ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ ክርስቶስ ለሰባሰገል የተገለጠበት በዓል ላይ የኢዮቤልዩ የተስፋ ዓመት ማጠናቀቃቸው ተገለጸ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የላቲን ሥርዓት በሚከተሉ ካቶሊካዊ ምዕመናን ዘንድ የተከበረውን የብርሃነ ልደቱ በዓል በመስዋዕተ ቅዳሴ መርተዋል። በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ውስጥ ለ5,800 ምዕመናን በመሩት የመስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢዮቤልዩ የተስፋ ዓመት በይፋ ያበቃበትን የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ቅዱስ በር ዘግተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በላቲን ሥርዓት ተከታዮች ዘንድ ማክሰኞ ታኅሳስ 28/2018 ዓ. ም. የተከበረውን የብርሃነ ጥምቀቱ በዓል ምክንያት በማድረግ፣ በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ውስጥ ለ5,800 ምዕመናን የቀረበውን መስዋዕተ ቅዳሴን መርተዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ በመስዋዕተ ቅዳሴው መጀመሪያ ላይ የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ቅዱስ በርን በይፋ የዘጉት ሲሆን፥ ይህ ምልክት ስፍር ቁጥር የሌላቸው የተስፋ ምዕመናን በባዚሊካው ደጃፍ የሚያልፉበት እና “የአዲሲቷ ኢየሩሳሌም በሮች ዘወትር ክፍት ናቸው” ብለው የገለጹት የመንፈሳዊ ጉዞ ወራት ማብቃትን የሚያመለክት እንደሆነ ታውቋል።

ሰብዓ ሰገልና ሄሮድስ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ ከማቴዎስ ወንጌል ተወስዶ በተነበበው ላይ በማስተንተን ባሰሙት ቃለ ምዕዳን፥ መጽሐፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር መገለጥ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን ውጥረት ፈጽሞ እንደማይደብቅ ጠቅሰው በሰብዓ ሰገል ደስታ እና በሄሮድስ ፍርሃት ላይ በማትኮር እንደተናገሩት፥  “መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ራሱን እንደሚገልጥ በሚናገርበት ጊዜ ሁሉ ደስታ እና ግርግር፣ ተቃውሞ እና ታዛዥነት፣ ፍርሃት እና ጉጉት የመሳሰሉ ተቃራኒ ምላሾች መኖራቸው አይደብቅም” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በመቀጠልም ይህ መለኮታዊ መገለጥ የተስፋ መጀመሪያን እንደሚያሳይ፥ የእግዚአብሔር መገለጥ ሰዎች ‘ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም’ እንዲሉ የሚያደርገውን የሐዘን ቸልተኝነት በማስቆም በምትኩ አዲስ ነገር የሚጀምረው “ተነሺ፣ አብሪ፤ ብርሃንሽ መጥቶአል እና የእግዚአብሔርም ክብር በአንቺ ላይ ወጥቷል” በሚለው ትንቢታዊ ተስፋ መፈጸሙን ተናግረዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ቀጥለውም፥ “በሰብዓ ሰገል ፍለጋ ተቸግራ መገለጥን የለመደች ከተማ ኢየሩሳሌም ናት” ሲሉ ተናግረው፥ ቅዱሳት መጻሕፍትን የሚያውቁ እና መልሶች እንዳሉት የሚያስቡ መኖራቸውን ተናግረው፥ ይህ “ጥያቄን የመጠየቅ እና ለማወቅ ያላቸውን ፍላጎት የማዳበር ችሎታቸውን ያጡ ይመስላል” ብለው፥ ከተማዋ በተስፋ ተገፋፍተው በሚመጡት ሰዎች እንደማትረጋጋ፥ በምትኩ የደስታ ምንጭ መሆን በሚገባው ስጋት ውስጥ መግባቱ እንደ ቤተ ክርስቲያን እኛንም ይፈታተናል” ብለዋል።

