ፈልግ

የነሐሴ 03/2018 ዓ.ም የ17ኛው መደበኛ እለተ ሰንበት ሣምንት ንባባትና የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ የነሐሴ 03/2018 ዓ.ም የ17ኛው መደበኛ እለተ ሰንበት ሣምንት ንባባትና የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ 

የነሐሴ 03/2018 ዓ.ም የ17ኛው መደበኛ እለተ ሰንበት ሣምንት ንባባትና የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ

የእለቱ ንባባት

1.      1 መ. ነግሥት 3፡5. 7-12

2.     መዝሙር 118

3.     ሮም. 8፡28-30

4.    ማቴዎስ 13፡44-52

የእለቱ ቅዱስ ወንጌል

ስለተሰወረው መዝገብ፥ ዕንቁና መረብ ምሳሌ

“መንግሥተ ሰማያት አንድ ሰው በእርሻ ውስጥ አግኝቶ መልሶ የሸሸገው የተሰወረ መዝገብ ትመስላለች፤ ከደስታውም ብዛት ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጦ ያንን እርሻ ገዛው።

“ደግሞ መንግሥተ ሰማያት ክቡር ዕንቁ የሚፈልግ ነጋዴን ትመስላለች፤ ዋጋዋ እጅግ ውድ የሆነ አንዲት ዕንቁ ባገኘ ጊዜ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ገዛት።

“ደግሞም መንግሥተ ሰማያት ወደ ባሕር የተጣለችና ከሁሉም ዓይነት ዓሣ የሰበሰበች መረብን ትመስላለች፤ በሞላች ጊዜ ወደ ወደቡ አወጡአት፤ ተቀምጠውም መልካሞቹን ለቅመው በዕቃዎች ውስጥ አስቀመጡ፤ ክፉውን ግን ጣሉት። በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል፤ መላእክት መጥተው ክፉዎችን ከጻድቃን ይለዩአቸዋል፤ ወደ እቶን እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያም ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”

ስለ አዲሱና ስለ አሮጌው መዝገብ

“ይህን ሁሉ አስተዋላችሁን?” አላቸው፤ “አዎን” አሉት። 52እርሱም “ስለዚህ የመንግሥተ ሰማያት ደቀመዝሙር የሆነ ጸሐፊ ሁሉ ከመዝገቡ አዲሱንና አሮጌውን የሚያወጣ ባለቤትን ይመስላል፤” አላቸው።

የእለቱ ቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳቹ!

በዛሬው እለተ ሰንበት የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል (ማቴ. 13፡44-52 ይመልከቱ) ወንጌላዊ ማቴዎስ ስለመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ያሰፈረውን ምዕራፍ የመጨረሻ ክፍል ያቀፈ ነው። ምንባቡ በጣም በአጭሩ የተገለጹ ሦስት ምሳሌዎችን ያጠቃልላል-የተደበቀ ውድ ሀብት ፣ ውድ ዕንቁ እና ወደ ባሕር የተጣለ መረብ ተካተውበታል።

መንግሥተ ሰማያት በሁለት የተለያዩ “ውድ” ዕቃዎች ማለትም በዕርሻ ውስጥ የተደበቀውን ውድ ሀብት እና ከፍተኛ ዋጋ ካለው ዕንቁ ጋር የሚነፃፀርባቸውን የመጀመሪያዎቹን ሁለቱን ምሳሌዎች እመለከታለሁ። ዕንቁውን ወይም ሀብቱን ያገኘው ሰው የሰጠው ምላሽ ተመሳሳይ ነው - ይህ ሰው እና ነጋዴው አሁን በጣም የሚወዱትን ውድ የሆነ ነገር ለመግዛት ሁሉንም ነገር ይሸጣሉ። በነዚህ ሁለት ምሳሌዎች ፣ ኢየሱስ መንግሥተ ሰማያት መገንባት ሂደት ውስጥ እኛን ለማሳተፍ ሃሳብ አቅርቧል ፣ ክርስቲያናዊ ሕይወትን ለመንግሥተ ሰማያት ሕይወት አስፈላጊ ባህርይ መሆኑን በመግለጽ ለመንግሥቱ  ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ ያስገዙ እና ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች፣ መንግሥተ ሰማይ ለመግባት የተቻላቸውን ሁሉ የሚያደርጉ ቁርጠኛ የሆኑ ብርቱ የሆኑ ሰዎች እንደ ሆኑ ይገልጻል። በእርግጥም በእነዚህ ሁለት ምሳሌዎች ውስጥ ያለው ሰውም ሆነ ነጋዴ ያላቸውን ሁሉ ይሸጣሉ፣ ስለሆነም ቁሳዊ ደህንነታቸውን ይክዳሉ። ከዚህ በመነሳት መረዳት የሚቻለው የመንግሥተ ሰማይ መግባት የሚቻለው በእግዚአብሔር ፀጋ ብቻ ሳይሆን ፣ የሰውን ልጅም ንቁ ፈቃድን እና ተሳትፎ እንደ ሚጠይቅ እንመለከታለን። ሁሉም ነገር በፀጋ ነው የሚከናወነው ፣ ሁሉም ነገር! ጸጋን ለመቀበል ፈቃደኝነትን መግለጽ ይገባናል እንጂ፣ ጸጋን መቃወም አያስፈልግም።



