ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ቅዱሳን በክርስቶስ ያለውን የእምነት ብርሃን ያቃጥላሉ ማለታቸው ተገለጸ!
የዚህ ዚግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ እሑድ ቤተ ክርስቲያን የዓለም ተልዕኮ ዕለተ ሰንበትን ስታከብር ሰባት ወንዶች እና ሴቶችን ወደ ሲመተ ቅድስና ክብር ከፍ እንዲሉ አድርገዋል።
በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በተካሄደው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እነዚህ ሰባት ብፁዓን በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቅዱሳን እንዲሆኑ አውጀዋል፣ ስማቸውም ቅዱስ ኢኛሱስ ሹኩራላህ ማሎዋያን (ከአርሜኒያ)፣ ቅዱስ ፒተር ትሮት (ፓፓዋ ኒው ጊኒ)፣ ቅድስት ቪንቼንሳ ማሪያ ፖሎኒ (ከጣሊያን፣ ቬሮና)፣ ቅድስት ሬዲሌስ ማርቲነዚ (በቬኑዙዌላ የቀርሜሎስ እምቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ማሕበር አባል)፣ ቅድስት ማርያ ቶሮንካቲ (ጣልያናዊት)፣ ቅዱስ ኦዜ ግሬጎሪዮስ ፍርናደዝ (ከካራካስ፣ ቬንዙዌላ) እና ቅዱስ ባርቶሎ ሉጎን (ጣሊያናዊ) እንደሆኑም ተዘግቧል።
ቅዱስ አባታችን በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት የሰው ልጅ ዳግም ሲመጣ በምድር ላይ እምነትን ያገኝ እንደሆነ ኢየሱስ ባቀረበው ጥያቄ ላይ አስተንትኖ ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን ጳጳሱ እንዳሉት የጌታ ጥያቄ እምነት በእግዚአብሔር እና በህዝቡ መካከል ያለው ውድ የፍቅር ማሰሪያ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።
"ዛሬ ሰባት የእምነት ምስክሮች በፊታችን አሉ፣ አዳዲሶቹ ቅዱሳን፣ በእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእምነት መብራት እንዲበራ ያደረጉ፣ በእርግጥም እነርሱ ራሳቸው የክርስቶስን ብርሃን ማስፋፋት የሚችሉ መብራቶች ሆኑ" ሲሉ የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የዓለማችን ታላላቅ "የቁሳቁስ፣ ባህላዊ፣ ሳይንሳዊ እና ጥበባዊ ሀብቶች" ከመጠን በታች የሆነ ዋጋ ሊነፈጋቸው አይገባም ማለት ተገቢ እንዳልሆነ የገለጹ ሲሆን ነገር ግን እውነተኛ ትርጉማቸው ያለ እምነት ድጋፍ ትርጉማቸው እንደጠፋ ተናግረዋል።
ጳጳሱ አክለውም፣ እምነት የሌለበት ዓለም፣ በልባቸው የመዳን ተስፋ ስለሌለ የሕይወት ፍላጎት በሌላቸው፣ አባት በሌላቸው ልጆች ይሞላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
በዚህ ምክንያት፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን የፍቅር ትስስር እንዲጸና እና ልባችን ማዳኑን እንዲቀበል ኢየሱስ ሁል ጊዜ እንድንጸልይ ጋብዘናል ያሉት ቅዱስነታቸው "መተንፈስ የሰውነትን ህይወት እንደሚደግፍ ሁሉ ጸሎትም የነፍስን ህይወት ይደግፋል" ብሏል። “በእርግጥ እምነት የሚገለጸው በጸሎት ነው፣ እና ትክክለኛው ጸሎት በእምነት ላይ ይኖራል" ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ እኛ ክርስቲያኖች ስንጸልይ ብዙ ጊዜ ሁለት ፈተናዎች ያጋጥሙናል፣ አንዱ ፈተና የክፋት አሳፋሪ ነገር እንዲያሸንፈን መፍቀድ እና እግዚአብሔር ለችግራችን ደንታ እንደሌለው እንድናስብ ማድረግ ነው። በሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ እኛ እውነታዊ አተረጓጎም ፍትሃዊ እርምጃ እንዲወስድ በመፈለግ ጸሎትን እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ልንመለከተው እንፈተናለን" ያሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ በመስቀል ላይ ባቀረበው ጸሎት ከሁለቱም ፈተናዎች ነፃ ያደርገናል፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይፈጸም ዘንድ ጠየቀ ሲሉ ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋ።
እግዚአብሔር በፈተና ውስጥ የት እንደሆነ ስናስብ፣ ሰዎች በሚሰቃዩበት ቦታ ሁሉ እግዚአብሔር እንዳለ በመገንዘብ ይህን ጥርጣሬ ወደ ጸሎት እንለውጠው ብሏል።
"በጥላቻ እና በጦርነት፣ በሥቃይ እና በዓመፅ 'ስንሰቀል' ክርስቶስ ቀድሞውኑ በመስቀል ላይ፣ ለእኛ እና ከእኛ ጋር ነው" ሲሉ ተናግሯል "እግዚአብሔርን የማያጽናናው ጩኸት የለም፥ ከእግዚአብሔር ልቡ የራቀ እንባ የለም" ሲሉ አክለው ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።
"ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?” (ሉቃስ 18፡8) ወደ ሚለው በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ማብቅያ ላይ ኢየሱስ ወዳነሳ ጥያቄ በመመለስ በምድር ላይ እምነት ቢያገኝ፣ ጳጳሱ ክርስቲያኖች እምነትን በሁሉም የሕይወት ዘርፍ እንዲቀበሉ ጋብዟቸዋል፣ ምክንያቱም እምነት ለፍትህ ያለንን ቁርጠኝነት እና የእግዚአብሔር ፍቅር ዓለምን ለማዳን ያለንን ፍላጎት ስለሚደግፍ ነው ሲሉ አፅኖት ሰጥተው ተናግረዋል።
በማጠቃለያውም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ሰባቱ አዳዲስ ቅዱሳን በቅድስና መንገድ ላይ እንድንራመድ የምያቀርቡልንን ጥሪ እንድናከብር እንዲረዱን በአዳዲስ ቅዱሳን አማልጅነት መጸለይ እንደምያስፈልግ በመግለጽ “በምድር ላይ ያለ እምነት የመንግሥተ ሰማያትን ተስፋ ያጸናል” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን አጠናቀዋል።
