ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሐዋርያዊ ሥልጣናቸውን የሚገልጽ አዲስ በትር ይዘው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሐዋርያዊ ሥልጣናቸውን የሚገልጽ አዲስ በትር ይዘው  (@Vatican Media)

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ አዲስ የሐዋርያዊ ሥልጣን በትር መያዛቸው ተገለጸ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ ከጥር 6 ጀምሮ ሐዋርያዊ የአገልግሎ ሥልጣንን የሚገልጽ አዲስ በትር መምረጣቸውን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የሥርዓተ አምልኮ ጽ/ቤት አስታውቋል። ይህም የቀደሙት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ከሚያደርጉት ጋር ተከታታይነት ያለው ሲሆን፥ የኢየሱስ ክርስቶስን የመስቀል ላይ ምስጢር የማወጅ ተልዕኮን ከትንሣኤው መገለጫ ጋር አንድ የሚያደርግ እንደሆነ ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ በላቲን ሥርዓት ተከታዮች ዘንድ ማክሰኞ ታኅሳስ 28/2018 ዓ. ም. የተከበረውን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰብዓ ሰገል የተገለጠበት መታሰቢያ እና የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ቅዱስ በር መዝጊያ ሥነ-ሥርዓት በተፈጸመበት ዕለት አዲስ የሐዋርያዊ ሥልጣን በትር መያዝ መጀመራቸው ተመልክቷል።

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የሥርዓተ አምልኮ ጽ/ቤት እንደገለጸው፥ የሐዋርያዊ ሥልጣን ምልክታቸው ከቀደሙት ምልክቶችች ጋር ቀጣይነት ባለው መልኩ የሚያገለግል፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የገለጸውን የፍቅር ምስጢር በትንሣኤው ታላቅነት የሚያሳይ እንደሆነ ታውቋል።

“የፋሲካው ምስጢር የሐዋርያዊ አዋጅ ማዕከል ነው” ያለው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የሥርዓተ አምልኮ ጽ/ቤቱ፥ የፋሲካ ምስጢር ለሰው ልጅ የተስፋ ምክንያት እንደሆነ ገልጾ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት ሞት በሰው ልጅ ላይ ምንም ሥልጣን የለውም” ሲል አስታውቋል።

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከአሁን በኋላ በሐዋርያዊ ሥልጣናቸው ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያሳዩት በሕማማቱ ሳይሆን ወደ አብ በማረግ በክብር አካሉ እንደሆነ፥ ከሞት እንደተነሳው ጌታ በመገለጥ፣ቁስሎቹን የድል ምልክቶች አድርጎ የሚያሳይ እና የሰውን ሥቃይ ሳያስወግድ ነገር ግን ወደ መለኮታዊ ሕይወት የሚለውጥ ነው” ሲል ጽሕፈት ቤቱ አስረድቷል።

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የሥርዓተ አምልኮ ጽ/ቤት በተጨማሪም፥ ሐዋርያዊ ምልክቱ እንደ ጳጳሳዊ ምልክት በሮም ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ምልክቶች መካከል ፈጽሞ ያልታየ መሆኑን አስታውቆ፥ ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የሐዋርያዊ ሥልጣን በትር ይጠቀሙ እንደ ነበር እና ይህም መንፈሳዊ ሥልጣናቸውን እና አስተዳደራቸውን የሚያመለክት እንደሆነ ታውቋል።

የሐዋርያዊ ሥልጣን በትር ቅርጽ በትክክል ባይገለጽም፥ በቀላል መስቀል የተገለጸ በትር ሊሆን እንደሚችል ታውቋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ይህንን ዓርማ የተቀበሉት ለሐዋርያዊ መሪነት ከተመረጡ በኋላ፣ በቅዱስ ዮሐንስ ዘላቴራን ባዚሊካ ውስጥ በያዙበት ወቅት እንደ ነበር ተገልጿል።

ነገር ግን የሐዋርያዊ ሥልጣን በትር አጠቃቀም በተወሰኑ አጋጣሚዎች ለምሳሌ በቅዱስ በር መከፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ በሮችን ሦስት ጊዜ በማንኳኳት ወይም ቤተ ክርስቲያናት በሚባርኩበት ጊዜ በሥነ ሥርዓቱ ላያ የተደነገጉ የላቲን እና የግሪክ ፊደላትን በመሬት ላይ ለመከተል እንደ ሆነ ታውቋል።

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ታህሳስ 8/1965 ዓ. ም. በተካሄደው ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ መዝጊያ ላይ፥ የተሰቀለውን ክርስቶስን ምስል የያዘ ከብር የተሠራ የሐዋርያዊ ሥልጣን በትር የተጠቀሙት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ጳውሎስ 6ኛ እንደ ነበሩ ይታወሳል።

የቅርጻ ቅርጽ ባለሙያው ሌሎ ስኮርዜሊ የሐዋርያዊ ሥልጣን በትራቸውን በዚህ መንገድ ለማዘጋጀት የሞከረው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳት ቅዱስ ጳዎሎስ 6ኛ ስማቸውን ለመቀበል የመረጡት የሐዋርያው ​​ጳውሎስን ጥሪ ማለትም የተሰቀለውን የክርስቶስ ምስክር እና ሰባኪ መሆናቸውን ለመግለጽ እንደሆነ ታውቋል (1ኛ ቆሮ 2፡2)።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ጳውሎስ 6ኛ ሐዋርያዊ በትራቸውን መጠቀም ያቆሙት ተተኪዎቻቸው ከዚያ በኋላ እንደሚያደርጉት ሁሉ ይህንን ሐዋርያዊ መስቀል በአምልኮ ሥርዓቶች ውስጥ በብዛት መጠቀም ከጀመሩበት ጊዜ እንደሆነ ታውቋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤነዲክቶስ 16ኛም ቀደም ሲል ብፁዕ ፒዮስ 9ኛ ይጠቀምበት በነበረው የወርቅ መስቀል ላይ የተገጠመ ሐዋርያዊ እረኝነት በትር በኋላም በመስቀሉ መሃል ላይ የፋሲካ በግ ምልክት እና የኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጻፈበት የሐዋርያዊ ሥልጣን የትንሣኤውን ምስጢር የሚወክል አድርገው የሰጡትን የእረኝነት በትር መጠቀምን መርጠዋል።

 

 

10 Jan 2026, 16:24