ፈልግ

2025.05.10 Incontro con i Cardinali - Aula del Sinodo

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የመጀመሪያውን ልዩ የካርዲናሎች ጉባኤ ማድረግ እንደሚጀምሩ ተገለጸ!

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከጥር ሰባት እስከ ጥር 8/2026 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ያህል የሚቆይ የብጹዕን ካርዲናሎች ጉባኤ በቫቲካን እንደሚከናወን የተገለጸ ሲሆን ጉባኤው በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ 4፡00 ሰዓት በቫቲካን በሚገኘው የሲኖድ አዳራሽ ይከፈታል። ሂደቱ በዝግ በር ይካሄዳል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

እንደ የጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሚቀጥለው ቀን፣ ጥር 8/2026 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ከካርዲናሎቹ ጋር በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚልካ ውስጥ መስዋዕተ ቅዳሴ እንደምያሳርጉ የሚጠበቅ ሲሆን በሮ የሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 9፡30 ላይ፣ የጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ተጀምሮ እስከ ምሽቱ 12፡45 ድረስ ጉባኤው እንደሚቀጥል ተገልጿል፣ ጉባኤው በዝግ በሲኖዶስ አዳራሽ ውስጥ ይከናወናል። በመጨረሻም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እና ካርዲናሎቹ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 3፡15 እስከ ምሽቱ 7፡00 ሰዓት እንደገና ይገናኛሉ፣ ከእዚያም ለሁለት ቀን በዝግ ሲከናወን የነበረው ጉባኤ እንደሚጠናቀቀ ተገልጿል።

07 Jan 2026, 11:26