ፈልግ

የአፍሪካዊያን ኢዩቤሊዩ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በተከበረበት ወቅት የአፍሪካዊያን ኢዩቤሊዩ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በተከበረበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ሊዮ 'በአፍሪካ ውስጥ ያለችው ቤተክርስቲያን ሕያው፣ ጠንካራ እና ተለዋዋጭ እውነታ ነች’ አሉ

ለመካከለኛው አፍሪካ ሪፖብሊክ ጳጳሳት በጻፉት መልእክት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በክልላቸው ውስጥ ያሉ ቄሳውስት የሚያጋጥሟቸውን ታላላቅ ፈተናዎች እንደምገነዘቡ የገለጹ ሲሆን እናም “ማህበረሰቡን የሚያዳክሙ ክፉ ነገሮችን” ማለትም ጎሰኝነትን፣ የጎሳ ግጭቶችን፣ ጦርነቶችን እና የቤተሰብ መከፋፈልን ጨምሮ “ወንጌል፣ እርቅን እና የልብ ሰላምን ይጠይቃል” በማለት አፅንዖት ሰጥተው ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

“እንደ ቄሳውስት፣ በአገልግሎታችሁ ውስጥ በተለይ በብርቱ የሚታዩ አጣዳፊ ጉዳዮች ያጋጥሟችኋል” በማለት በመልእክታቸው ያሰፈሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ይህንን አስተያየት የሰጡት በቫቲካን ዋና ጸኃፊ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን በኩል ተፈርሞ ለመካከለኛው አፍሪካ ጳጳሳት በጻፉት መልእክት ነው።

ካሜሩን፣ ጋቦን፣ ኢኳቶሪያል ጊኒን፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክን፣ የኮንጎ ሪፐብሊክን እና ቻድን የሚያካትተው የማዕከላዊ አፍሪካ ክልል የኤጲስቆጶሳት ኮንፈረንስ ማህበር (ACERAC) 13ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተላከው መልእክት በቻድ የሚገኙት የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልዑክ በሆኑት ሊቀ ጳጳስ ጁሴፔ ላተሬዛ በኩል መልእክቱ በስብሰባው መጀመሪያ ላይ ተነበዋል።

ከጥር 17 እስከ የካቲት 1/2018 ዓ.ም የሚካሄደው ስብሰባ “የቤተክርስቲያን ተግዳሮቶች፣ የእግዚአብሔር ቤተሰብ በማዕከላዊ አፍሪካ፥ 'ቤተ ክርስቲያን በአፍሪካ' የተሰኘው የድህረ-ሲኖዶሳዊ ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ ከተጻፈ ከሰላሳ አመታት በኋላ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል።

ካሜሩን፣ ጋቦን፣ ኢኳቶሪያል ጊኒን፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክን፣ የኮንጎ ሪፐብሊክን እና ቻድን የሚያካትተው የማዕከላዊ አፍሪካ ክልል የኤጲስቆጶሳት ኮንፈረንስ ማህበር (ACERAC) የቻድ የጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት ጳጳስ ማርቲን ዋይንጌ ባኒ የተላከው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መልእክት መንፈሳዊ ቅርበታቸውን በመግለጽ ጳጳሳቱን በየቀኑ በሐዋርያዊ እንክብካቤቸው ሥር በአደራ ለተሰጣቸው ማህበረሰቦች ለሚሰጡት አገልግሎት “ሙሉ እውቅና” እሰጣለሁ ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን አያቋርጡም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ “ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን አያቆሙም፣ ከካህናት፣ ከተባባሪዎች፣ ከዲያቆናት፣ ከወንድሞችና ከእህቶች ጋር በመሆን በሁሉም የቤተክርስቲያን ሕይወት ዘርፎች ደስታችሁን እና የክርስቶስ ምስክር እንደመሆናችሁ ኃላፊነታችሁን የሚጋሩትን ምዕመናን፣ መጸለይ እና ምስጋና ማቅረባቸውን አያቋርጡም" ሲሉ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን መልእክት አጋርተዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመደበኛ ስብሰባዎቻቸው የተደገፈውን ጥረታቸውን አድንቀዋል፤ እምነትን፣ ተስፋን እና ፍቅርን በክርስቲያኖች ልብ ውስጥ ለመጨመር፤ ከሌሎች የሃይማኖት ማህበረሰቦች እና ከሲቪል ባለስልጣናት ጋር ግንኙነት ለመፍጠር፤ ወንጌልን በባህል እና በማህበራዊ ህብረ ህዋስ ውስጥ ለማቅረብ፤ የሰውን ሕይወት ለመጠበቅ፤ ሰላምንና ፍትህን ለማስፈን፤ የግጭት ሰለባ ለሆኑ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች እንክብካቤ ለማድረግ፤ እና ፍጥረትን ለመንከባከብ፥ ለእነዚህ ሁሉ ተግባራት ቅዱስነታቸው ማስጋና አቅርበዋል። ለሁሉም ክፍት የሆነ የመገናኘት ባሕላቸው እና ወንድማማችነታቸው ለአንድ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን የጋራ ቁርጠኝነት ጥንካሬ እና ጉልበት እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

