ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሆስፒታል ውስጥ ጥሩ ምሽት ማሳለፋቸው ተገለጸ!
የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት አርብ ማለዳ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ “ጳጳሱ ምሽቱን በመልካም እረፍት አሳልፈዋል" ሲል አስረድቷል።
ሐሙስ ዕለት፣ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራችስኮስ የጤና ሁኔታ ምንም ዓይነት "የመተንፈስ ችግር" ሳይታይበት የተረጋጋ ሆኖ አልፏል ሲል የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት የገለጸ ሲሆን "የጤና ሁኔታቸው የተረጋጋ ከሆነ ቀጣዩ የህክምና ገለጻ ቅዳሜ ይወጣል" ሲል አክሎ ገልጿል። ነገር ግን የፕሬስ ጽ/ቤቱ ስለ ቅዱስ አባታችን አጫጭር መረጃዎችን መስጠቱን ይቀጥላል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የካቲት 7/2017 ዓ.ም ሆስፒታል ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ በሁለትዮሽ የሳንባ ምች በሽታ በመጠቃታቸው የተነሳ በሮማ ከተማ በሚገኘው የጂሜሊ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ይታወቃል።
የእርሳቸው የሁለትዮሽ የሳንባ ምች በሕክምና ውስጥ የዚህ ዓይነቱ ሁኔታ መደበኛውን ዝግመተ ለውጥ ይከተላል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከታዘዙት የሕክምና ዘዴዎች ጋር በንቃት ይተባበራሉ፣ ስሜታቸውም መልካም ነው።
የጳጳሱ ዶክተሮች ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ ቀውሶች አለመኖራቸውን ያብራራሉ፣ ነገር ግን ለተጨማሪ ግምገማዎች ጊዜ ያስፈልጋል። የጤና ሁኔታቸው ሁኔታ ውስብስብ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ቢገኝም የተረጋጋ ሆኖ ይቆያል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ 21 ቀናት ያህል በሆስፒታል ውስጥ አሳልፈዋል።