ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 15ኛ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 15ኛ  (@Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 'በላዳቶ ሲ' ንቅናቄ ኮንፈረንስ ላይ ንግግር እንደምያደርጉ ተገለጸ!

የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በላቲን ቋንቋ "ላውዳቶ ሲ" (ውዳሴ ለአንተ ይሁን) በሚል አርዕስት የጋራ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን ስለመንከባከብ (የአየር ንብረት ለውጥን ስለመዋጋት) በማስመልከት የዛሬ ዐስር አመት ገደማ ጳጳሳዊ መልእክት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። ይህ ጳጳሳዊ መልእክት ይፋ የሆነበት 10ኛው አመት በመጪው መስከረም 21/2018 ዓ.ም እንደሚከበር የተገለጸ ሲሆን በዚህ ዝግጅት ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ “የአየር ንብረት ፍትሕ ተስፋን ማሳደግ” በተሰኘው ዓለም አቀፍ ዝግጅት ላይ ከ400 በላይ የሃይማኖት መሪዎች፣ የአየር ንብረት ባለሙያዎች፣ እና ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ የሲቪል ማህበረሰብ እና ተቋማት ተወካዮች ጋር በሚገናኙበት ወቅት ንግግር እንደምያደርጉ ይጠበቃል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በካስቴል ጋንዶልፎ፣ በፎኮላር ንቅናቄ በሚመራው “ቼንትሮ ማሪያፖሊ” በተሰኘው ስፍራ በላውዳቶ ሲ ንቅናቄ ከተለያዩ የቤተ ክህነት እና የተቋማት አጋሮች ጋር በመተባበር “የአየር ንብረት ፍትሕን ተስፋን ማሳደግ” በሚል ርዕስ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ረቡዕ መስከረም 21/2018 ዓ.ም ይጀመራል።

በጋዜጣዊ መግለጫው መሠረት፣ እስከ መስከረም 25/2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆየው ጉባኤ ከ400 በላይ የሃይማኖት መሪዎችን፣ የአየር ንብረት ባለሙያዎችን እና የሲቪል ማህበረሰብ እና ተቋማት ተወካዮችን በማሰባሰብ ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ አንጻር ሥነ-ምህዳራዊ ለውጥን ተግባራዊ ለማድረግ ቀጣይ እርምጃዎችን የምያሳይ ወይም የሚጠቁም ጉባኤ እንደ ሚሆን ከአሁን ተስፋ ተጥሎበታል።

ረቡዕ መስከረም 21/2018 ዓ.ም ከሰአት በኋላ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ "የተስፋ በዓል" በተሰኘው ስብሰባ ላይ በመሳተፍ ንግግር እንደምይደርጉ ይጠበቃል።

ዝግጅቱ የብራዚል የአካባቢ እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር ማሪና ሲልቫ እና የቀድሞ የካሊፎርኒያ ገዥ አርኖልድ ሽዋርዜንገር ለፈጠራ ጥበቃ በሚደረጉ ጅምሮች ውስጥ የተሳተፉትን ጨምሮ የተለያዩ ምስክርነቶችን ያቀርባል።

ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ ንግግር በኋላ፣ የጋራ ቁርጠኝነት ምሳሌያዊ እና መንፈሳዊ ጊዜ ይኖራል፣ በመቀጠልም በርዕሰ ሊቀ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ እና በጉባኤ ተሳታፊዎች ቡድን መካከል የሚደረግ ስብሰባ የሚከናወን ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት፣ የስራ ክፍለ ጊዜዎች፣ በጠረጴዛ ዙሪያ የሚደረጉ ስብሰባዎች እና መንፈሳዊ ዝግጅቶች መርሐግብር ተይዞላቸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በካስቴል ጋንዶልፎ በሚገኘው በላቲን ቋንቋ 'ላውዳቶ ሲ' (ወዳሴ ለአንተ ይሁን) መንደር በቅርቡ ተገኝተው ለፍጥረት እንክብካቤ ይደረግ ዘንድ ለማሳሰብ የተደርገውን የመጀመሪያውን መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት ክርስቲያኖች ለዓለማችን እና ለፍጥረት ሁሉ ሰላም እና እርቅ ለማምጣት የተሰጣቸውን ተልእኮ እንዲወጡ ማሳሰባቸው ይታወሳል፣ ተፈጥሮን ለመንከባከብ ሥነ ምህዳራዊ ቀውስ ላይ ማሰላሰል ይጠይቃል ሲሉ አክሎ መናገራቸውን መዘገባችንም ይታወሳል። 

26 Sep 2025, 15:05