ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ሊዮ የካርዲናሎች ሸንጎ ካርዲናሎች በቤተክርስቲያን መንገድ ላይ የሚያሰላስሉበት ጊዜ ነው አሉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ እርሳቸው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በተከናወነው ልዩ የካርዲናሎች ሸንጎ ከተሰበሰቡት ካርዲናሎች ጋር መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው የተገለጸ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቤተክርስቲያኗን እንዲመሩ ለመርዳት ሲፈልጉ የእረኝነት አገልግሎት ተግዳሮቶቻቸውን እርስ በእርስ እንዲጋሩ ጋብዘው ነበር።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የካርዲናሎች ልዩ ሸንጎ ሁለተኛ ቀን መጀመሪያ ላይ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከዓለም ዙሪያ የመጡትን ካርዲናሎችን በድጋሚ ሰላምታ በማቀረብ የተከናወነውን መስዋዕተ ቅዳሴ መርተዋል። ረቡዕ ታኅሳስ 29/2018 ዓ.ም ውይይታቸውን የጀመሩት “ሲኖዶስ እና ሲኖዶሳዊነት” እና “ወንጌላዊነት እና በቤተክርስቲያን ውስጥ ተልዕኮ በ'ኢቫንጀሊ ጋውዲየም' ብርሃን” በሚሉት ጭብጦች ላይ እንደ ነበረም ተገልጿል።

በስብከታቸው፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የወንድማማችነት ፍቅር ጭብጥ በመያዝ፣ የካርዲናሎች ሸንጎ  ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ያላቸውን አንድነት የሚገልጽ የጸጋ ጊዜን እንደሚወክል ተናግረዋል። "ኮንሲስቶሪ"  የሚለው ቃል የመጣው “ማቆም” ከሚለው የላቲን ሥርወ ቃል መሆኑን ጠቅሰዋል፣ ካርዲናሎቹ በሮም ከእርሳቸው ጋር ለመሆን የተለመደውን ሥራቸውን እንዳቆሙ ተናግረዋል።

“ለተወሰነ ጊዜ እንቅስቃሴዎቻችንን አቁመን አስፈላጊ የሆኑ ቁርጠኝነቶችን እንኳን ትተናል፣ ስለዚህም ጌታ ለሕዝቡ ጥቅም ከእኛ የሚጠይቀውን ለመረዳት አንድ ላይ ተሰባስበናል” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ይህንን ለአለማችን “ትንቢታዊ ምልክት” ሲሉ ቆም ብለው መጸለይና አንድ ላይ ማዳመጥ በዓላማችን ላይ እንድናተኩር ስለሚያደርገን በጭፍን ተግባር እንዳንወድቅ ይረዳናል ብለዋል። ምንም አይነት የግል ወይም የጋራ አጀንዳዎችን ከማራመድ ይልቅ፣ ካርዲናሎቹ ክርስቶስ እቅዳቸውን የጠራ፣ የበራ እና የተለወጠ እንዲሆን በቅዱስ ቁርባን ብርሃን እንዲያስተውሉ ጋብዘዋል።

“የካርዲናሎች ሕብረት በብዙ ክህሎቶች እና በሚታወቁ ስጦታዎች የበለፀገ ቢሆንም፣ በመጀመሪያ ደረጃ የባለሙያዎች ቡድን እንዲሆን አልተጠራም፤ ነገር ግን እያንዳንዱ የሚያመጣው ስጦታ - ለጌታ የሚቀርበው እና በእርሱ የሚመለሰው - እንደ እግዚአብሔር ቸርነት - ትልቁን ፍሬ የሚያፈራበት የእምነት ማህበረሰብ እንዲሆን ተጠርቷል” ሲሉ ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ ካርዲናሎቹን የእግዚአብሔርን ሥላሴያዊ ፍቅር እንዲቀበሉ እና “የማቆም” ጊዜያቸውን ወደ “ታላቅ የፍቅር ተግባር - ለእግዚአብሔር፣ ለቤተክርስቲያን እና ለሁሉም የዓለም ወንዶችና ሴቶች” እንዲቀይሩ ጋብዛቸዋል።

በጸሎትና በዝምታ፣ እርስ በእርሳቸው ፊት ለፊት እንዲተያዩ፣ እርስ በእርሳቸው እንዲያዳምጡ እና ጌታ በሐዋርያዊ እንክብካቤያቸው በአደራ ለሰጣቸው ሁሉ ድምጽ እንዲሆኑ ተጠርተዋል ያሉ ሲሆን የካርዲናሎች ሸንጎ “በትህትና እና ለጋስ ልብ ለመኖር፣ እዚህ ያለነው በጸጋ እንደሆነ በመገንዘብ፣ እና ከያዝነው ነገር ውስጥ ያልተቀበልነው ምንም ነገር እንደሌለ፣ እንደ ስጦታ እና እንደ ተሰጥኦ ሊባክን ሳይሆን በጥበብ እና በድፍረት መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ” እንደሆነ ተናግሯል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ታላቁ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ሊዮ ክርስቲያኖች በተመሳሳይ መንፈስ እንዲተባበሩ የሰጡትን ማሳሰቢያ አስታውሰዋል፤ ይህም የተራቡት እንዲመገቡ፣ የተራቆቱ እንዲያለብሱ እና ማንም ሰው የሌሎችን ጥቅም እንዳይፈልግ ማበረታታት እና መሥራት ነው ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የቤተክርስቲያኗን “ባለብዙ ​​ገጽታ ውበት” አስታውሰዋል፣ የካርዲናሎች ሸንጎ  “በጸጋ እና በእምነት አንድነት” ይመሰከራል ብለዋል።

ካርዲናሎቹ ኢየሱስ በመከራ እና “በተስፋ መቁረጥ የህልውና ባዶነት” መካከል ለመትረፍ ለሚታገለው “እጅግ ብዙ ሕዝብ” የሰላም ፍላጎት ምላሽ እንዲሰጡ ጥሪውን እንዲቀበሉ አሳስበዋል። የካርዲናሎቹ አንድ ላይ የመሰብሰቢያ ዓላማ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ  እንደ ተናገሩት ከሆነ “መንፈሳዊ ፀጋ ልጆቹ እርዳታ በሚጠይቁበት ቦታ የምያቀርበውን አምስት ዳቦ እና ሁለት ዓሣ ለመቀበል እና ለማከፋፈል ነው” ብለዋል።

“በየደረጃው ለቤተክርስቲያኗ የምትሰጡት አገልግሎት ውስጥ የሚያቀርቡት ታላቅ እና እጅግ በጣም የግል እና ጥልቅ፣ ለእያንዳንዱ እና ለሁሉም ልዩ እና ውድ የሆነ ነገር ነው” ብለዋል። “እናም ከጴጥሮስ መንበር ተተኪ ጋር የሚጋሩት ኃላፊነት ከባድ እና ተግዳሮት ያለው ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

በመጨረሻም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ካርዲናሎቹን ለአገልግሎታቸው አመስግነው ሥራቸውን ለጌታ አደራ ሰጥተዋል።

 

09 Jan 2026, 13:02