ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የመጀመሪያውን የካርዲናሎች ሕብረት ምክር ቤት ስብሰባ ጠሩ! ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የመጀመሪያውን የካርዲናሎች ሕብረት ምክር ቤት ስብሰባ ጠሩ!   (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የመጀመሪያውን የካርዲናሎች ሕብረት ምክር ቤት ስብሰባ ጠሩ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የጵጵስና ዘመናቸው የመጀመሪያው የሆነውን የካርዲናልች ሕብረት ምክር ቤት ስብሰባ እንዲካሄድ መጥራቸው የተገለጸ ሲሆን ይህ ስብሰባ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከመጪው ጥር 7-8/2026 ይካሄዳል፤ ስብሰባው በርዕሰ ሊቀ ጳጳሱ ጸሎት፣ ድጋፍ እና ምክር እንደሚከፈት ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት ዝቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የቅድስት መንበር የፕሬስ ጽሕፈት ቤት የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የመጀመሪያውን የካርዲናሎች ሕብረት ምክር ቤት ስብሰባ ዝርዝር መረጃ ይፋ አድርጓል፤ ይህም እ.አ.አ ከጥር 7-8/2026 በቫቲካን ይካሄዳል።

“ስብሰባው ለሁለት ቀናት ይካሄዳል፤ በኅብረት እና በወንድማማችነት ጊዜያት እንዲሁም ለማሰላሰል፣ ሐሳብ ለመካፈል እና ለጸሎት በተሰጡ ጊዜያት” እንደሚከናወን ቅዳሜ ዕለት የወጣው መግለጫ ገልጿል።

ካርዲናሎቹ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ጋር አብረው ሲጸልዩ እና ሲያሰላስሉ፣ ስብሰባው ማስተዋልን ለማሳደግ እና “በዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን አስተዳደር ውስጥ ያላቸውን ከፍተኛ እና ከባድ ኃላፊነት በመወጣት ረገድ ለቅዱስ አባታችን ድጋፍ እና ምክር ለመጠየቅ” ይጥራል።

“የካርዲናሎች ምክት ቤት ስብሰባ በቤተክርስቲያኒቱ ሕይወትና ተልዕኮ አውድ ውስጥ የተቀመጠ ነው” ሲል መግለጫው ይገልጻል፣ “እናም በሮም ጳጳስና በካርዲናሎቹ መካከል ያለውን ኅብረት ለማጠናከር ያለመ ሲሆን እነዚህም ለአለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ጥቅም ሲባል በልዩ መንገድ እንዲተባበሩ ተጠርተዋል”።

የካርዲናሎች ምክር ቤት ስብሰባ ምንድን ነው?

የካርዲናሎች ሕብረት ምክር ቤት ስብሰባ የሚካሄደው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የቅዱስ ጴጥሮስ ባሲልካ ቅዱስ በርን በጥር እ.አ.አ 6/2026 ዓ.ም ከዘጉ በኋላ ሲሆን ይህም የጌታ የጥምቀት በዓል ላይ የሚከናወን ስብሰባ ነው።

ከላቲን “ኮንሲስቶሪ” “አብረን መቆም” ከሚለው ቃል የመጣ ኮንሲስቶሪ የካርዲናሎች ሕብረት (ምክር ቤት) መደበኛ ስብሰባ ነው።

እነዚህ ኮንሲስቶሪ በአብዛኛው ሥነ ሥርዓታዊ ሥነ ሥርዓት ያላቸው እና በሮም የሚኖሩ ካርዲናሎች የሚሳተፉባቸው ወይም ልዩ ሊሆኑ ይችላሉ።

በጥር ወር የተካሄደው እንደ ልዩ ኮንሲስቶሪዎች ያሉ በዓለም ዙሪያ ያሉ ካርዲናሎችን በሙሉ መጓዝ የሚችሉ እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የቤተክርስቲያኒቱን ሕይወት በሚነኩ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከመላው የክርዲናሎች ሕብረት ጋር እንዲመካከሩ ያስችላቸዋል።

 

22 Dec 2025, 10:12