ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ   (AFP or licensors)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ "ለክርስቲያኖች ሙሉ አንድነት ጸሎታችንን እናጠናክር" ማለታቸው ተገለጸ!

ለክርስቲያናዊ ሕብረት ለአንድ ሳምንት ያህል የሚደርገው የጸሎት ሳምንት በጥር 10/2018 ዓ.ም መጀመሩን ያስታወሱት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የጸሎት ሳምንት መጀመሩን በማስታወስ በክርስቲያኖች መካከል የሚታይ ሕብረት እንዲኖር አዲስ ጸሎት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በጥር 10/2018 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ካደረጉ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ እንደ ተናገሩት ከሆነ ዛሬ የሚጀምረው ለክርስቲያኖች ሕብረት የሚደርገው የጸሎት ሳምንት ከሁለት ምዕተ አመታት በፊት መጀመሩን ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል። ይህ ተነሳሽነት በሊቀ ጳጳስ ሊዮ 13ኛ “በጥብቅ ተበረታቷል” እና በትክክል ከአንድ መቶ ዓመታት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ለክርስቲያኖች አንድነት የሚደርገው የአንድ ሳምንት ጸሎት እንደበለፀገ ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የዘንድሮው ሳምንት ጭብጥ የተወሰደው ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች በጻፈው መልእክት “በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ" (ኤፌ 4፡4) በተሰኘው ላይ ያተኮረ ሲሆን ጸሎቶቹና አስተያየቶቹ የተዘጋጁት በአርሜኒያ ሐዋርያዊ ቤተክርስቲያን የሃይማኖቶች መካከል ግንኙነት መምሪያ በተቀናጀው የኢኩሜኒካል (የክርስቲያኖች ሕብረት) ቡድን ነው።

“ስለዚህ ሁሉም የካቶሊክ ማህበረሰቦች በእነዚህ ቀናት ለሁሉም ክርስቲያኖች ሙሉና የሚታይ አንድነት ጸሎታቸውን እንዲያጠናክሩ እጋብዛለሁ።” ብለዋል። ቅዱስ አባታችን አክለውም ይህ የኅብረት ጥሪ በሳምንቱ ውስጥ በሙሉ ከማሰላሰል ጋር አብሮ እንደሚሄድ እና እሁድ ጥር 17/2018 ዓ.ም ላይ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል። ይህ ለክርስቲያኖች ሕብረት የሚደርገው የጸሎት ሳምንት የክርስቲያኖች አሳዳጅ የነበረው ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ለውጥ ያመጣበት በዓል በሚከበርበት ወቅት እንደተለመደው የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከቅጥሩ ውጭ በሚገኘው የቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ ውስጥ በሮም የሰዓት አቆጣጠር በ5፡30 ሰዓት ላይ በሚደርግ ጸሎት እንደሚጠናቀቅ ተዘግቧል።

 

19 Jan 2026, 10:43