ፈልግ

እ.አ.አ በ2026 ዓ.ም በሚላን የሚካሄደው የኦሎፒክ ዝግጅት እ.አ.አ በ2026 ዓ.ም በሚላን የሚካሄደው የኦሎፒክ ዝግጅት  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት 'ኦሊምፒክ መቀባበልን፣ አንድነት እና ሰላምን ያበረታታ' ማለታቸው ተገለጸ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በሚላን በሚገኘው የቅዱስ ባቢላ ቤተክርስቲያን የአትሌቶች መስቀል በደረሰበት ወቅት ይህንን አጋጣሚ አስመልክተው ቅዱስነታቸው የቴሌግራም መልእክት ልከዋል፣ እዚያም የበረዶ ወቅት ኦሊምፒክ በሥፍራው ይከናወናል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

"ስፖርት፣ ወንድማማችነትን እና ሰላምን የሚያበረታታ ነው" ይህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ሐሙስ ምሽት ጥር 21/2018 ዓ.ም ላይ የቫቲካን ዋና ጸኃፊ በሆኑት ካርዲናል ፓሮሊን የተፈርሞ ይፋ የሆነው መልእክት ማዕከላዊ ጭብጥ ሐሳብ ሲሆን መልእክቱም ለሚላን ሊቀ ጳጳስ ማሪዮ ዴልፒኒ ልከዋል።

ወዳጅነት እና ወንድማማችነት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ዛሬ ምሽት በቅዱስ ባቢላ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከሚሳተፉት ሁሉ ጋር በመንፈሳዊነት እንደሚቀላቀሉ ተናግረዋል፣ በዚህ ክብረ በዓል ላይ በሊቀ ጳጳሱ መሪነት በሚካሄደው የሚላን-ኮርቲና ኦሊምፒክ እና የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች የአትሌቶች መስቀል፣ እ.አ.አ ከየካቲት 6 እስከ 22/2026 ዓ.ም በይፋ ወደ ከተማው አቀባበል ይደረግለታል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ "ይህ አስፈላጊ ክስተት የጓደኝነት እና የወንድማማችነት ስሜትን ሊቀሰቅስ፣ ስፖርት ለሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት አገልግሎት ያለውን ዋጋ ግንዛቤን ሊያጠናክር ይችላል" የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።

በሕዝቦችና በባህሎች መካከል ድልድዮችን መገንባት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ በመልእክታቸው በኦሎምፒክ የሚካሄደው “ጤናማ ውድድር” “በባህሎችና በሕዝቦች መካከል ድልድዮችን ለመገንባት፣ አቀባበል ለማድረግ፣ አንድነትን እና ሰላምን ለማስፈን” እንዲረዳ እንደሚጸልዩ ተናግረዋል።

በመስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ከሚሳተፉት መካከል በቫቲካን የባህልና የትምህርት ጉዳዮችን የሚመለከተው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት ዋና ጸኃፊ የሆኑት አቡነ ፖል ቲጌ እና የጣሊያን ጳጳሳት ኮንፈረንስ (CEI) ምክትል ጸሐፊ እና የመዝናኛ፣ የቱሪዝም እና የስፖርት ብሔራዊ የሐዋርያዊ እንክብካቤ ቢሮ ጊዜያዊ ዳይሬክተር አባ ሚሼል ጂያኖላ ይገኙበታል።

30 Jan 2026, 15:25