ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ሁሉንም ትንንሽ ልጆች መጠበቅ አለብን፣ በደልን ፈጽሞ መታገስ የለብንም አሉ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
በእለቱ የተነበበው የእግዚአብሔር ቃል
በዚያች ሰዓት ደቀመዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው፥ በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ነው? ብለው ጠየቁት። ሕፃን ልጅ ጠርቶ በመካከላቸው አቆመው፤ እንዲህም አለ “እውነት እላችኋለሁ፥ ካልተመለሳችሁና እንደ ሕፃናት ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም (...) በእኔ ከሚያምኑ ከእነዚህ ታናናሾች አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ፥ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር ቢሰጥም ይሻለዋል (ማቴ 18፡1-3፣6)።
ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ እህቶቼ እና ሕጻናት እንደምን አረፈዳችሁ!
ዛሬ ደግሞ ስለ ልጆች እንነጋገራለን። ባለፈው ሳምንት ትኩረታችንን ያደረግነው፣ ኢየሱስ በሥራው፣ ሕፃናትን መጠበቅ፣ መቀበል እና መውደድ አስፈላጊ መሆኑን በተደጋጋሚ ተናግሯል።
ሕሊናን ማንቃት፣
ሆኖም ዛሬም በዓለም ላይ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሕፃናት ምንም እንኳን ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሰዎች የሚሰሩትን የግዴታ ሥራዎች ለመወጣት ዝቅተኛው የሆነ ዕድሜ ቢኖራቸውም፣ ለመሥራት ይገደዳሉ፣ ብዙዎቹ በተለይ ለአደገኛ ሥራ ይጋለጣሉ፣ ለሴተኛ አዳሪነት ወይም ለብልግና ምስሎችና ሥዕሎች፣ ለግዳጅ ጋብቻ ባሪያ የሆኑ ወንድና ሴት ልጆችን ማሰብ እንችላለን። በማህበረሰባችን ውስጥ፣ በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ህጻናት የሚንገላቱባቸው እና የሚጎዱባቸው ብዙ መንገዶች አሉ። በልጆች ላይ የሚደርስ ጥቃት ምንም ይሁን ምን በጣም አጸያፊ እና ክፉ የሆነ ድርጊት ነው። በቀላሉ በህብረተሰቡ ላይ መጥፎ እና ወንጀል የሚባል ድርጊት ቢቻ አይደለም፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት መጣስ ነው። አንድም ልጅ መበደል የለበትም። አንድ ጉዳይ እንኳን በጣም ብዙ ነው። ስለዚህ ሕሊናን ማንቃት፣ ከተበደሉ ሕፃናትና ወጣቶች ጋር መቀራረብንና እውነተኛ አብሮነትን መለማመድ፣ በተመሳሳይ ጊዜም በተረጋጋ መንፈስ የሚያድጉበትን ዕድልና አስተማማኝ ቦታ ለመስጠት በቁርጠኝነት በሚሠሩት መካከል መተማመንና መተሳሰር መፍጠር ያስፈልጋል።
የተንሰራፋው ድህነት፣ ለቤተሰቦች የማህበራዊ ድጋፍ መሳሪያዎች እጥረት፣ ከቅርብ አመታት ወዲህ እየጨመረ የመጣው ህዳግ፣ ከስራ አጥነት እና ከስራ እጦት ጋር በተያያዘ መልኩ ቤተሰብ ለልጆቻቸው ከፍተኛ ዋጋ እንዲከፍሉ የሚያደርጉ ምክንያቶች ናቸው። በታላላቅ ከተሞች ውስጥ ማህበራዊ ክፍፍል እና የሞራል ውድቀት "የሚነክሰው" በአደገኛ ዕፅ ንግድ እና በጣም የተለያየ ህገወጥ ተግባራት ላይ የተሰማሩ ልጆች አሉ። ከእነዚህ ልጆች ውስጥ ስንቶቹ መስዋዕት ሆነው ሲወድቁ አይተናል! አንዳንድ ጊዜ በሚያሳዝን ሁኔታ የእኩዮቻቸው “ገዳዮች” እንዲሆኑ ይገፋፋሉ፣ እንዲሁም ራሳቸውን፣ ክብራቸውንና ሰብአዊነታቸውን ይጎዳሉ። ነገር ግን፣ በመንገድ ላይ፣ በቁምስና አከባቢ፣ እና እነዚህ የጠፉ ህይወቶች በዓይናችን ፊት ሲቀርቡ፣ ብዙ ጊዜ ወደ ሌላ አቅጣጫ እንመለከታለን።