የአፍሪካ ቤተ ክርስቲያን

ርዕሰ ሊቀ ጳጳሱ በልዩ ሁኔታ እ.አ.አ በ2026 ዓ.ም ቤተክርስቲያኗ " Ecclesia in Africa" (የአፍሪካ ቤተ ክርስቲያን) የተሰኘው ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ የተጻፈበትን 31ኛ ዓመት ክብረ በዓልን እንደምታከብር አስታውሰዋል፤ ይህም “ጌታ በአፍሪካ ውስጥ ያሉትን ሕዝቦቹን ጎብኝቷል። በእርግጥም ይህች አህጉር ዛሬ የጊዜ ምልክቶች፣ ምቹ ጊዜ፣ ለአፍሪካ የመዳን ቀን ተብሎ ሊጠራ የሚችል ነገር እያሳለፈች ነው” ሲሉ ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አስፍረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ይህንን በአእምሯችን ይዘን  “በአፍሪካ ውስጥ ያለችው ቤተክርስቲያን በእርግጥ ሕያው፣ ጠንካራ እና ተለዋዋጭ እውነታ ናት” ሲሉ የተናገሩ ሲሆን  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ከሠላሳ አንድ ዓመታት በኋላ ቢሆን ሰነዱ ሙሉ በሙሉ ጠቃሚ እንደሆነ ተናግረዋል።

ወንጌልን ከዓለም ጋር አታላምዱ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በማገልገል ረገድ ዘወትር የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች አምነው ተቀብለው አንድ አስፈላጊ ቦታ መዕመናንን ማገልገል መሆኑን በመጥቀስ ተናግረዋል። “ይህ ማለት ወንጌልን ከዓለም ጋር ማስማማት ማለት አይደለም፤ ነገር ግን በእያንዳንዱ ባህል ውስጥ የማይጠፋውን ቃል፣ ሕይወት የሚሰጥ እና ለሰው ልጅ ህልውና የሚያገለግል ቃልን ለማወጅ ተስማሚ ቅርጾችን ማግኘት ማለት ነው” ሲሉ ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

“እንደ ጎሰኝነት፣ የጎሳ ግጭቶች፣ ጦርነቶች፣ የቤተሰብ መከፋፈል እና የመሳሰሉትን ማህበረሰቡን የሚያዳክሙ ክፉ ነገሮችን መጋፈጥ" ያስፈልጋል ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ "ወንጌል እርቅንና የልብ ሰላምን ይጠይቃል" ሲሉ አክለው በመልእክታቸው ገልጸዋል።

በቀውሶች የተንቀጠቀጠ

የቤተክርስቲያኒቱ የሲኖዶሳዊ ጉዞ ቄሳውስት በአደራ የተሰጣቸውን ሕዝቦች በማዳመጥ፣ በርኅራኄ እና በደግነት መንፈስ እንዲቀርቡ ጥሪ ሲያቀርብ፣ “በሀገራቸው እና በቤተክርስቲያኒቱ ሕይወት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ የሚጥሉ ብዙ ወጣቶችን ድምፅ እንድትሰሙ ይርዳችሁ” ሲሉ ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ማህበረሰቦች በስደተኞች እና በተፈናቀሉ ሰዎች ቀውስ እንደተናወጡ ይገኛሉ” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በመልእክታቸው ያሰፈሩ ሲሆን “ለእነሱ የሚያሰቃዩት ሰዎች ሁሉ ክርስቶስ መጽናኛውን ይስጣቸው" ብለዋል።

በመጨረሻም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሥራቸውን የወንጌላዊነት ኮከብ፣ የእናቶች ተንከባካቢ ለሆነችው ለድንግል ማርያም በአደራ በመስጠት ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን በሁሉም ላይ ይሆን ዘንድ ከተመኙ በኋላ ለእነሱም ሆነ በማዕከላዊ አፍሪካ ክልል ውስጥ በተለያዩ መንገዶች ቤተክርስቲያኑን ለሚያገለግሉ ሁሉ በጸሎት ከእናተ ጋር ነኝ ካሉ በኋላ መልእክታቸውን ደምድመዋል።

30 Jan 2026, 15:22