የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጤና ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣቱ ተገለጸ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ማክሰኞ እለት መጋቢት 02/2017 ዓ.ም ምሽቱን በተረጋጋ ሁኔታ ማሳለፋቸውን የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽህፈት ቤት ረቡዕ ዕለት የገለጸ ሲሆን የጳጳሱ ዶክተሮች በሆስፒታል ውስጥ ቅዱስነታቸው ተጨማሪ ጊዜ እንደምያስፈልጋቸው እና የጤናቸው ሁኔታ በጣም አስጊ እንዳልሆነ ገልጿል።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሮብ ማለዳ ላይ መጋቢት 03/2017 ዓ.ም በቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት ታትሞ የወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ምሽቱን በመልካም ሁኔታ ማሳለፋቸውን ገልጿል።
ማክሰኞ ማምሻውን የፕሬስ ጽ/ቤት የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን ውሎ አስመልክቶ ወቅታዊ መረጃ አቅርቧል፣ በቫቲካን በአሁኑ ወቅት እየተደረገ የሚገኘውን ሱባኤ ከጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ ጋር በቪዲዮ አገናኝተው በመከታተል፣ በፀሎት፣ በክፍላቸው ውስጥ ማሳለፋቸውን የገለጸው መግለጫው፣ በጸሎት ቤት ውስጥ ቅዱስ ቁርባን የተቀበሉ መሆናቸውን በመጥቀስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቀኑን ሙሉ የተለመደውን ከፍተኛ-ፍሰት ኦክሲጅን ሕክምናን ማድረጋቸውን ቀጥለዋል ሲል አክሎ መግለጫው አስታውቋል።
የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጤና ሁኔታ የተረጋጋ ቢሆንም ሐኪሞች በዐውደ-ጽሑፍ ውስጥ ትንሽ መሻሻሎችን እንዳሳዩ በማረጋገጥ ሁኔታቸው ግን ውስብስብ እንደ ሆነም ገልጿል።
ቅዱስነታቸው በብሮንካይተስ በሽታ በመያዛቸው ምክንያት ከየካቲት 07/2017 ዓ.ም ጀምሮ በሮም ጂሜሊ ሆስፒታል ውስጥ ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ይታወቃል።
የጤና ሁኔታቸው በጣም አስጊ ባይሆንም ነገር ግን ዶክተሮቹ እንዳሉት ከሆነ ቅዱስነታቸው በሆስፒታል ውስጥ ተጨማሪ ጊዜ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።