ር.ሊ.ጳ ሊዮ ለአሜሪካ ወጣቶች፣ እግዚአብሔር ላዘጋጀልህን ነገር ክፍት እንሁን ማለታቸው ተገለጸ
“ምን ትፈልጋላችሁ?”
ኢየሱስ ለመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት ያቀረበው ጥያቄ በልባቸው ውስጥ ያለውን እንደሚያውቅ ያሳያል፣ “እረፍት የሌላቸው፣ ግን በጥሩ መንገድ” ላይ የሚጓዙ ነበሩ፣ ለእግዚአብሔር ክፍት ነበሩ እና በሕይወታቸው ውስጥ ትርጉም ለማግኘት ይናፍቁ ነበር ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።
በዩናይትድ ስቴትስ በሚካሄደው አመታዊ “SEEK” የወጣቶች ኮንፈረንስ ላይ ለሚሳተፉ ወጣቶች በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ኢየሱስ ዛሬ እያንዳንዳችንን ተመሳሳይ ጥያቄ እየጠየቀን ነው ብለዋል።
“መልሱ” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ንግግራቸውን የቀጠሉ ሲሆን መልሱ “በአንድ ሰው ውስጥ ይገኛል፡ ጌታ ኢየሱስ ብቻ እውነተኛ ሰላምና ደስታን ያመጣልናል፣ እና እያንዳንዱን ጥልቅ ምኞታችንን ያሟላል” ያሉ ሲሆን የመጀመሪያዎቹን ደቀ መዛሙርት ተሞክሮ ላይ ማሰላሰላቸውን በመቀጠል፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ኢየሱስ የት እንደሚኖር መጠየቃቸውን አስታውሰዋል። “ለሌላ ሰው ኢየሱስ የእግዚአብሔር በግ መሆኑን መንገር ብቻ በቂ አልነበረም” ብለዋል። “ከእርሱ ጋር ጊዜ በማሳለፍ በአካል እሱን ለማወቅ ፈልገው ነበር" ያሉት ቅዱስ አባታችን ለወጣቶችም በጉባኤው ወቅት “ከጌታ ጋር ጊዜ የማሳለፍ” እድል እንደሚያገኙ ነግሯቸዋል - አንዳንዶቹ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ሌሎቹ ደግሞ ከኢየሱስ ጋር ያላቸውን ግንኙነት የማጠናከር እድል እንደሚያገኙ ጭምር ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ተሳታፊዎችን “ጌታ ለእነሱ ስላዘጋጀላችሁ ነገር ክፍት እንዲሆኑ” አበረታተዋል፣ ደቀ መዛሙርቱ ከኢየሱስ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት ለጥቂት ቀናት ብቻ ቢሆንም፣ ሕይወታቸውን ለዘላለም እንደለወጠው አስታውሷቸዋል።
ጳጳሱ ኢየሱስን ማወቃቸውን እንዲቀጥሉ ያበረታቱ ሲሆን ልክ ለቅዱስ እንድርያስ እንዳደረገው ሁሉ፣ ለወንድማቸው ለቅዱስ ጴጥሮስ መሲሑን እንዳገኘ ወዲያውኑ እንደ ነገረው ሁሉ እናንተም ኢየሱስን መገናኘታችሁን ለሁሉም መስክሩ ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በጉባኤው ላይ ያሉ ወጣቶች “በዚህ በሚስዮናዊነት ቅንዓት በዙሪያችሁ ላሉት ከጌታ ጋር ከነበራችሁት እውነተኛ ግንኙነት የተቀበላችሁትን ደስታ እንዲያካፍሉ ጸልየዋል” እግዚአብሔርን ለምን እንደሚጠራቸው ለመጠየቅ እንዳይፈሩ ያበረቷቷቸው ሲሆን ለክህነት፣ ለሃይማኖታዊ ሕይወት ወይም ለጋብቻ እና ለቤተሰብ ሕይወት የቀረበላችሁን ጥሪ ከተሰማችሁ “አትፍሩ… እግዚአብሔር ይመራችኋል እና ይጠብቃችኋል !” ብለዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ መልእክታቸውን የደመደሙት አድማጮቻቸውን “ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን እንድናውቀው፣ በእውነት እንድናውቀው፣ ለእኛ ያለውን ፍቅር እና ለእያንዳንዳችን ሕይወታችን ያለውን አስደናቂ ዕቅድ እንድናውቅ” ማርያምን እንዲጠይቁ በመጋበዝ ነው።
በካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሕብረት (FOCUS) የተደገፈው አመታዊው የSEEK" ኮንፈረንስ በሺዎች የሚቆጠሩ ካቶሊኮች በጸሎት፣ በአምልኮ፣ በቅዱስ ቁርባን እና አነቃቂ ተናጋሪዎች ክርስቶስን ለመገናኘት የሚሰበሰቡበት የአምስት ቀናት ተሞክሮ ነው።
ከ25,000 በላይ ወጣቶች በዚህ ሳምንት እ.አ.አ ከጥር 1-5/2026 ባለው የዩናይትድ ስቴትስ የኮሎምበስ፣ ኦሃዮ ከተሞች፣ ዴንቨር፣ ኮሎራዶ እና ፎርት ዎርዝ፣ ቴክሳስ በሚካሄደው 26ኛው የSEEK ኮንፈረንስ ላይ እየተሳተፉ ነው።
