ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 'ካርዲናሎች፣ በእናንተ እተማመናለሁ" ማለታቸው ተገለጸ።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ከአራቱ ሀሳቦች መካከል ሁለት ጭብጦችን - ሲኖዶሳዊነት እና ሐዋርያዊ ተልዕኮ "በኢቫንጀሊ ጋውዲየም" ("ኢቫንጀሊ ጋውዲየም" (የወንጌል ደስታ) እ.አ.አ በሐምሌ 24/2013 ዓ.ም የታተመ እና በቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የተጻፈ ሐዋርያዊ ምክር ሲሆን የጵጵስና ሥልጣናቸው ዘመን ፕሮግራም ያዘለ ሰነድ ተደርጎ ይወሰዳል። ጽሑፉ እያንዳንዱ ክርስቲያን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለውን የግል ግንኙነት እንዲያድስ እና አዲስ የደስታ እና የሚስዮናዊ ወንጌል ምዕራፍ እንዲጀምር ይጋብዛል) ብርሃን እንዲከናወን በመምረጣቸው ካርዲናሎቹን አመስግነዋል፣ እንዲህም ብለዋል፡- “ለዚህ ምርጫ እናመሰግናለን፤ ሌሎቹ ጭብጦች አልተረሱም። አሁንም መፍታት የሚገባን በጣም ተጨባጭ፣ ልዩ ጉዳዮች አሉ” ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።
“በእናንተ ላይ መተማመን መቻል አስፈላጊ ሆኖ ይሰማኛል፡ ይህንን አገልጋይ ወደዚህ ተልዕኮ የጠራችሁ እናንተ ናችሁ። ስለዚህ፣ አብረን መሥራታችን፣ አብረን ማስተዋል፣ መንፈስ ከእኛ የሚጠይቀውን መፈለግ አስፈላጊ እንደሆነ አምናለሁ” ሲሉ አክለው ተናግረዋል። በቫቲካን በተከናወነው ልዩ የካርዲናሎች ሸንጎ የመጀመሪያ ቀን መደምደሚያ ላይ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ እንደገና በቦታው የተገኙትን 170 ካርዲናሎች ድጋፍ እና እርዳታ ጠይቋል።
"በኢቫንጀሊ ጋውዲየም" ብርሃን ሲኖዶሳዊነት እና ተልዕኮ የተሰኙት ጭብጦች የተመረጡት “በግልጽ አብላጫ ድምጽ” ሲሆን ይህም የአምልኮ ሥርዓቱን እና የሐዋርያዊ ሕገጋቱን የሚያከብር 'ኢቫንጀሊየም'ን ያካተተ ዝርዝር ነው።
ርዕሰ ሊቀ ጳጳሳት ሊዮ በቡድን ውይይቶች በቀጥታ አልተሳተፉም፣ ነገር ግን የጠረጴዛዎቹ ዘጠኝ ጸሐፊዎች - ከሮማ ኩሪያ ውጭ ካሉ ካርዲናሎች የተውጣጡ - ስራቸውን ባቀረቡበት እና ቢበዛ በሦስት ደቂቃዎች ውስጥ ሁለቱን ጭብጦች የመምረጥ ምክንያቶችን ባብራሩበት አጠቃላይ ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እንዳብራሩት፣ ከሮማ ኩሪያ አባላት ጋር መመካከር ቀላል ነው ሲሉ ተናግረዋል። የሮማ ኩሪያ በቫቲካን የቅድስት መንበር እና የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማዕከላዊ የአስተዳደር አካል ሲሆን እንደ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ፍርድ ቤት" ወይም ቢሮክራሲ ሆኖ ዓለም አቀፋዊውን ቤተክርስቲያን ለማስተዳደር ይረዳል። እንደ ብሔራዊ መንግሥት ካቢኔ ወይም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ሁሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱን በማስተማር፣ በመቀደስ እና በማስተዳደር ተግባራት የሚያግዙ የተለያዩ ጉባኤዎችን፣ ፍርድ ቤቶችን እና ቢሮዎችን ያቀፈ ነው።
“አንድ ጭብጥ ከሌላው ሊለይ አይችልም”
በስብሰባው መደምደሚያ ላይ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት - ካዳመጡ እና ማስታወሻ ከወሰዱ በኋላ - ካርዲናሎቹን “በዚህ የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜ ለተከናወኑት ስራዎች ሁሉ” እና በሁሉም ጠረጴዛዎች “በብዙ አብላጫ ድምጽ” ለተደረጉት ምርጫዎች በማመስገን በድጋሚ ተናገሩ። “አንድ ጭብጥ ከሌላው ሊለይ አይችልም” ሲሉ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።
“አብረን ልንመረምራቸው የምንችላቸው ብዙ ነገሮች አሉ” ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፣ “ነገር ግን ወደ ራሷ ብቻ የማትመለከት፣ ሚስዮናዊት፣ ወደፊት የምትመለከት፣ ወደ ሌሎች የምትመለከት ቤተክርስቲያን መሆን እንፈልጋለን” ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።
"ቤተክርስቲያን የመሆን ምክንያት ለካርዲናሎች፣ ለጳጳሳት ወይም ለካህናት ሲባል ብቻ አይደለም” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን ይልቁንም “ወንጌልን የማወጅ ነው ዋና ተግባሯ፣ በዚህ ምክንያት፣ ለሁለቱ ጭብጦች ምርጫ ምስጋናቸውን ገልጸዋል።
