የዓለም አቀፍ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የሚዲያ ባለሙያዎች ማህበር (SIGNIS)  የጎረጎሳዊያኑ የ 2026 ዓ.ም. ምልክት (ሎጎ) የዓለም አቀፍ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የሚዲያ ባለሙያዎች ማህበር (SIGNIS) የጎረጎሳዊያኑ የ 2026 ዓ.ም. ምልክት (ሎጎ)  

የካቶሊክ እህቶች የራሳቸውን ታሪክ በመናገር ረገድ ግንባር ቀደም ሚና እየወሰዱ መሆኑ ተነገረ

በሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ ከተማ ውስጥ ከሃምሌ 27 እስከ ነሃሴ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ “የዲጂታል መገናኛዎች ለባሕሎች መግባባት እና ለአካባቢ ደህንነት” በሚል ርዕሥ በተዘጋጀው የዓለም አቀፍ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የሚዲያ ባለሙያዎች ማህበር (SIGNIS) ዓለም አቀፍ ጉባኤ ጎን ለጎን የቫቲካን ኒውስ ከፕሮግራም ኦፕሬሽን ተባባሪ ምክትል ፕሬዝዳንት እና በኮንራድ ሂልተን ፋውንዴሽን ውስጥ የካቶሊክ እህቶች ኃላፊ ከሆኑት እህት ጄን ዋካሂዩ ጋር ቆይታ አድርጓል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ
እህት ጄን ካቶሊካዊያን እህቶች የእርስ በርስ ግንኙነት አቅምን በታለሙ ፕሮጀክቶች፣ በትምህርት እና በስልጠና ማጠናከር ያለውን አስፈላጊነት በመግለጽ፥ ገዳማዊያቱ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የተገለሉ ማህበረሰቦች ውስጥ ያላቸውን የሥራ ተፅእኖ የበለጠ ለማጉላት እንዳስቻለ አመላክተዋል።

እህት ጄን ዋካሂዩ የካቶሊክ እህቶች በተለያዩ የዲጂታል መድረኮች የራሳቸውን ታሪክ የመናገር አስፈላጊነትን አፅንዖት ሰጥተው በመግለጽ፥ በተለይም በዲጂታል የግንኙነት ዘመን ይህ እጅግ ጠቃሚ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፥ ለበርካታ ዘመናት የእህቶች ተሞክሮዎች ብዙውን ጊዜ በሌሎች ሰዎች ሲተረኩ እንደነበር አስታውሰው፥ ነገር ግን እህቶች እራሳቸው በገጠሩ ማህበረሰቦች፣ በከተማ ውስጥ በሚገኙ አካባቢዎች እና ጠረፍ ላይ በሚኖሩ ሰዎች መካከል የሚሰሩትን ሥራ በትክክለኛነት ለመግለጽ በተሻለ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የጴንጤቆስጤ ፕሮጀክት
በዚህም ረገድ ከቅድስት መንበር የተግባቦት ጽህፈት ቤት ድጋፍ ስለሚደረግለት የጴንጤቆስጤ ፕሮጀክትን ያስታወሱት እህት ጄን፥ በዚህ ፕሮጄክት የዲጂታል ታሪክ አተራረክ የእህቶችን እና እነሱ የሚያገለግሏቸውን ማህበረሰቦችን ድምፅ የሚያጎለብትበትን መንገድ እንደ አንድ ምሳሌ ጠቅሰዋል።

በቫቲካን ኒውስ ላይ በ10 ቋንቋዎች በሚታተሙ ሳምንታዊ ዘገባዎች አማካይነት፣ ፕሮጀክቱ ብዙ ጊዜ ችላ ከተባሉ አከባቢዎች፣ ማህበረሰቦች እና የጦርነት ቀጠናዎች የመጡ እህቶችን ተሞክሮዎች ድምጽ ለዓለም ለማድረስ፥ እንዲሁም የተስፋ፣ የደስታ እና የጽናት ታሪኮቻቸውን ለማካፈል ያለመ ፕሮጄክት እንደሆነ አስረድተዋል።

የቤተክርስቲያንን ተልዕኮ በተግባር የሚፈጽሙ እህቶች
እህት ጄን እነዚህን ታሪኮች የወንጌላዊነት ዓይነት ብለው የጠሯቸው ሲሆን፥ እህቶችን በጸሎት ቤት ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ከሰዎች ጋር በመሆን - የቤተክርስቲያኗን ተልዕኮ እና የማህበረሰባቸውን ህይወት በተግባር ሲኖሩ ርህራሄ፣ ፍቅር፣ እምነት እና ተስፋን እንደሚሰጡ ጠቅሰው፥ እህቶች በውጫዊ ታዛቢዎች ዘንድ እንደ ጀግና ገጸ-ባህሪያት ብቻ ተደርገው ሊታዩ እንደማይገባ አበክረው በመግለጽ፥ ከዚህም ይልቅ ከማህበረሰቦች ጋር አብረው የሚጓዙ፣ ቋንቋቸውን የሚናገሩ፣ ልማዶቻቸውን የሚረዱ እንዲሁም ተስፋንና ባህላዊ መስተጋብርን ወደነበረበት ለመመለስ የሚረዱ ተደርገው መታየት እንደሚገባ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

12 Aug 2026, 15:22