የሊቀ ጳጳስ ሊዮ 14ኛ የመጀመሪያ “የሰላም የገና በዓል” ጥሪ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
“የጌታ የገና በዓል የሰላም የገና በዓል ነው” በዚህ ጥቅስ፣ በታኅሳስ 12/2018 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ለሮማ ኩሪያ (የሮማ ኩሪያ (Roman Curia) የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዳደር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን የሚረዳ ማዕከላዊ አስተዳደር ወይም የጳጳሳት ቢሮክራሲ ሲሆን፣ እንደ የመንግሥት ሚኒስትሮችና ቢሮዎች (Dikasteries) ለአስተዳደር፣ ለሕግ አውጪ እና ለፍትህ ተግባራት የሚያገለግል ካቢኔ ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን፣ በላቲን ቃል "ፍርድ ቤት" ወይም "ስብሰባ" በሚለው ቃል ላይ የተመሠረተ ነው) ጋር የገና በዓል መዳረሻ ላይ በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ዋና ዋና ጭብጦች አንዱን እንደገና ያስታውሳሉ፣ ለዚህ በዓል የተዘጋጀ ካርድ በመስጠት የመጀመሪያውን የገና ሰላምታ አቅርበዋል።
በስጦታው ካርድ ላይ እንዲሰፍር የተመረጠው ጥቅስ የተወሰደው ሊዮ የሚለውን ስም የያዘው የመጀመሪያው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በታላቁ ቅዱስ ሊዮ ስብከት 26 ላይ የተመሰረተ ነው። ከካርዱ ጋር የተያያዘው የሽፋን ምስል እ.አ.አ በ1955 ዓ.ም ለጳጳሱ አፓርታማ በጣሊያናዊው አርቲስት አልቤርቶ ሳሊቴቲ (1892–1961) የፈጠረውን ሞዛይክ ወይም ሕብረ ቀለም ያሳያል።
የጳጳሱ የገና ካርድ
እ.አ.አ ታህሳስ 23/2015 በካስቴል ጋንዶልፎ በሚገኘው ቪላ ባርበሪኒ መግቢያ በር ላይ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ “ቢያንስ በአዳኙ የልደት በዓል ላይ አንድ የሰላም ቀን እንዲከበር” በጎ ፈቃድ ያላቸውን ሰዎችን ጠይቀው ነበር። ያ “ያለ ትጥቅ እና ትጥቅ የማስፈታት” ሰላም ለመጀመሪያ ጊዜ እ.አ.አ በግንቦት 8/2025 በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ለመጀመሪያ ጊዜ በቀረቡበት ወቅት የሰላም ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል፣ ይህም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡ ቡኋላ ብዙም ሳይቆይ የቀረበ ጥሪ ነበር።
የገና በዓላት
ስለዚህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እ.አ.አ በታኅሳስ 24/2025 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ የጌታን የልደት በዓል በእርሳቸው መሪነት በተከናወነ መስዋዕተ ቅዳሴ ማክበራቸው የሚታወስ ሲሆን ከደቡብ ኮሪያ፣ ከህንድ፣ ከሞዛምቢክ፣ ከፓራጓይ፣ ከፖላንድ እና ከዩክሬን የተውጣጡ አስር ልጆች አበባ ይዘው በባዚሊካ ወደሚገኘው የልደት ትዕይንት ሁደት ላይ ከጳጳሱ ጋር ተሳትፈዋል።
ከዚያም እ.አ.አ ታህሳስ 25/2025 በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ጥዋት ላይ የተካሄደውን መስዋዕተ ቅዳሴ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ማሳረጋቸው የሚታወስ ሲሆን የቀድሞዎቹ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛ ያላከበሩትን የገና ቀን ቅዳሴ እንደገና አቅርበዋል። ለመጨረሻ ጊዜ በአንድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጥዋት ላይ የተከናወነው እ.አ.አ በታህሳስ 25/1994 በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ነበር።
