ር.ሊ.ጳ ሊዮ በማይናማር የተኩስ አቁም እንዲደረግና ጦርነት ባለበት ቦታ ሰላም እንዲሰፍን ተማጽነዋል
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
በአለም የተልዕኮ እለተ ሰንበት ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ካሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ማብቂያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በዓለም ላይ ሰላም ይሰፍን ዘንድ ጸሎት አቅርበዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እ.አ.አ ከግንቦት ወር 2021 ዓ.ም ጀምሮ ግጭት በተቀሰቀሰበት ምያንማር የተኩስ አቁም እንዲደረግ ተማጽነዋል፣ ከደቡብ ምሥራቅ እስያ ሀገር የሚመጡ ዜናዎችን “አስጨናቂ” ናቸው ሲሉ ቅዱስነታቸው ስለሁኔታው ገለጸዋል።
በሰላማዊ ሰዎች እና በመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ በተፈፀመው የትጥቅ ግጭት እና የአየር ላይ ጥቃት በቁጭት በመግለጽ በአመፅና በችግር ለሚሰቃዩ ሁሉ ያላቸውን አጋርነት ቅዱስነታቸው ገልጿል።
"አፋጣኝ እና ውጤታማ የሆነ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ልባዊ ጥሪዬን አድሳለሁ" ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የጦር መሳሪያዎች ሁሉን አቀፍ እና ገንቢ በሆነ ውይይት ለሰላም ቦታ ይልቀቁ" ሲሉ ተናግረዋል።
ከዚያም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ለቅድስት ሀገር፣ ዩክሬን እና ሌሎች በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች ሰላም ይሰፍን ዘንድ ጸሎት ያደረጉ ሲሆን "እግዚአብሔር ለሁሉም መሪዎች ፍትሃዊ እና ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ጥበብ እና ጽናትን ይስጣቸው" ሲሉ ተማጽነዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የመልአከ ሰላም ጸሎት ከማድርገቸው በፊት ባደረጉት ንግግር በዓለም ተልዕኮ እለተ ሰንበት ክርስቲያኖችን የቤተክርስቲያኗን ሚስዮናዊ ተፈጥሮ እንዲቀበሉ ጋብዘዋል።
“ቤተክርስቲያኗ ሙሉ በሙሉ ሚስዮናዊ ናት፣ነገር ግን ዛሬ በተለይ ሁሉንም ነገር ትተው ወንጌልን ለማያውቁት የተጉትን አዳዲስ ወንድ እና ሴት ቅዱሳን አማላጅነት እንጸልያለን፣ በአሕዛብ መካከል የተስፋ ሚስዮናውያን ናቸው፣ ጌታ ይባርካቸው!" ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ሳምንታዊ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።
