አቡነ ፒተር ኪማኒ፥ በኬንያ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ (KCCB) የወጣቶች ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር አቡነ ፒተር ኪማኒ፥ በኬንያ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ (KCCB) የወጣቶች ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር 

ቤተ ክርስቲያን ከአፍሪካ ወጣቶች ጋር ለመገናኘት ዝግጁ መሆኗን ተገለጸ

በኬንያ የኤምቡ ሀገረ ስብከት ጳጳስ እና በኬንያ ጳጳሳት ጉባኤ (KCCB) የወጣቶች ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር አቡነ ፒተር ኪማኒ፥ “በምሥራቅ አፍሪካ የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ አገራት (AMECEA) ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ለጥያቄዎቻቸው መላሽ፣ ማካተትን፣ ተሳትፎን እና በቤተ ክርስቲያኗ የአመራር መዋቅር ውስጥም ጭምር ጠንካራ ተባባሪዎች ለመሆሆን ይፈልጋሉ” ሲሉ ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

አቡነ ፒተር ኪማኒ ይህን የተናገሩት በናይሮቢ ኬንያ በመካሄድ ላይ ባለው 21ኛው የምሥራቅ አፍሪካ የብፁዓን ጳጳሳት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለቫቲካን የዜና አገልግሎት በሰጡት መግለጫ ሲሆን፥ በማከልም ጉባኤው በትክክለኛው ጊዜ ላይ መካሄዱን ተናግረዋል።

ሲኖዶሳዊ ውይይቶች

አቡነ ፒተር ኪማኒ በመግለጫቸው፥ የአፍሪካ ብጹዓን ጳጳሳት ጠቅላላ ጉባኤውን ከሚሳተፉ የወጣቶች ልዑካን ጋር በሲኖዶሳዊ መንገድ በመወያየት አጥጋቢ የሆነ ሐዋርያዊ ውሳኔዎችን እንደሚያስተላልፉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

የወደፊት ሕይወቸውን የሚመለከቱ ጉዳዮችን ጨምሮ “የአፍሪካ ወጣቶች በእምነት በኩል እንደገና እየተነቃቁ ይገኛሉ” ያሉት አቡነ ፒተር ኪማኒ፥ “በምሥራቅ አፍሪካ የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ አገራት (AMECEA) ውስጥ የምትገኝ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ከወጣቶች ጋር ለመወያየት ያገኘችውን ይህን ሐዋርያዊ ዕድል በጠቅላላ ጉባኤው ወቅት ብቻ ሳይሆ በኋላም መጠቀም ይገባል ብለዋል።

የአፍሪካ ብጹዓን ጳጳሳት ጠቅላላ ጉባኤውን የተሳተፉት የወጣቶች ተወካዮች
የአፍሪካ ብጹዓን ጳጳሳት ጠቅላላ ጉባኤውን የተሳተፉት የወጣቶች ተወካዮች

በብርሃን የተሞላ ትውልድ

በኬንያ ጳጳሳት ጉባኤ (KCCB) የወጣቶች ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር አቡነ ፒተር ኪማኒ ለዜና አገልግሎቱ እንደተናገሩት፥ በምሥራቅ አፍሪካ አገራት ውስጥ የምትገኝ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ወጣቶች የዛሬ እና የወደፊት ስለሆኑ ከወጣቶች ጋር ለመነጋገር መወስኗን ገልጸው፥ ኬንያ ውስጥ የተከሰተውን የወጣቶች ንቅናቄ በመጥቀስ፥ “ወጣቶች በዙሪያቸው ስለሚሆነው ነገር ቸልተኞች እንዳልሆኑ እናያለን” ሲሉ ተናግረዋል።

በኬንያ ወጣቶች የሚመራው “ጄን ዜድ” የተሰኘ ንቅናቄ ኬንያውያንን በሙሉ በማስገረም የፖለቲካ ተቋምን ማናወጡ የሚታወስ ሲሆን እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከሰኔ 2024 ዓ. ም. ጀምሮ የአገሪቱ አመራር በመላ አገሪቱ የተከሰቱ ሰላማዊ ሰልፎችን እየተከታተለ እንደ ነበር፣ እንደ X፣ ቲክቶክ እና ኢስታግራም የመሳሰሉ መድረኮችን በመጠቀም የተቀናበረ እና የተደራጀ እንቅስቃሴ አድርጎ እንደ ነበር ይታወሳል።

