ፈልግ

የቅድስት ሀገር ጳጳሳት የጋዛን የተኩስ አቁም በደስታ ተቀብለዋል የቅድስት ሀገር ጳጳሳት የጋዛን የተኩስ አቁም በደስታ ተቀብለዋል 

የቅድስት ሀገር ጳጳሳት የጋዛን የተኩስ አቁም በደስታ ተቀብለዋል።

በቅድስት ሀገር የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የተለያዩ መንፈሳዊ ማሕበራት በትላንትናው እለት በታወጀው የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት መደሰታቸውን ይገለጹ ሲሆን ነገር ግን በ "ረጅም ሂደት" ውስጥ የመጀመሪያው እርምጃ ብቻ እንደሆነ ያስጠነቅቃሉ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የቅድስት ሀገር የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጉባኤ አባላት በጋዛ የተኩስ አቁም መደረጉን የምያመለክት ዜና በመስማታቸው እጅግ በጣም መደሰታቸውን የገለጹ ሲሆን እርቀ ሰላሙ በ15 ወራት ጦርነት ምክንያት የተፈጠረውን “የማይለካ ስቃይ” በዘላቂነት እንደሚያስቆም ያላቸውን ተስፋ ገልጿል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ፣ በኢየሩሳሌም፣ በፍልስጤም፣ በእስራኤል፣ በዮርዳኖስ እና በቆጵሮስ ያሉ የካቶሊክ ጳጳሳትን፣ አገረ ስብከቶችን እና ገዳማትን ያቀፈ ጉባኤው ግን “የጦርነቱ ማብቂያ ማለት አይደለም” ሲል አጽንዖት ሰጥቶ በመግለጫው ላይ ማስፈሩ የተገለጸ ሲሆን አሁን "የግጭቱ መጨረሻ" ነው ለማለት ያስቸግራል ያሉ ሲሆን 

የሚያስፈልገው የካቶሊክ ማሕበረሰብ የግጭቱ ዋና አካል የሆኑትን "ስር የሰደዱ ችግሮችን" ለመፍታት "ረጅም ሂደት" መወሰድ እንደ ሚገባው ነው ማለታቸው ተገልጿል።

በዚህ ረገድ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ “ከጦርነቱ በኋላ ላለው ጊዜ ግልፅ እና ፍትሃዊ የፖለቲካ አመለካከት እንዲያዳብር” ጥሪ አቅርበዋል ።

መንፈሳዊ ንግደት እና ቅዱስ ዓመት

የቅድስት ሀገር የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጉባኤ አባላት “መንፈሳዊ ነጋዲያን ወደ ቅዱሳን ስፍራዎች የሚመለሱበትን ጊዜ በጉጉት እየጠበቅን ነው” ብለዋል።

የክርስቲያኑ ማሕበረሰብ መንፈሳዊ ነጋዲያን ዓመቱን ሙሉ በፍልስጤም እና በእስራኤል ወደሚገኙ ቅዱሳን ቦታዎች ይጎርፋሉ፣ ነገር ግን ጦርነት ከተቀሰቀሰበት እ.ኤ.አ. በጥቅምት 2023 ዓ.ም በኋላ ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል - በቱሪዝም ላይ ጥገኛ በሆኑ የአካባቢ ኢኮኖሚዎች ላይ አስከፊ ኢኮኖሚያዊ መዘዝ አምጥቷል።

በመጨረሻም፣ የቅድስት ሀገር የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጉባኤ አባላት የቤተክርስቲያኗን 2025 ዓ.ም ኢዮቤልዩ አመት ዋቢ አድርገዋል፣ እሱም ጭብጥ ‘የተስፋ መንፈሳዊ ነጋዲያን’ የሚለው መሆኑን አስታውሰዋል።

የኢዮቤልዩ ዓመት መጀመሪያ ላይ “ተስፋ በፍጹም አያሳፍረንም" ሲሉ የተኩስ አቁም ስምምነትን “የእግዚአብሔርን ታማኝነት የሚያስታውሰን ምልክት” በማለት ገልጸዋል።

17 January 2025, 14:23