ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ የፔሩ ብጹዓን ጳጳሳትን በቫቲካን ተቀብለዋል ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ የፔሩ ብጹዓን ጳጳሳትን በቫቲካን ተቀብለዋል   (@Vatican Media)

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ የፔሩ ብጹዓን ጳጳሳት የሐዋርያትን ሕይወት እንዲኖሩ አሳሰቡ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ የፔሩ ብጹዓን ጳጳሳት በዛሬው ዓለም የወንጌል አገልግሎት ፈተናዎችን ሲጋፈጡ፥ ለአንድነት፣ ለወንጌል ታማኝነት እና ለሐዋርያዊ ቅርበት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንዲያድሱ በማሳሰብ፥ በአገሪቱ ውስጥ የቀሰሙትን ሐዋርያዊ ልምዳቸውን በማስታዎስ በልባቸው ውስጥ ለፔሩ ልዩ ቦታ እንዳያላት ተናግረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ቫቲካን የመጡ የፔሩ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳትን ተቀብለው ባስተላለፉት መልዕክት፥ የሐዋርያትን ሕይወት እንዲኖሩ አሳሰቡ

ቅዱስነታቸው ብጹዓን ጳጳሳቱ ወደ ቫቲካን ያደረጉትን መንፈሳዊ ንግደት ሰፋ አድርገው በመመልከት፥ የላቲን አሜሪካ ብጹዓን ጳጳሳት ጠባቂ የቅዱስ ቶሪቢዮ ደ ሞግሮቬዮ 300ኛ ዓመት መታሰቢያን አስታውሰው፥ “ብጹዓን ጳጳሳቱ ቅዱስ ቶሪቢዮ ደ ሞግሮቬዮ በእነዚያ አገራት ውስጥ የዘራቸው የወንጌል ዘር ፍሬዎች ናቸው” ሲሉ አስታውሰዋል።

የተዓማኒነት ልብ አንድነት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ለብጹዓን ጳጳሳቱ ባደረጉት ንግግር፥ አንድነትን እና ኅብረትን እንዲያሳድጉ በማለት ጠንካራ ጥሪ አቅርበው፥ “ዛሬ ስብከታችን ተዓማኒነት በሐዋርያዊ እረኞች ውስጥ እና እንዲሁም ከሕዝበ እግዚአብሔር ጋር ባላቸው ግንኙነት ውስጥ መለያየትን፣ የግል ምኞቶችን እና ማንኛውንም ዓይነት መገለልን በሚያሸንፍ እውነተኛ እና ከልብ በመነጨ ኅብረት መካከል የሚያልፍ ሊሆን ይገባል” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው የጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ እና የቅዱስ ቶሪቢዮን ምስክርነት በማስታወስ እንደተናገሩት፥ እውነተኛ ኅብረት መዋቅራዊ ብቻ ሳይሆን ጥልቅ መንፈሳዊ፣ በጋራ እምነት እና ተልዕኮ ላይ የተመሠረተ መሆኑን ጠቁመዋል።

ለወንጌል ያለ ታማኝነት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በፔሩ ያለች ቤተ ክርስቲያንን ያጋጠሟት ተግዳሮቶች በማስታወስ ሲናገሩ፣ በሙላት የሚሰበክ አዲስ የወንጌል ታማኝነት እንደሚያስፈልግ ጠቁመው፥ ቅዱስ ቶሪቢዮ የራሱን ቃል እንዳልሰበከ ነገር ግን በሚለውጥ ኃይሉ በመታመን ከእየሱስ ክርስቶስ የተቀበለውን ቃል መስበኩን በመግለጽ፥ “ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ክርስቲያናዊ ማንነቷን ሳታጣ ከባህል ጋር ለመወያየት የሚያስችል ግልጽ፣ ደፋር እና አስደሳች ዜናን ለማወጅ ተጠርታለች” ሲሉ አስረድተዋል።

ሐዋርያዊ ቅርበት እና ሚስዮናዊ ቁርጠኝነት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ስለ ሐዋርያዊ ቅርበት አስፈላጊነት ሲናገሩ፥ ብጹዓን ጳጳሳት አገልግሎታቸውን፥ ለወንጌል ሲሉ ለሁሉም ሰዎች ሁሉን ከሆኑት ሐዋርያት እና ከቅዱስ ጳውሎስ አገልግሎት ጋር እንዲያዛምዱ አሳስበዋል።

የሐዋርያትን ሕይወት መኖር ማለት በአደራ ወደ ተሰጡት ሁሉ ዘንድ መቅረብ፣ ለእነሱ ትኩረት መስጠት፣ ሕይወታቸውን እና መንገዳቸውን መካፈል ማለት ነው” ብለው፥ እጅግ ደካማ እና ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ማሰብ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ቅዱስነታቸው ከፔሩ ጋር ያላቸው የግል ትስስር

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በፔሩ የነበራቸውን የሐዋርያነት ሕይወት ልምድ አስታውሰው፥ አገሪቱ በልባቸው ውስጥ ልዩ ቦታ እንዳላት ገልጸው፥ ፔሩ ውስጥ ደስታን እና መከራን መካፈላቸውን፣ ከሕዝቡ እምነትን መማራቸውን እና በፈተናዎች መካከልም ቢሆን ተስፋ ማድረግ የምትችል ቤተ ክርስቲያን ጥንካሬን መለማመዳቸውን ተናግረዋል።

ለመላው የፔሩ ሕዝብ ቡራኬያቸውን ልክዋል

ር ዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ በንግግራቸው ማጠቃለያ፥ ለፔሩ ጳጳሳት፣ ካኅናት፣ ገዳማውያን እና ገዳማውያት እንዲሁም ለመላው የፔሩ ምእመናን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት በመለመን፥ ከፍተኛ ብርታት እና መጽናናት ለሚያስፈልጋቸው በሙሉ ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን አበርክተዋል።

31 Jan 2026, 16:15