ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳ ሊዮ የሰላም ዓመት ለመገንባት ዛሬ እንጀምር ማለታቸው ተገለጸ!

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የማሕበረሰብ ክፍሎች ዘንድ የተከበረውን የ2026 አዲስ አመት አስመልክተው በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ባደረጉት የመጀመሪያ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ሁሉም ሰው “ልባችንን በማስታጠቅ እና ከማንኛውም ዓይነት ዓመፅ በመቆጠብ የሰላም ዓመት እንዲገነባ” አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የማሕበረሰብ ክፍሎች ዘንድ የተከበረውን የ2026 ዓ.ም የመጀመሪያ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ወደ 40,000 የሚጠጉ ምዕመናን ቅዱስነታቸው አዲስ አመትን አስመልክተው የሚሰጡትን ቡራኬ እና የአዲስ አመት ሰላምታን ለመቀበል በሥፍራው የተገኙ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ለሰላም እና ለበጎ ነገር ሁሉ ልባዊ ምኞታቸውን አስተላልፈዋል። እንዲሁም ለጣሊያን ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎትን ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ቅዱስነታቸው ካደርጉ በኋላ ባስተላለፉት የአዲስ አመት መልእክት ባለፉት 58 ዓመታት - እ.አ.አ በ1968 ዓ.ም በሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ጳውሎስ 6ኛ ምኞት - ጥር 1 የዓለም የሰላም ቀን ሆኖ መከበር መጀመሩን ጠቅሰዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ለዚያ ቀን ይፋ ባደረጉት መልእክት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡ በኋላ “ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን!” ብለው እንደ ተናገሩ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል፣ ይህም እግዚአብሔር የሰጠው” ሰላምታ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

ቀጥለውም ይህ ሰላም፣ “ያለ ትጥቅና ትጥቅ የሚፈታ፣ ከእግዚአብሔር የተገኘ፣ ያለ ቅድመ ሁኔታ የፍቅሩ ስጦታ የሆነ፣ እና ለኃላፊነታችን የተሰጠ ነው” ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

ወደ አዲሱ የሰላም ዓመት ጥሪ

በዚህ ኃላፊነት፣ ቅዱስ አባታችን በክርስቶስ ጸጋ ሁሉንም ሰው ዛሬ “የሰላም ዓመት መገንባት፣ ልባችንን ማስታጠቅ እና ከሁሉም ዓመፅ መቆጠብ” የሚለውን ጥያቄ እንዲጀምር ጥሪ አድርገዋል።

በዓለም ዙሪያ ያሉ ብዙ ሰዎችና ድርጅቶች ዓመፅን ለማስቆም ራሳቸውን ሰጥተው ሰላምን ለመገንባት ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ተነሳሽነቶች እንደፈጠሩ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በተለይም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እ.አ.አ በታህሳስ 31/2025 ዓ.ም ምሽት በካታኒያ፣ ጣሊያን የተካሄደውን ብሔራዊ ሰልፍ እንዲሁም የቅዱስ ኤጂዲዮ ማህበረሰብ አባላት የሚያካሂዱትን የሰላም ጥሪ ሰልፍ አጉልተው ገልጸዋል።

በመጨረሻም፣ በዩናይትድ ስቴትስ ከሪችላንድ፣ ኒው ጀርሲ የመጡ ተማሪዎችንና መምህራንን ለመቀበል ጊዜ የወሰዱት ቅዱስነታቸው የአዚዚው የቅዱስ ፍራንችስኮስ ሞት ዝክር 800ኛ ዓመት ክብረ በዓልን በማስታወስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የመልአከ እግዚአብሔርን ጸሎት ካደርጉ በኋላ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰደውን የቅዱስ ቡራኬ ጥቅስ በመጠቀም “ጌታ ይባርክህ ይጠብቅህም፤ ጌታ ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም፤ ጌታ ፊቱን ወደ አንተ ይመልስ፣ ሰላምንም ይስጥህ” ካሉ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ማርያም የእግዚአብሔር እናት “በአዲሱ ዓመት በጉዟችን እንድትመራን” እንማጸናት ካሉ በኋላ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

 

02 Jan 2026, 16:59