ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን ከአልባኒያ የሙስሊም ቤክታሺ አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን ከአልባኒያ የሙስሊም ቤክታሺ አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት   (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት፡ ‘የሰላም ድልድዮችን ለመገንባት የሃይማኖት ተቋማት ተባብረው መሥራት አለባቸው’

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን ከአልባኒያ የሙስሊም ቤክታሺ ተቋም ልዑካን ቡድን ጋር ተገናኝተው በሀይማኖት ተቋማት መካከል የሚደረጉ ውይይቶች በህዝቦች መካከል ሰላማዊ አብሮ መኖርን ለመፍጠር ያለውን ወሳኝ ሚና አጉልተው ተናግረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሐሙስ እለት ጥር 07/2017 ዓ.ም  በሃይማኖቶች መካከል የሚደረግ ውይይት እና ትብብር ከመቼውም ጊዜ በላይ በግጭት እና በመከፋፈል በተወጠረው ዓለም ውስጥ አስፈላጊ መሆናቸውን ገልፀው ነበር።

ለበለጠ ወንድማማች ዓለም ለውይይት የጋራ ቁርጠኝነት

“የሀይማኖት ተቋማት መሪዎች በመከባበር መንፈስ ተሰባስበው በውይይት ፣በመግባባት እና በመተባበር የመገናኘት ባህልን ለማዳበር በሚተጉበት ጊዜ ፣የተሻለ እና ፍትሃዊ ዓለም የመፍጠር ተስፋችን ይታደሳል እና ይረጋገጣል” ብለዋል ቅዱስነታቸው በቫቲካን ከአልባኒያ የቤክታሺ የሙስሊም ተቋም ልዑካን ጋር በተገናኙበት ወቅት።

ቤክታሺስ በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አናቶሊያ በዘመናዊው ቱርኪ የተፈጠረ እና በኦቶማን ኢምፓየር ውስጥ ተስፋፍቶ እስከ አልባኒያ እና የአልባኒያ ህዝቦች በኮሶቮ፣ መቄዶኒያ እና ሞንቴኔግሮ ውስጥ የተስፋፋ ታዋቂ የሙስሊም ሱፊ ስርዓት ነው።

ስርዓቱ በፍቅር፣ በመቻቻል እና በመንፈሳዊ እውቀት ላይ በማተኮር ታዋቂ ሲሆን ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና ከቅድስት መንበር ጋር ሃይማኖታዊ ውይይቶችን በምያመቻቸው ጽኃፈት ቤት በኩል ወዳጃዊ ግንኙነቶችን እያከናወነ ይገኛል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እነዚህን ግንኙነቶች እንደ “በረከት” ገልፀው “በሕዝቦች መካከል ወንድማማችነትን እና ሰላማዊ አብሮ መኖርን በማገልገል ላይ” እንደሚሆኑ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በግሬስ ሃቺ ባባ ኤድሞንድ ብራሂማጅ ለተመራው የልዑካን ቡድን ንግግር ሲያደርጉ “በዓመፅ እና አለመግባባት አመክንዮ” በተበላሸ ዓለም ውስጥ የሃይማኖት ተቋማት በምትኩ “የግንኙነት፣ የጓደኝነት እና አብሮ የመሥራት መሠረታዊ እሴቶችን በግልፅ እንድንቀበል ይረዳናል" ብለዋል። የጋራ ጥቅምን ለማስከበር የሚደረግ ትብብር” እሱም “ለጋራ ሰብአዊነታችን ውስጣዊነት” አስፈላጊ ነው ብለዋል ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ በ1993 ዓ.ም በባልካን አገሮች ሰላም ይሰፍን ዘንድ የተደረገውን የሰላም ጸሎት፣ በቀድሞው ዩጎዝላቪያ ጦርነት ወቅት እና በ2011 ዓ.ም በጣሊያን አዚዚ የተካሄደውን የሰላም የጸሎት ቀንን ጨምሮ በበርካታሺ ማህበረሰብ እና ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን መካከል የወንድማማችነት ግንኙነት ያደረጉባቸውን በርካታ አጋጣሚዎች በአመስጋኝነት አስታውሰዋል። ከሌሎች ሙስሊሞች፣ ክርስቲያኖች እና ከአልባኒያ አማኞች ሁሉ ጋር በአገራቸው ብቻ ሳይሆን “የእርቅና የጋራ መበልጸግ ድልድይ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። ግን ደግሞ በምስራቅ እና በምዕራብ መካከል የሰላም ድልድይ ሆነን ማገልገል ይኖርብናል" ብለዋል።

"የቤክታሺ ማህበረሰብ ከሌሎች ሙስሊሞች፣ ክርስቲያኖች እና ከአልባኒያ አማኞች ሁሉ ጋር በአገራችሁ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በምስራቅ እና በምእራብ መካከልም የእርቅ እና የጋራ መበልጸግ ድልድይ ሆነው ሊያገለግሉ እንደሚችሉ እርግጠኛ ነኝ" ብለዋል።

የወደፊት ሰላምን ለመገንባት የሃይማኖቶች ውይይት ልዩ ሚና

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በማጠቃለያው ላይ እንዳሉት፣ አሁን ያሉ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ ሃይማኖታዊ ውይይት “የዓለም ሕዝቦች በተለይም ወጣቶች ከልብ የሚመኙትን የወደፊት የእርቅ፣ የፍትህ እና የሰላም ዕድል በመገንባት ረገድ ልዩ ሚና እንዳለው” አረጋግጠዋል።

17 January 2025, 14:16