የዘንድሮ የብርሃነ ጥምቀቱ በዓል አንዳንድ ገጽታዎች

የዛሬዎቹ ወንዶች እና ሴቶች ፍለጋ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በኢዮቤልዩ ዓመት ላይ በማስተንተን ባሰሙት ቃለ ምዕዳን፥ ምእመናን የዛሬዎቹን ወንዶች እና ሴቶች ባላቸው መንፈሳዊ ፍለጋ ላይ እንዲያስቡ ጋብዘው፥ “እነዚህ ወንዶች እና ሴቶች እነማን እንደ ነበሩ እና ምን አነሳሳቸው?” ሲሉ ጠይቀው፥ እንደ ሰብዓ ሰገል በውስጣቸው ያለውን ጥያቄ እና ስሜት ይዘው ብዙዎች አሁንም ለመጓዝ እንደተገደዱ ይሰማቸዋል” ብለው፥ “ሰብዓ ሰገሎች ዛሬም አሉ” ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል። እነዚህም ከጉዞአቸው ጋር የተያያዙ አደጋዎችን በመቀበል ብዙውን ጊዜ አስደሳች እና አደገኛ በሆነ ዓለም ውስጥም ቢሆን ወጥተው መፈለግ እንዳለባቸው የሚሰማቸው ናቸው” ብለዋል።

ቅዱስ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን የሰውን ልጅ የመፈለግ እንቅስቃሴ እንዳትፈራ፣ ነገር ግን እንድታደንቅ እና ወደሚደግፈን እግዚአብሔር እንድታመራ ያሳስባል” ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። “እርሱ ዘወትር የሚያስታውሰን እንደ ብር እና ወርቅ ጣዖታት በእጃችን ውስጥ ጸንቶ የማይቆይ በመሆኑ ይልቁንም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በእቅፏ እንዳሳደገችው እና ጠቢባኑም እንደወደዱት ሕፃን ሕያው እና ሕይወት ሰጪ ነው” ብለዋል።

በዚህም ምክንያት ቅዱሳን ቦታዎች ሕይወትን ማስተላለፍ አለባቸው” ብለው፥ የኢዮቤልዩ የአምልኮ ቦታዎች የሕይወትን መዓዛን ማሰራጨት ሌላው ዓለም የጀመረው የማይረሳ ግንዛቤ ነው” ካሉ በኋላ  “በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ሕይወት አለ ወይ? አዲስ ነገር የሚወለድበት ሥፍራ አለ ወይ? ጉዞን እንድንጀምር የሚያደርገንን አምላክ እንወዳለን ወይ? ስለ እርሱ እናውጃለን ወይ?” ሲሉ ጠይቀዋል።

በተቃራኒው ኃይልን የማጣት ፍርሃት ለእግዚአብሔር እርምጃ የሚሰጠውን ምላሽ የሚያዛባ ሄሮድስ አለ” ያሉት ቅዱስነታቸው፥ ሄሮድስ ለዙፋኑ እንደሚፈራ እና ከቁጥጥሩ ውጪ እንደሆኑ በሚሰማቸው ነገሮች ላይ ይጨነቃል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል። “የወንጌል ደስታ ግን በተቃራኒው ነፃ ያወጣናል፣ አማኞችን ብልህ፣ ደፋር፣ አስተዋይ እና ዘዴኞች በማድርግ ቀደም ሲል ከተጓዙበት የተለዩ መንገዶችን ይከፍታል” ብለዋል።

በብርሃ ጥምቀቱ ልብ ውስጥ

በቃለ ምዕዳናቸው ውስጥ ብርሃነ ጥምቀቱን ያስታወሱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ ብርሃነ ጥምቀቱ

በገንዘብ ሊገዙት ወይም ሊቆጣጠሩት የማይችሉት ስጦታ እንደሆነ ገልጸው፥ “ሰብዓ ሰገል የሚያመልኩት ሕጻን በዋጋ ሊተመን የማይችል መልካም ሰው ነው” ብለዋል።

“የተስፋ ተጓዦች መሆን ድንቅ ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው፥ “አብረን ተጓዦች ሆነን መቀጠል ለእኛ ድንቅ ነገር ነው” ብለው፥ በመጨረሻም ቤተ ክርስቲያን የመታሰቢያ ሐውልት መሆንን ተቃውማ ቤት ሆና ከቀጠለች አሁንም የአዲስ ንጋት ትውልድ መሆን የምትችል፥ በኃያላን ሳይሆን ዘወትር የንጋት ኮከብ በሆነች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ድጋፍ በፍቅር ሥጋ በሆነው በእግዚአብሔር የምትመራ ናት” ሲሉ አስረድተዋል።

የኢዮቤልዩ ዓመት በይፋ የተገባደደበት የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ቅዱስ በር መዝጊያ ሥነ-ሥርዓት

 

06 Jan 2026, 16:26