ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በቫቲካን ሥር በሚገኙ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ለሚሰሩት የቫቲካን ሰራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው ጋር በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በቫቲካን ሥር በሚገኙ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ለሚሰሩት የቫቲካን ሰራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው ጋር በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ   (@Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ትሕትና እና ቀናነት የቤተክርስቲያኗ ዘይቤ ይሁኑ ማለታቸው ተገልጸ!

በቫቲካን ሥር በሚገኙ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ለሚሰሩት የቫቲካን ሰራተኞች ልማዳዊ በሆነ መልኩ በእየአመቱ በሚከናወነው የገና በዓል ወቅት የ'እንኳን አደረሳችሁ' ሰላምታ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ መሳተፋቸው የተገለጸ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በዚህ የገና በዓል የኢየሱስ ልደት ትሕትና እና ቀናነትን እንዲማሩ፣ እንዲሁም ይህ የቤተክርስቲያኗ ዘይቤ እንዲሆን እንዲያረጋግጡ ጋብዘዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የቫቲካን ሰራተኞችን በዚህ የገና በዓል የኢየሱስ ልደት ትህትናን እና ቀናነትን እንዲማሩ እና “ይህ በሁሉም አገላለጾቿ የቤተክርስቲያኗ ዘይቤ እንዲሆን” እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ሰኞ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም የሮማ ኩሪያ፣ የቫቲካን ከተማ ግዛት ገዥ እና የሮም አገረ ስብከት ካህናት እና  ቤተሰቦቻቸው የገና ሰላምታ ለመለዋወጥ በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ውስጥ ለተሰበሰቡት ይህንን ጥሪ እና ግብዣ አቅርበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ለተደረገላቸው ሞቅ ያለ አቀባበል እና ለስራቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፣ ቫቲካንን “ታላቅ የቢሮዎች ስብስብ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ስብስብ” እንደሆነ እያወቁ መምጣታቸውን አስረድተዋል። “ቀስ በቀስ፣ በእግዚአብሔር እርዳታ፣ የተለያዩ የስራ ቦታዎችን በመጎብኘት ራሴን ማግኘት እንደምችል አስባለሁ” ብለዋል። “እባካችሁ በቤት ውስጥ ላሉ የምትወዷቸው ሰዎች ሰላምታዬን አስተላልፉ፤ በተለይም ለአረጋውያንና ለታመሙ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እየጸለዩላቸው እንደሆነ ንገሯቸው” ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

በዕለት ተዕለት ህይወታችሁ ለእግዚአብሔር ክብር ስጡ

በሰላምታ በታሪክ ሂደት ውስጥ ወደ ልደት ትዕይንቶች የተጨመሩትን እና የዕለት ተዕለት ሕይወትን የሚወክሉ የተለያዩ ምስሎችን እና ገጸ-ባህሪያት ላይ ቅዱስነታቸው አስተንትኖ በማድረግ የተናገሩ ሲሆን ለምሳሌ “አንጥረኛ፣ የእንግዳ ማረፊያ ቤት ባለቤት፣ የቤት እመቤት፣ የልብስ ማጠቢያ፣ የቢላ መሞረጃ . . . ወዘተ” ስለእነዚህ ጉዳዮች ቅዱስነታቸው ተናግሯል።

ምንም እንኳን እነዚህ ሙያዎች ከጥንት የመጡ ቢሆኑም - እና አንዳንዶቹ በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል - አሁንም በትውልድ ትዕይንቶች ውስጥ አስፈላጊ ትርጉም እንዳላቸው ጠቁሟል።

“ሁሉም እንቅስቃሴዎቻችን፣ የዕለት ተዕለት ሥራዎቻችን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ባለው የእግዚአብሔር ዕቅድ ውስጥ ሙሉ ትርጉማቸውን እንደሚያገኙ ያስታውሰናል” ብለዋል።

“በግርግም ውስጥ የተኛው ሕፃን ኢየሱስ ሁሉንም ነገር እና ሁሉንም ሰው ይባርካል። ገር እና ትሑት መገኘቱ የእግዚአብሔርን ርህራሄ በየቦታው ያሰራጫል” ብለዋል።

ማርያም፣ ዮሴፍ እና እረኞቹ በኢየሱስ ልደት ሲያደንቁ፣ ሌሎቹ ገጸ-ባህሪያት ግን ሥራቸውን እንደሚቀጥሉ አጉልቶ አሳይቷል። ከዚህ አስፈላጊ ክስተት የተለዩ ቢመስሉም፣ በእውነቱ ግን በቦታቸው በመቆየት እና ስራቸውን በመስራት እየተሳተፉ መሆኑን አብራርተዋል።

"ይህ በስራ ህይወታችን ውስጥም ለእኛ እውነት ሊሆን እንደሚችል ማሳሰብ እወዳለሁ፡ እያንዳንዳችን ተግባራችንን እንፈጽማለን እና በጥሩ ሁኔታ፣ ቁርጠኝነትን በማሳየት እግዚአብሔርን እናወድሳለን" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

"አንዳንድ ጊዜ በስራችን በጣም ስለተጠመድን ስለ ጌታ ወይም ስለ ቤተክርስቲያን አናስብም፣ ነገር ግን በትጋት መስራት፣ ምርጡን ለመስጠት መሞከር፣ እና እንዲሁም - ለእናንተ - ለቤተሰባችሁ፣ ለልጆቻችሁ - ፍቅር ለጌታ ክብር ​​ይሰጣል" ሲሉ ቅዱስነታቸው መናገራቸውም ተዘግቧል።

22 Dec 2025, 14:33