ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ በጥምቀት ለአዲስ ሕይወት ተወልደናል ማለታቸው ተገለጸ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ክቡራና እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከተታተሉን።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!
ዛሬ የምናከብረው የኢየሱስ የጥምቀት በዓል የራሳችንን ጥምቀት ጨምሮ ብዙ ነገሮችን እንድናስብ ያደርገናል። ኢየሱስ ለኃጢያት ስርየት ጥምቀትን ከሚቀበሉት ህዝብ ጋር ተቀላቅሏል። በዛሬው ስርዓተ አምልኮ ላይ የተነበበውን ቃል ለማስታወስ እወዳለሁ፡ ኢየሱስ "በባዶ ነፍስና በባዶ እግሩ" በዮሐንስ ሊጠመቅ ሄደ። ባዶ ነፍስ እና ባዶ እግር።
እናም ኢየሱስ ጥምቀትን ሲቀበል መንፈሱ እራሱን ይገለጣል፣ እናም የእግዚአብሔር ግልጸት ይከሰታል፣ በልጁ ላይ ፊቱን ገልጦ ድምፁን አሰምቷል፣ እርሱም “የምወደው ልጄ አንተ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል” (ሉቃስ 3፡22) ፊት/መልክ እና ድምጽ።
በመጀመሪያ ደረጃ ፊት/መልክ። በወልድ በኩል ራሱን አብ መሆኑን በመግለጥ፣ እግዚአብሔር ከሰው ልጆች ጋር ለመነጋገር እና ለመግባባት ልዩ ቦታን ዘረጋ። በተወደደው ልጁ ፊት አማካይነት።
በሁለተኛ ደረጃ ድምጽ። ፊት እና ድምጽ። "አንተ የምወድህ ልጄ ነህ" (ሉቃስ3፡ 22) ይህ ከኢየሱስ መገለጥ ጋር አብሮ የሚሄድ ሌላ ምልክት ነው።
ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ የዛሬው በዓል በኢየሱስ ሰብአዊነት የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ፊት እና ድምጽ እንድናሰላስል ያደርገናል። እናም ስለዚህ እራሳችንን እንጠይቅ፣ እንደወደድነው ይሰማናል ወይ? በእግዚአብሔር እንደምወደድ እና እንደምታጀብ ይሰማኛል ወይስ እግዚአብሔር ከእኔ የራቀ ይመስለኛል ወይ? በኢየሱስ፣በወንድሞቻችን እና በእህቶቻችን ውስጥ ፊቱን የማወቅ ችሎታ አለን ወይ? እናም ድምፁን መስማት ለምደናል?
አንድ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ-እያንዳንዳችሁ የጥምቀት ቀናችሁን ታስታውሳላችሁ ወይ? ይህ በጣም አስፈላጊ ነው! አስቡ፡ በምን ቀን ተጠመቅሁ? ካላስታወስን ደግሞ ቤት ስንደርስ ወላጆቻችንን ወይም አያቶቻችንን የተጠመቅንበትን ቀን እንጠይቅ። ይህንንም ቀን እንደ አዲስ ልደት፡ በእግዚአብሔር መንፈስ መወለድን እናክብረው። አትርሱ! ይህ የእኛ የቤት ሥራ ነው፡ የጥምቀት ቀናችንን ማወቅ ይኖርብናል።
ለድንግል ማርያም ረድኤትዋን እየለመንን እራሳችንን እንስጥ። እናም የጥምቀት ቀናችሁን አትርሱ!