ማኅበራዊ ኢፍትሃዊነት
ሁለት ልጆች፣ ምናልባትም በአንድ ሰፈር ወይም አፓርታማ ውስጥ የሚኖሩ፣ ተቃራኒ የሆኑ መንገዶችን እና እጣ ፈንታቸውን እንዲከተሉ ያደረጋቸውን ማኅበራዊ ኢፍትሃዊነት ስናውቅ በጣም ያማል። ተቀባይነት የሌለው የሰው እና የማህበራዊ መለያየት፣ ማለም በሚችሉ እና መሸነፍ በሚገባቸው መካከል። ኢየሱስ ግን ሁላችንም ነፃ እና ደስተኛ እንድንሆን ይፈልጋል፣ ወንድና ሴትን ሁሉ እንደ ወንድና ሴት ልጁ አድርጎ የሚወዳቸው ከሆነ ሕፃናትን በፍጹም ልቡ ይወዳቸዋል። ለዚህም ነው ቆም ብለን ድምጽ የሌላቸውን፣ ያልተማሩትን መከራ እንድንሰማ የሚጠይቀን። ብዝበዛን መዋጋት በተለይም የህጻናት ብዝበዛን መዋጋት ለመላው ህብረተሰብ የተሻለ የወደፊት እድል መፍጠር ነው።
በሕጻናት የጉልበት ብዝበዛ ውስጥ ተሳታፊ አለመሆን
እናም ስለዚህ እራሳችንን እንጠይቅ፣ ምን ማድረግ እችላለሁ? በመጀመሪያ ደረጃ የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛን ለማጥፋት ከፈለግን በዚህ ውስጥ ተባባሪ መሆን እንደማንችል መገንዘብ አለብን። እናም ይህ መቼ ነው የሚከናወነው? ለምሳሌ የልጆች ጉልበት ብዝበዛን የሚያካትቱ ምርቶችን ስንገዛ። ከዚያ ምግብና ልብስ ጀርባ ትምህርት ቤት ከመሄድ ይልቅ የሚሠሩ የተበዘበዙ ልጆች እንዳሉ እያወቅን እንዴት መብላትና መልበስ እንችላለን? የምንገዛውን ነገር ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ተባባሪ ላለመሆን የመጀመሪያ ተግባር ነው። አንዳንዶች እንደ ግለሰብ ብዙ መሥራት አንችልም ይላሉ። እውነት ነው፣ ግን እያንዳንዳቸው ከብዙ ጠብታዎች ጋር በመሆን ባህር ሊሆኑ የሚችሉ ጠብታዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን፣ የቤተ ክርስቲያን ተቋማትን ጨምሮ ተቋማት፣ እና ኩባንያዎችም ኃላፊነታቸውን ማስታወስ አለባቸው፣ መዋዕለ ንዋያቸውን ወደ ህጻናት የጉልበት ሥራ ለማይጠቀሙ ወይም ወደማይፈቅዱ ኩባንያዎች በማዛወር ለውጥ ማምጣት ይችላሉ። ብዙ መንግስታት እና አለምአቀፍ ድርጅቶች የህጻናት ጉልበት ብዝበዛን የሚቃወሙ ህጎችን እና መመሪያዎችን አውጥተዋል፣ ነገር ግን ብዙ ማድረግ ይቻላል። ጋዜጠኞችም የድርሻቸውን እንዲወጡ አደራ እላለሁ፡ ስለችግሩ ግንዛቤ ማስጨበጥ እና መፍትሄ እንዲያገኝ ማገዝ ይችላሉ።
እናም ህጻናት ቶሎ አዋቂ እንዲሆኑ ሲገደዱ ሲያዩ ዓናቸውን ከእዚህ ጉዳይ ላይ የማይነቅሉ ሰዎችን ሁሉ አመሰግናለሁ። የኢየሱስን ቃል ሁል ጊዜ እናስታውስ፡- “ከእነዚህ ከሁሉ ከሚያንሱ ወንድሞቼ ለአንዱ ያደረጋችሁትን ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው” (ማቴ 25፡40) ይለናል። የካልካታዋ ቅድስት ቴሬዛ፣ በጌታ የወይን ቦታ ደስተኛ የሆነች፣ በጣም የተቸገሩ እና የተረሱ ልጃገረዶች እና ወንዶች ልጆች እናት ነበሩ። በዓይናቸው ርኅራኄና ትኩረት፣ የማይታዩትን ትንንሽ ልጆችን፣ ለፍትሕ መጓደል ልንተወው የማንችላቸውን በጣም ብዙ የዓለም ባሮች ለማየት ይጓዙ ነበረ። ምክንያቱም የደካሞች ደስታ የሁሉንም ሰላም ይገነባል። እናም ከእማሆይ ቴሬዛ ጋር፣ ለልጆቹ ድምጽ እንስጥ፡-
"የምጫወትበት አስተማማኝ ቦታ እጠይቃለሁ።
መውደድን ከሚያውቅ ሰው፣ ፈገግታ እጠይቃለሁ።
ተስፋ ለመሆን፣ የተሻለ አለም ለመገንባት
ልጅ የመሆን መብትን እጠይቃለሁ ።
እንደ ሰው የማደግ መብት እጠይቃለሁ።
በአንተ መታመን እችላለሁን?’ (የካልካታዋ ቅድስት ትሬዛ)