና ራድ እና አባ ሚጌል ሜሎ እንዲሁም ይህንን ተልዕኮ የሚደግፉ አባላትን እና አጋሮችን ሁሉ አመስግኗል።

30 Jan 2026, 15:28