ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በሮም ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው በካስተል ጋንዳልፎ ከጋዜጠኞች ጋር ቃለመጠይቅ ባደረጉበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በሮም ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው በካስተል ጋንዳልፎ ከጋዜጠኞች ጋር ቃለመጠይቅ ባደረጉበት ወቅት  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፡- ለሰላም ድምፃችንን እናሰማ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሮም ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው በካስቴል ጋንዶልፎ ለተገኙ ጋዜጠኞች አጭር መግለጫ በሰጡበት ወቅት በመካከለኛው ምስራቅ ስላለው ሁኔታ አስተያየት ሲሰጡ ሰዎች ለሰላም እንዲጸልዩ አሳስበዋል። እ.አ.አ በ2026 በሆሎኮስት መታሰቢያ ቀን (እ.አ.አ ጥር 27) ዓለም የአውሽዊትዝ-በርኬኑ በናዚ ወታደሮች ማጎሪያ ውስጥ ለብዙ አመታት በስቃይ ውስጥ የነበሩ እስረኞች ነፃ የወጡበትን 81ኛ ዓመት ተከብሮ ማለፉ የሚታወስ ሲሆን ይህንን መታሰቢያ ቀንን በማስታወስ “ሁሉንም ዓይነት ፀረ-ሴማዊነት እንዋጋ፣ ለሰላም በጣም መጸለይ እንዳለብን ብቻ ነው የሚሰማኝ" ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ቃላት የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ቃሎች ነበሩ፣ ልክ እንደተለመደው ማክሰኞ በካስቴል ጋንዶልፎ በሚገኘው መኖሪያቸው ወደ ቪላ ባርበሪኒ ሲሄዱ ለጣሊያን ቴሌቪዥን በሰጡት አጭር መግለጫ ላይ ነበር ቅዱስነታቸው ይህንን የተናገሩት።

በመካከለኛው ምስራቅ ስላለው ሁኔታ፣ በተለይም በፋርስ ባሕረ ሰላጤ የባሕር ቀጠና ውስጥ በአሜሪካ የአውሮፕላን ተሸካሚ አብርሃም ሊንከን መርከብ የሚመራ የባህር ኃይል ጥቃት ቡድን መኖሩን ጋዜጠኞች ሲጠይቁ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሰላም ጥሪያቸውን በድጋሚ አቅርበዋል።

“እኛ ትንንሽ ልጆች ድምፃችንን ከፍ አድርገን ሁልጊዜም ውይይት ማድረግ እንችላለን እንጂ ሁከትን አንፈልግም” ብለዋል፣ “በተለይም በዚህ የሾሃን መታሰቢያ ቀን” ሲሉ ቅዱስነታቸው የተናገሩ ሲሆን ዛሬ የሆሎኮስት መታሰቢያ ቀን በመሆኑ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ቀደም ብለው በX አካውንታቸው @Pontifex ላይ “ሁሉንም ዓይነት ፀረ-ሴማዊነት እንዋጋ” ሲሉ መልእክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል።

28 Jan 2026, 11:25