በ21ኛው የምስራቅ አፍሪካ የጳጳሳት ጉባኤ ላይ የተገኘው የኢትዮጵያ ጳጳሳት ልኡካን ቡድን  በ21ኛው የምስራቅ አፍሪካ የጳጳሳት ጉባኤ ላይ የተገኘው የኢትዮጵያ ጳጳሳት ልኡካን ቡድን  

21ኛው የምስራቅ አፍሪካ የጳጳሳት ጉባኤ የመክፈቻ መስዋዕተ ቅዳሴ ተካሄደ

በየአራት አመት የሚካሄደው የምስራቅ አፍሪካ የጳጳሳት ጉባኤበኬንያ አዘጋጅነት ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. በይፋ ተከፍቷል። ጉባኤው የዘጠኙን አባል ሀገራት ብፁዓን ጳጳሳት ያቀፈ ሲሆን በመክፈቻ ጉባኤውም ከመቶ በላይ ጳጳሳት ተገኝተዋል።

አዘጋጅ፥ ቤዛዊት አሰፋ

የመክፈቻ መስዋዕተ ቅዳሴው በምስራቅ አፍሪካ ካቶሊክ ዩኒቨርስቲየተካሄደ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ በኬንያ ከሚገኙ የተለያዩ ሀገረስብከቶች እና ቁምስናዎች የተሰባሰቡ ምዕመናን እና እጅግ በርካታወጣቶች ተገኝተዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ሚካኤል የቅድስት መንበር ሁለንተናዊ የሰውልጅ እድገት ክፍል ኃላፊ መስዋዕተ ቅዳሴውን አሳርገዋል። የኬንያ ጳጳሳት ጉባኤን በመወከል ብፁዕ አቡነ ሙሄሪያ ከአባል ሀገራትየተወከሉ ጳጳሳትን፣ የቅድስት መንበር ተወካዮችን፣ ከመላው ዓለም ለጉባኤው የመጡ እንግዶችን አስተዋውቀዋል። 

“ሲኖዶሳዊ ጉዞ ከወጣቶች ጋር፤ የአንድነት፣ የተስፋ፣ የፍትህ እና የመልካምአስተዳደር ድልድልይን መገንባት” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ጉባኤ አባል ሀገራቱ በዋነኝነት በሐዋርያዊ ጉዳዮችን በማስቀደም በቀጠናውያሉትን ማህበራዊ ጉዳዬች በመወያይት የጋራ የቤተክርስቲያን አቅጣጫ ያቀርባሉ።

21ኛው ጉባኤያቸው በወጣቶች ህይወት ላይ በማተኮር ቤተክርስቲያንሲኖዶሳዊ በሆነ መንገድ ከወጣቶች ጋር እንዴት መጓዝ እንደምትችል የሚወያዩ ይሆናል። የወጣቶች ሥራ ማጣት፣ ከማህበረሰብ የመገለል፣ስደት፣ የአቻ ግፊት እና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ከብዙዎቹ በጥቂቱ የሚነሱ ጉዳዮች ሲሆኑ ጉባኤው ወጣቶችን በማዳመጥ አዲስ ተስፋእና የመፍትሄ ሀሳቦችን ለማቅረብ ከሁሉም አባል ሀገራት ከተወከሉ ወጣቶች ጋር በቀጣይ ቀናት ቆይታ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

21 Jul 2026, 11:33