“ወጣቶቹ እውቀት ያላቸው እና በዙሪያቸው ስለሚሆነው ነገር ጥልቅ ግንዛቤ አላቸው” ያሉት አቡነ ፒተር ኪማኒ፥ “በተመሳሳይም ፍርሃታቸው፣ ጭንቀታቸው፣ ጥርጣሬያቸው እና ስለወደፊት ሕይወታቸው እርግጠኞች አለመሆናቸው በመንግሥታት እና በቤተ ክርስቲያን ተቋማት ላይ ያላቸውን እምነት እየሸረሸረው መሆኑን እናያለን፣ ተግዳሮቶችም ብዙ ናቸው” ብለው፥ በቤተሰብ ውስጥም ቢሆን ወጣቶች ቦታቸውን ለማግኘት እየታገሉ እንደሚገኙ አስረድተዋል። በማከልም በጠቅላላ ጉባኤው እና ወደ ጉባኤው በሚያመሩ ዝግጅቶች ወቅት ወጣቶች ራሳቸውን ገልጸዋል፣ እንደ ጳጳሳትም አዳምጠናቸዋል” ሲሉ አቡነ ኪማኒ ተናግረዋል።

የአራት ዓመት ሐዋርያዊ ዕቅድ

የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ብፁዓን ጳጳሳት በጉባኤው ወቅት ከወጣቶች የቀረቡ ሃሳቦችን እና ጥያቄዎችን ካዳመጡ በኋላ ቅድሚያ ሊሰጥባቸው በሚገቡ የአራት ዓመት ሐዋርያዊ መርሃ ግብሮች ላይ እያሰቡ መሆኑን ተናግረዋል። እቅዱ በቤተ ክርስቲያኗ ሕይወት እና ተልዕኮ ውስጥ እውነተኛ የወጣቶች ተሳትፎን የሚዳስሱ የድርጊት መርሃ ግብሮችን የያዘ ሲሆን እነርሱም፥ በምሥራቅ አፍሪካ የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ አባላ አገራት (AMECEA) ውስጥ ያሉ አንዳንድ መዋቅሮችን መገምገም፣ የክልል አገራት ወጣቶች ውክልና እና ተሳትፎ ተቋማዊ ማድረግ እና በአባል አገራት ውስጥ የሚገኙ ካኅናትን ማጠናከር የሚሉት ናቸው።

ከፍተኛ ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ሌሎች ዘርፎች፥ በወጣቶች መካከል ከአእምሮ ጤና ግንዛቤ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ሲሆኑ፥ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ (AMECEA) የወጣቶችን ስልጠና ቅድሚያ ለመስጠት እና ወጣቶችን በኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች ውስጥ ለመምራት የታሰቡ የምክር ፕሮግራሞችን ለማዘጋጀት ቃል ገብቷል።

ጉባኤውን የተካፈሉት የምሥራቅ አፍሪካ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ አገራት ወጣቶች
ጉባኤውን የተካፈሉት የምሥራቅ አፍሪካ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ አገራት ወጣቶች

ወጣቶች በዲጂታሉ መድረኮች

“ወጣቶች የቤተ ክርስቲያን አካል ናቸው፤ ብዙዎች በሚገኙባቸው በዲጂታሉ መድረኮች ላይም እናገኛቸዋለን” ሲሉ አቡነ ኪማኒ ተናግረዋል።

ከሌሎች ጉዳዮች በተጨማሪ፣ በምሥራቅ አፍሪካ የብፁዓን ጳጳሳት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተገኙት የወጣቶች ተወካዮች፥ የመስመር ላይ ትናንሽ ክርስቲያን ማኅበረሰቦችን ለማቋቋም፣ እንደ ዲጂታል ሚስዮናውያን ስልጠና ለመስጠት እና በዲጂታል ዓለም ውስጥ የወጣቶች ሥራ አጥነት ፈተናን የሚመልሱ የማቋቋሚያ ኮርሶችን ለማፅደቅ ጠይቀዋል።

“ወጣቶችን ወደ እኛ ስናቀርብ ከእነሱ ጋር መተባበር፣ አብሮ መሥራት፣ እርስ በርስ መደማመጥ እና ቤተ ክርስቲያኒቱን የተሻለች ለማድረግ አሳቢ ማኅበረሰቦችን መፍጠር እንዲሁም ወጣቶች የሚያስፈልጋቸውን ተስፋ እና መመሪያ ለመስጠት ሕዝቡን የሚያገለግሉ እና በካቶሊክ ማኅበራዊ አስተምህሮ መርሆዎች ላይ ያተኮሩ ተዓማኒ ተቋማትን እና የአመራር ዘይቤዎችን እንዲወርሱ ማድረግ አለብን” ሲሉ አቡነ ኪማኒ ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።

 

25 Jul 2026, 13:32