21ኛውን የምስራቅ አፍሪካ የጳጳሳት ጉባኤ ለመሳተፍ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት እና ተወካዮች ናይሮቢ ኬንያ ገቡ 21ኛውን የምስራቅ አፍሪካ የጳጳሳት ጉባኤ ለመሳተፍ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት እና ተወካዮች ናይሮቢ ኬንያ ገቡ  

21ኛው የምስራቅ አፍሪካ የጳጳሳት ጉባኤ በኬኒያ ናይሮቢ ተጀመረ

ሐምሌ 11/2018 ዓ.ም. 21ኛውን የምስራቅ አፍሪካ የጳጳሳት ጉባኤ ለመሳተፍ በብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ የተመራ ልዑካን ቡድን ናይሮቢ ኬንያ ገብቷል። ልዑካን ቡድኑ በጆሞ ኬንያታ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በምስራቅ አፍሪካ የጳጳሳት ጉባኤ ጽ/ቤት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና በወጣቶች ደማቅ ባህላዊ አቀበባበል ተደርጎላቸዋል።

የዚህ ዜና አዘጋጅ ቤዛዊት አስፋ

ከሐምሌ 11 - 19 ቀን 2018 ዓ.ም በኬንያ የጳጳሳት ጉባኤ መሪነት የተዘጋጀው ጉባኤ ቆይታውን ናይሮቢ በሚገኘው በምስራቅ አፍሪካ ካቶሊክ ዪኒቨርስቲ የሚያደርግ ሲሆን መሪ ቃሉን “ሲኖዶሳዊ ጉዞ ከወጣቶች ጋር እና መልካም አስተዳደር” በማድረግ ከአባል ሀገራት ከተወከሉ ብፁዓን ጳጳሳት፣ ወጣቶች፣ ገዳማውያን፣ ምዕመናን እና ግብዣ ከተደረገላቸው ተሳታፊዎች ጋር ያደርጋል።

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንን በመወከል ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን፣ ብፁዕ አቡነ ሙሴ የቀድሞ የእምድብር ሀገረስብከት ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የጅማ ቦንጋ ሀገረስብከት ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የእምድብር ሀገረስብከት ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ደጀኔ የሶዶ ሀገረስብከት ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ሚልኪያስ የነቀምቴ ሀገረስብከት ጳጳስ፣ ክቡር አባ ከተማ አስፋው የጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጸኃፊ፣ ክቡር አባ አብርሃም ገብረማርያም የሐዋሪያዊ ሥራዎች አስተባባሪ፣ የምእመናን፣ የወጣት ተወካዮች እና የሚዲያ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

 

Photogallery

21ኛውን የምስራቅ አፍሪካ የጳጳሳት ጉባኤ ለመሳተፍ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት እና ተወካዮች ናይሮቢ ኬንያ ገቡ
20 Jul 2026, 16:20