ሲኖዶስ እና ሲኖዶሳዊነት በዛሬው ዓለም ሚስዮናዊ ቤተክርስቲያን እንዴት መሆን እንደሚቻል ያለውን ፍላጎት ይገልጻሉ፣ 'ኢቫንጀሊ ጋውዲየም' ደግሞ ቤተክርስቲያን “ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ወንጌልን እንድታውጅ” ጥሪ ያቀርባል፣ “ይህ የእኛ ተልእኮ ነው” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተናግረዋል።
“ሌሎቹ ጭብጦች አልተረሱም” ሲሉ አክለዋል የተናገሩት ቅዱስነታቸው “አሁንም መፍታት ያለብን በጣም ተጨባጭ፣ ልዩ ጉዳዮች አሉ” ያሉ ሲሆን እንዲሁም እያንዳንዱ ካርዲናል ከእሱ ወይም ከሌሎች ጋር በመካሄድ ላይ ባለው “የውይይት እና የማስተዋል ሂደት” አካል ሆኖ ለመነጋገር “በእውነት ነፃነት ይሰማዋል” የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።
ጉዞው እንደ ውጤቱም አስፈላጊ ነው።
ጳጳሱ ባደረጉት አጭር ሰላምታ፣ ከጸሐፊዎቹ አንዱ የተናገሩትን ጠቅሰዋል፣ እሱም “ጉዞው በጠረጴዛው ላይ እንደተደረገው ሥራ መደምደሚያ አስፈላጊ ነበር” ብለዋል። ይህ የአንድነት ተሞክሮ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እንደተናገሩት፣ የሸንጎ ፍሬ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ ተሞክሮ “ለቤተክርስቲያኒቱ እና ለዓለም ምስክርነት” የሚያቀርብ ሲሆን “ለቤተክርስቲያኒቱ እና ለዓለም አንድ ላይ የመሆን ፍላጎት” ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ዛሬም ሆነ ነገ ለቤተክርስቲያን የሚያስፈልገውን ነገር አንድ ላይ ለመፈለግ “ለአንዳንዶቻችሁ፣ በጣም ረጅም” የጉዞ መስዋዕትነት እና ዋጋ የምያስከፍል መሆኑን መገንዘብ ነው ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የስብሰባው ጊዜ “በጣም አጭር” ነው፣ ነገር ግን “ለእኔም በጣም አስፈላጊ ጊዜ” ነው ያሉ ሲሆን እንደገና፣ አብሮ መሥራት፣ አብሮ ማስተዋል እና መንፈስ ቅዱስ ከቤተክርስቲያኒቱ የሚጠይቀውን መፈለግ አስፈላጊ መሆኑን በድጋሚ ገልጸዋል።
“በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ሕይወት አለ?”
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በማጠቃለያ ንግግራቸው፣ ቀደም ሲል በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ውስጥ ሰባሰገለ ሕጻኑን ኢየሱስን ለማያት የመጡበት እለት በሚከበርበት "የክርስቶስ መገለጥ" በዓል በተከናወነው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ከነበሩት መንፈሳዊ ትምህርቶች የተወሰዱትን ክፍሎች ያስታወሱ ሲሆን የኢዩበሊዩ ቅዱስ በር ከተዘጋ በኋላ በተለይም “እራሳችንን እንጠይቅ፡ በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ሕይወት አለ?” የሚለውን ጥያቄ ደግመው አንስተዋል።
“በዚህ እንዳለ እርግጠኛ ነኝ” ሲሉ ቅዱስነታቸው የተናገሩ ሲሆን “በእነዚህ ወራት - ከዚህ በፊት ስለ ቤተክርስቲያኗ ሕይወት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ውብ ተሞክሮዎች አጋጥመውኛል። ሆኖም ጥያቄው አሁንም አለ፡ በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ሕይወት አለ? ለሚወለደው ነገር ቦታ አለው? ወደ ጉዞው የሚመልሰንን አምላክ እንወዳለን እና እናውጃለን ወይ?” ብለን ጥያቄ ማንሳታችንን መቀጠል አለብን ብለዋል።
በእርግጥም ገና የሚጠበቅ ጉዞ አለ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት፣ “ሁሉም ነገር አስቀድሞ ተፈጽሟል፣ ተጠናቋል - ሁልጊዜ እንደምናደርገው ማድረጋችንን እንቀጥል” ከሚለው ሀሳብ ማንም ሊሸሽ አይችልም። ስለዚህ ይህ የካርዲናሎች ሸንጎ፣ ቤተክርስቲያኗን አንድ ላይ እንድትራመድ ይረዳል ሲሉ ተናግረዋል።
ከስብከታቸው ሌላ ምንባብ በማስታወስ እና ንጉሥ ሄሮድስን በመጥቀስ፣ የተናገሩት ቅዱስነታቸው “ፍርሃት ዕውር” ያደርጋል ወንጌል ግን “ነፃ ያወጣናል፣ ብልህ” ያደርገናል፣ ነገር ግን “ደፋር፣ አስተዋይ እና ፈጠራ ያለው” እና “ቀደም ሲል ከተወሰዱት የተለዩ መንገዶችን” ይከፍታል ብለዋል።
ርዕሰ ሊቀ ጳጳስ ሊዮ 14ኛ፣ የካርዲናሎች ሸንጎ “የቤተክርስቲያኗን አዲስነት በእውነት ከምንለማመድባቸው ብዙ አገላለጾች አንዱ” ነው። “መንፈስ ቅዱስ ሕያው ነው እና በመካከላችንም ይገኛል” ብለዋል። “በጀልባው ውስጥ አብረን መገኘታችን እንዴት ደስ ያሰኛል! ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።
