ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ሆነው የሚያሳይ ምስል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ሆነው የሚያሳይ ምስል   (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከመሬት መንሸራተት በኋላ ለሚያንማር ካቺን ግዛት የእርዳታ ጥሪ አቀረቡ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጥር 07/2017 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ ዳራሽ ለተገኙ ምዕመናን የጠቃላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ካደረጉ በኋላ ባስተላለፉት መልእክት በምያንማር ሰሜናዊ ካቺን ግዛት በጃድ ማዕድን ማውጫ አካባቢ በቆሻሻ መደርመስ አደጋ የተጎዱ ሰዎችን ለመርዳት እና ለቁጥር የሚታክቱ ግድያዎች አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የጦር መሳሪያ አምራቾች መንፈሳዊ ለውጥ እንዲያመጡ መጸለይ እንደሚገባ የገለጹ ሲሆን፣ በዓለም ዙሪያ በአሁኑ ወቅት እየተከናወኑ የሚገኙ ጦርነቶች እና ግጭቶች እንዲቆሙ መጸለይ እንደሚገባ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሰሜናዊ ምያንማር ካቺን ግዛት በጃድ ማዕድን ማውጫ አካባቢ በተከሰተው ከባድ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ርዳታ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው ቢያንስ 12 ሰዎች በአደጋው ሕይወታቸውን አጥተዋል፣  ሌሎች ብዙ ሰዎች ያሉበት ሁኔታ እስካሁን እንደ ማይታወቅ የተገለጸ ሲሆን  በትንሹ 50 ቤቶች በአደጋው ምክንያት መቀበራቸው ወይም መፍረሳቸው ተገልጿል።

ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ የቀረበ ይግባኝ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዚህ አደጋ ለተጎዱት ሰዎች ቅርብ መሆናቸውን ገልጸው፣ ህይወታቸውን ላጡ እና ለቤተሰቦቻቸው እየጸለዩ ነው።

"እንደዚህ ዓይነት ፈተናዎችን እየታገሡ ያሉ ወንድሞች እና እህቶች የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ እና ትብብር እንዳይጎድልባቸው" ሲሉ ተማጽኗል።

ቅዱስ አባታችን እንደተለመደው በጦርነትና በግጭት ለሚሰቃዩ ሁሉ፣ ሁሉም እንዲጸልይ አሳስበዋል።

የጦር መሣሪያ አምራቾች ልብ መለወጥ

“ሰማዕት የሆኑትን ዩክሬንን፣ ምያንማርን፣ ፍልስጤምን፣ እስራኤልን እና በጦርነት ውስጥ ያሉ ብዙ አገሮችን እንዳንረሳ” ሲሉ አበክረው ገልጸዋል።

ምእመናን ሁሉ ለሰላም እንዲጸልዩ አሳስበዋል፣ ጦርነት ምንጊዜም ሽንፈት መሆኑን አስታውሰዋል።

ይህን በመመልከት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “የጦር መሣሪያ አምራቾች ልብ እንዲለወጥ እንጸልይ፣ ምክንያቱም እነርሱ በምያመርቱት እና በሚሸጡት የጦር መሣርያ የብዙ ሰዎች ሕይወት እየጠፋ ይገኛልና ሲሉ ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

15 January 2025, 12:11