ከዚያ በመቀጠል እ.አ.አ በታህሳስ 25/2025 ዓ.ም እኩለ ቀን ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ልማዳዊ በሆነ መልኩ በታላላቅ መንፈሳዊ በዓላት እኩለ ቀን ላይ “ኡርቢ እና ኦርቢ” (ለከተማው 'ሮም እና ለዓለም) የተሰኘውን መንፈሳዊ ቡራኬያቸውን ከቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ሆነው ማድረጋቸው እና በዓለም ላይ ሰላም ይሰፍን ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
ከዚያም እ.አ.አ በታህሳስ 26/2025 ዓ.ም የቤተክርስቲያኗ የመጀመሪያው ሰማዕት የቅዱስ እስጢፋኖስ በዓል እየተከበረ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ መርተዋል፣ በእለቱ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ተንተርሰው ባደርጉት አስተንትኖ "ቅዱስ እስጢፋኖስ ሰማዕትነት ወደ ብርሃን መወለድ እንደሆነ ያስተምረናል" ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።
እ.አ.አ ረቡዕ፣ ታህሳስ 31/2025 ዓ.ም የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ አገራት ዘንድ የዓመቱ የመጨረሻ ቀን ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጠዋት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፣ በአዲሱ ዓመት ዋዜማ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የተከናወነው ከ50 ዓመታት በፊት እ.አ.አ በ1975 ዓ.ም ሲሆን በወቅቱ በነበሩት ርዕሰ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ጳውሎስ ስድስተኛ ነበር የተከናወነው።
በዚያው ቀን ከሰዓት በኋላ በሮም የሰዓት አቆጣጠር በ5፡00 ሰዓት ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የጵጵሳና ዘመናቸው የመጀመሪያው የሆነውን አሮጌው ዓመት በሰላም በመጠናቀቁ በላቲን ቋንቋ "ቴ ዲየም" (ቴ ዲየም ጥንታዊ የላቲን ክርስትና የምስጋናና የውዳሴ መዝሙር ሲሆን በባህላዊ መልኩ በ4ኛው ወይም በ5ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ የተመሰረተ ነው። ርዕሱ የመጣው ከመክፈቻ ቃላቱ "ቴ ዲየም ላውዳመስ" ሲሆን ትርጉሙም "አንተን፣ እግዚአብሔር ሆይ፣ እናመሰግንሃለን" ማለት ነው) የተሰኘውን ጸሎት በአዲሱ አመት ዋዜማ ላይ ያቀርባሉ።
የጥር ዝግጅቶች እና የኢዮቤልዩ መጨረሻ
እ.አ.አ በ2026 ዓ.ም የመጀመሪያ ቀን፣ የ"ማርያም የእግዚአብሔር እናት" ክብረ በዓል እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ 59ኛውን የዓለም የሰላም ቀን በማስመልከት የሚከናወነውን መስዋዕተ ቅዳሴ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚልካ ከረፋዱ 4 ሰዓት ላይ በመስዋዕተ ቅዳሴ ያከብራሉ። እኩለ ቀን ላይ፣ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመሆን ያከናውናሉ።
ከዚያም ማክሰኞ፣ እ.አ.አ ጥር 6/2026 ዓ.ም ፣ የጌታ የጥምቀት በዓል፣ በማስመልከት የሚከናወነውን መስዋዕተ ቅዳሴ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ከጥዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ቅዳሴውን ይመራሉ፣ ከዚያም እ.አ.አ የ2025 ዓ.ም የኢዮቤልዩ ማብቂያን የሚያመላክተውን የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚልካ ቅዱስ በር ይዘጋሉ።
በመጨረሻም፣ እሁድ እ.አ.አ ጥር 11/2026 ዓ.ም የጌታ ጥምቀት በዓል፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሲስቲን ጸሎት ቤት ውስጥ በማስዋዕተ ቅዳሴ ያከብራሉ እና በርካታ ልጆችን ያጠምቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