ንብረታቸውን ሽጠው የበለጠ ውድ ሀብቶችን ለመግዛት የሚፈልገው ሰው እና ነጋዴው ወሳኝ ምልክቶች ናቸው፡፡ ነገር ግን እነሱ “እንድ አቅጣጫ መንገድ የሚያመለክቱ ምልክቶች ናቸው እንጂ የደርሶ መልስ መንገድ ምልክቶች አይደሉም። በተጨማሪም  ሁለቱም በደስታ የፈለጉትን ሀብት ስላገኙ በደስታ የተሰሩ ምልክቶች ናቸው። እኛ ጤናማ በሆነ መልኩ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመፈለግ የምንቅበዘበዝ ሰዎች እንድንሆን  እነዚህ ሁለት የወንጌል ምሳሌዎችን ዝንባሌ ከግምት ውስጥ እንድናስገባ ይጠይቀናል።  መንግሥቱን እንዳንፈልግ እና እንዳንገነባ የሚያግደንን አለም የሚሰጠንን ዋስትና ከባድ ሸክም የመተው ጉዳይ ነው፣ ለንብረት መጎምጀት ፣ ለትርፍ እና ለስልጣን ጥማት እና ስለራሳችን ብቻ ማሰብ የመሳሰሉትን ነገሮች ማስወገድ ይኖርብናል።

በዘመናችን ሁላችንም እንደምናውቀው አንዳንድ የሰዎች ሕይወት በሐዘን እና በድብርት ውስጥ ሊገባ ይችላል ምክንያቱም ምናልባት እውነተኛ ሀብትን ለመፈለግ ስለማይሄዱ ይሆናል፣ ማራኪ እና ጊዜያዊ በሆኑ ነገሮች ረክተው ይኖራሉ ፡፡ ብርሃናቸው በሚያንጸባርቅ መብራቶች ተስበው እውነት መስሎዋቸው በሚገቡበት ወቅት ብርሃን አልባ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፣ ጨለማ ውስጥ እንደ ሆኑ ይረዳሉ። ይልቁንም የእግዚአብሔ መንግሥት ብርሃን እንደ ርችት አይደለም ፣ እሱ ቀላል ነው ርችቶች ለአጭር ጊዜ ብቻ የሚቆዩ ናቸው፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር መንግሥት ብርሃን በሕይወታችን ሁሉ ላይ አብሮ ይኖራል።

መንግሥተ ሰማይ ዓለም ከምታቀርባቸው አስደናቂ ነገሮች በተቃራኒ ጎራ የሚገኝ ነው፣ ከመንግስተ ሰማይ ሕይወት በተቃራኒ የሚገኝ ሕይወት ነው - ህይወትን በየቀኑ የሚያድስ እና ወደ ሰፊው አድማስ እንዲዘዋወር የሚመራው ውድ ሀብት ነው። በእርግጥ  ይህንን ውድ ሀብት ያገኘ ሰው የፈጠራ ችሎታ እና አስተዋይ ልብ አላቸው፣ ይህም ደግሞ እግዚአብሔርን እንድንወድ ፣ ሌሎችን እንድንወድ እና እራሳችንን በእውነተኛ መንገድ እንድንወድ የሚያደርጉን አዲስ ጎዳናዎችን በመፈለግ  ወደ እርሱ መንግሥት እንድናመራ ያደርገናል ማለት ነው። በዚህ በመንግሥቱ ጎዳና የሚመላለሱ ሰዎች ምልክት የፈጠራ ችሎታ ነው፣ ሁልጊዜ የበለጠ ለማድረግ መሞከርን ያጠቃልላል። የፈጠራ ችሎታ ሕይወትን የሚሰጥ ነው። ሁልጊዜ ሕይወት የሚሰጠውን ብዙ ሌሎች መንገዶችን ይፈልጋል።

የተደበቀ ውድ ሀብትና ዕንቁ የሆነው ኢየሱስ አለም በሚሰጠን ደስታ መነሳሳት ብቻ ሳይሆን የህይወትን ትርጉም በማግኘት በደስታ እና በቅድሳን ራሳችንን ለእግዚአብሔር መንግሥት እንድንሰጥ ይረዳን ዘንድ ልንማጸነው የገባል።

እግዚአብሔር በኢየሱስ በኩል የሰጠን ፍቅር በቃል እና በተግባር መግለጽ እንችል ዘንድ እንዲገለጽልን ሁሌም የመንግሥተ ሰማይን ውድ ሀብት ለመፈለግ እንድንችል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በአማላጅነቷ ትርዳን።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ (ላዛሪስት)- ቫቲካን

 

08 Aug 2026, 16:07