ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ   (@Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለጣሊያን ጋዜጣ በጻፉት መልእክት የፕሬስ ነፃነትን አወድሰዋል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ለጣሊያን ጋዜጣ "ላ ሪፐብሊካ" 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፣ ጋዜጣው “ሁልጊዜም ነፃ እና ውይይት የተሞላበት፣ እውነትን ፍለጋ እና ያለ ጭፍን ጥላቻ የሚንቀሳቀስ ግንኙነትን ያበረታታል” የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

"የጣሊያን፣ የዓለምን እና የቤተክርስቲያንን ታሪክ፣ ከአገሮች ጋር የማያቋርጥ ግንኙነት፣ የጥያቄ ነፃነት እና ውይይትን እንደ ሰላም ግንባታ ልዩ መንገድ አድርገው በመተረክ ሃምሳ ዓመታትን አሳልፈዋል" እነዚህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ለጣሊያኑ ጋዜጣ "ላ ሪፐብሊካ" 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በላኩት መልእክት ከተወያዩባቸው ጭብጦች መካከል ናቸው፣ ለአዘጋጁ ማሪዮ ኦርፌኦ በጻፉት መልእክት እንደገለጹት።

ልዩ ትኩረት

በደብዳቤያቸው፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለግማሽ ምዕተ ዓመት ታሪክ ለሚተርኩ ጋዜጠኞች “እስከዚህ ደረጃ ያደረሳችሁን ከአንባቢዎችዎ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ማሳደግ አለባችሁ” ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

“የእናተ ጋዜጣ በብዙ ከተሞች ላይ የተመሠረተ፣ ነገር ግን በሮም የሊቀ ጳጳሱ ሀገረ ስብከት፣ ዋና መሥሪያ ቤቱ እና በጣሊያን እና በዓለም ዙሪያ የተከናወኑ ክስተቶችን ለመመልከት የሚያስችል ልዩ ቦታ ያለው። የእነዚህን ሃምሳ ዓመታት ገጾች አንብበዋል፣ እና የቤተክርስቲያኗን ታሪክ በነፃነት ዘግበዋል” ሲሉ ቅዲስነታቸው አክለው ገልጸዋል።

የፕሬስ ነፃነት

ነፃነት፣ የታሪክ አጻጻፍ እና በዓለም ላይ ልዩ የሆነ የአመለካከት ነጥብ የፕሬስ ነፃነት ማዕከል ናቸው ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተናግረዋል። “በተለያዩ የአመለካከት፣ የአስተያየት እና የባህል ልዩነቶች መካከልም ቢሆን ጋዜጣው ሁልጊዜም በግልጽነት እና በታማኝነት መንቀሳቀስ አለበት” ሲሉ ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አክለውም ጋዜጣው “ጠላትነት በማይኖርበት ጊዜ ለጋራ ጥቅም እና ለሰው ልጅ ቤተሰብ አንድነት አስተዋጽኦ የሚያደርግ የውይይት እድል መስጠት አለበት። በዚህ መንገድ ውይይት ግጭትን ያሸንፋል እና ሰላምን ይገነባል” ብለዋል።

መልእክታቸውን ወደ ፍጻሜ በማምጣት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጋዜጣው “ሁልጊዜም ነፃ እና ቃለ ምልልስ የሚያደርግ፣ እውነትን በመፈለግ እና ያለ ጭፍን ጥላቻ የሚንቀሳቀስ ግንኙነት ይገነባል” የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል። መልካም ሃምሳኛ ዓመት ክብረ በዓል!” ሲሉ ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ጋዜጣው ሃምሳኛ አመቱን ለማክበር በሮም ማታቶዮ ላ ሪፐብሊካ፡ የወደፊቱ ታሪክ የሚል ርዕስ ያለው ኤግዚቢሽን አዘጋጅቷል። እስከ መጋቢት 15 የሚቆየው የመልቲሚዲያ ኤግዚቢሽን በጋዜጣው ታሪክ ውስጥ ቁልፍ ጊዜያት የተነሱ ፎቶግራፎችን እና የጋዜጣ ገጾችን ያሳያል።

16 Jan 2026, 10:09