የር.ሊ.ጳ ሊዮ የጸሎት ሐሳብ 'በእግዚአብሔር ቃል ላይ ተመስርቶ ጸሎት ማድረግ' የሚል ጭብጥ ያዘለ ነወ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የማሕበረሰብ ክፍሎች ዘንድ በአዲሱ ዓመት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ “ከጳጳሱ ጋር ጸልዩ” በመባል ለሚታወቀው አዲስ ተነሳሽነት ድጋፋቸውን ሰጥተዋል፣ ይህም ወርሃዊ የጸሎት ዓላማቸውን በመላው ዓለም ወደ ቤተክርስቲያን ያመጣል።
አንድ የጋዜጣዊ መግለጫ አዲሱ ተነሳሽነት የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጳጳሱን የጸሎት ሐሳብ በቪዲዮ እና በድምጽ ለማካፈል ያላቸውን ፍላጎት እንደሚቀጥል ገልጿል።
“ይህ ተነሳሽነት የጳጳሱን የጸሎት ሐሳብ እይታን ለማሳደግ ያለመ ነው፣ ለጸሎት ተስማሚ የሆነ ቋንቋን አዲስ ቅርጽ በመጠቀም፣ በተለይም በዛሬው የዲጂታል ግንኙነት ዓለም ውስጥ በመላው ዓለም ምእመናንን በተሻለ ሁኔታ ለመድረስ” ጠቃሚ ነው ሲል መግለጫው ገልጿል።
የእግዚአብሔር ቃል “በጨለማ ውስጥ ተስፋ” ነው።
በአዲስ ቀረጻ በተሰራው የመጀመሪያ ቪዲዮ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ምእመናን በእግዚአብሔር ቃል ላይ ተመስርተው አዘውትረው እንዲጸልዩ ጋብዘዋል። ቅዱስ ወንጌል ብቻ ለሰው ልጅ ልብ ሰላምና ሙላት መስጠት እንደሚችል ተናግረዋል፣ ይህም እረፍት የሌለው እና ትርጉሙን ለመረዳት የሚራብ መሆኑን ገልጸዋል።
"በቅዱሳት መጻሕፍት አማካይነት በየቀኑ እንድንሰማህ አስተማረን" ብለዋል፣ "በድምፅህ እንድንፈተን እና ውሳኔዎቻችንን ከልብህ ጋር ካለው ቅርበት በመነሳት እንድንወስን" ይረዳናል ሲሉ ተናግረዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር ቃል "በድካም፣ በጨለማ ውስጥ ተስፋ እና በማህበረሰባችን ውስጥ ጥንካሬን ይሰጣል" ያሉ ሲሆን ሁሉም ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር ቃል ጥንካሬ እና መመሪያ እንዲያገኙ እና ቤተክርስቲያን ሁል ጊዜ ወንጌልን በደስታ እንድታውጅ ጸልየዋል።
"በቃልህ አማካኝነት ከአንተ ጋር በመገናኘታችን እምነታችን ይጨምራል" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ደምድመዋል፣ "ከሌሎች ጋር እንድንገናኝ፣ በጣም ተጋላጭ የሆኑትን እንድናገለግል፣ ይቅር እንድንል፣ ድልድዮችን እንድንገነባ እና ሕይወትን እንድናውጅ ከልብ ያነሳሳናል" ሲሉ አክለው ገልጸዋል።
ከሊቀ ጳጳሱ ጋር እንድንጸልይ የቀረበልን የታደሰ ግብዣ
ቀደም ሲል "የጳጳሱ ቪዲዮ" በመባል የሚታወቀው አዲሱ "ከሊቀ ጳጳሱ ጋር ጸልዩ" የተሰኘው ተነሳሽነት ቤተክርስቲያንን ከቅዱስ አባታችን ዕለታዊ ጸሎት ጎን ለማዋሃድ ይፈልጋል።
እንደ ሊቀ ጳጳሳቱ ዓለም አቀፍ የጸሎት ትስስር ዓለም አቀፍ ዳይሬክተር አባ ክሪስቶባል ፎኔስ ገለጻ፣ የተነሳሽነቱ አዲሱ ቅርጸት ካቶሊኮች ሊቀ ጳጳሱን በጥልቀት እንዲደግፉ ይዘቱን ቀላል ያደርገዋል ያሉ ሲሆን “ከጳጳሱ ጋር ጸልዩ፤ ማንኛውም ሰው በየትኛውም ቦታ ቢሆን ቅዱስ አባታችን በየወሩ ለሚያቀርቡት ሐሳብ እና ዓላማ እንዲጸልዩ ክፍት በር እንዲሆን ያለመ ነው፤ በሲኖዳሳዊነት እይታ ከእርሳቸው ጋር ጸልዩ፣ እያንዳንዳችን ምላሽ የምንሰጥበት ቀላል እና ሁሉን አቀፍ ግብዣ ነው” ሲሉ አክለው ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱን የሚያስጀምረው የጳጳሱ የጥር ወር ዓላማ ክርስቲያኖች “ክርስቶስን ለመገናኘት እንደ ልዩ ቦታ የቅዱሰ ቅዱሳን መንፈሳዊ ኃይል እንደገና እንዲያገኙ ያሳስባል” ሲል የጋዜጣዊ መግለጫው ገልጿል።
የቪዲዮ መልእክቱ የተቀረፀው በቫቲካን ከተማ ውስጥ ካሉት ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት አንዷ በሆነችው በቅዱስ ፔሌግሪኖ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሲሆን መሰረቱም እ.አ.አ ከ795 ዓ.ም. የጀመረ ነው።
ወግ እንደሚያሳየው በጳጳስ ሊዮ ሳልሳዊ ዘመን ንጉሠ ነገሥት ቻርለማኝ የሮም ቄስ እና የኦክሴሬ የመጀመሪያው ጳጳስ የነበሩትን የቅዱስ ፔሌግሪኖን ቅርሶች በቤተክርስቲያኗ ውስጥ እንዲያስቀምጡ ሰጥተው እንደ ነበረ የሚታወስ ሲሆን በጥንታዊው ቪያ ፍራንሲጌና አጠገብ የሚገኘው የቅዱስ ፔሌግሪኖ ቤተክርስቲያን በታሪክ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ መካነ መቃብር ለሚሄዱ ምዕመናን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት የምያስተላልፍ እና የጸሎት ቦታ እንደ ሆነም ይታወቃል።
