ፈልግ

የሐምሌ 05/2018 ዓ.ም የ13ኛ ሣምንት እለተ ሰንበት ንባባትና የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ የሐምሌ 05/2018 ዓ.ም የ13ኛ ሣምንት እለተ ሰንበት ንባባትና የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ 

የሐምሌ 05/2018 ዓ.ም የ13ኛ ሣምንት እለተ ሰንበት ንባባትና የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ

የእለቱ ንባባት

1.   2 መ. ነግሥት 4፡8-11፣ 14-16

2.     መዝ. 88

3.     ሮም 6፡3-4፣8-11

4.    ማቴዎስ 10፡37-42

የእለቱ ቅዱስ ወንጌል

ከእኔ ይልቅ እናቱን ወይም አባቱን የሚወድድ ለእኔ ሊሆን አይገባም፤ ከእኔ ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድድ ለእኔ ሊሆን አይገባም። መስቀሉን ተሸክሞ የማይከተለኝ የእኔ ሊሆን አይገባውም። ሕይወቱን ሊያድን የሚፈልግ ያጠፋታል፤ ሕይወቱን ስለ እኔ አሳልፎ የሚሰጥ ግን ያገኛታል።

“እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል፤ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቅን ዋጋ ያገኛል። ስለዚህ እውነት እላችኋለሁ፣ ማንም ሰው ከእነዚህ ከታናናሾች ለአንዱ ደቀ መዝሙሬ በመሆኑ አንድ ጽዋ ቀዝቃዛ ውሃ ቢሰጠው ዋጋውን አያጣም።”

የእለቱ ቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዚህ እሁድ የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል (ማቴ 10፡37-42) ለጌታ ያለንን ታማኝነት ሙሉ በሙሉ እና ያለምንም ማመንታት እድንገልጽ ግብዣ ያቀርብልናል። ቅዱስ ወንጌልን መስበክ መስዋዕትነት እና ጥረት ቢጠይቅም ደቀመዛሙርቱ ይህንን ነገር በቁም ነገር እንዲመለከቱ ኢየሱስ ይጠይቃል። በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ ሁለት ዋና ዋና ሐሳቦችን እንመለከታለን።

ለተከታዮቹ የሚያቀርበው እና በመጀመሪያ ደረጃ የሚጠይቀው ጥያቄ ከቤተሰብ ፍቅር በላይ ለእርሱ ፍቅር ማሳየት እንደ ሚገባን ነው። እንዲህም አለ “አባቱን ወይም እናቱን […] ወንድሙን ወይም እህቱን ከእኔ አብልጦ የሚወድ ለእኔ የተገባ አይደለም” (ማቴ 10፡ 37) በማለት ይናገራል። ኢየሱስ ለወላጆቻችን እና ለልጆቻችን ያለንን ፍቅር አቃለን እንድንመለከት አላሳሰበንም፣ ነገር ግን  ከቤተሰብ ጋር ያለን ትስስር እጅግ በጣም የተጋነነ እና የመጀመሪያውን ቦታ ከያዘ ከእውነተኛ መንገድ ሊለየን እንደ ሚችል ስለሚያውቅ የተናገረው ንግግር ነው። ይህንን ጉዳይ በሚገባ እንመልከት፣-በመንግስት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የሚታዩት አንዳንድ ሙስናዎች በትክክል እየተከሰቱ የሚገኙት ለዘመድ አዛማድ ያለን ፍቅር ከትውልድ አገራችን ካለን ፍቅር እጅግ የላቀ በመሆኑ የተነሳ ዘመዶቻቸውን ለመሾም እንደ ሚገደዱ እንመለከታለን። ለኢየሱስ የምናደርገውም ተመሳሳይ ነገር ነው- (ለቤተሰብ አባላቶቻችን) ያለን ፍቅር ከእርሱ ከኢየሱስ  ፍቅር የሚበልጥብን ከሆነ ተግባራችን የሚሆነው ከላይ እንደ ተጠቀሰው ነው። ሁላችንም በዚህ ረገድ ብዙ ምሳሌዎችን ማምጣት እንችላለን። የቤተሰባዊ ፍቅር ውስጥ ገብተው የተደበላለቀ ስሜት የሚሰማቸው ሰዎች ከወንጌል ፍቅር በተቃራኒ ሁኔታዎች ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ናቸው። በሌላ በኩል ደግሞ ለወላጆች እና ለልጆች ያለን ፍቅር በጌታ ፍቅር ሲዋጅ እና ሲነጻ ሙሉ ለሙሉ ፍሬያማ ይሆናል፣ እናም በቤተሰቡ ውስጥም ሆነ ከዚያ ውጭ ጥሩ ፍሬዎችን ያስገኛል። በዚህ ረገድ ኢየሱስ ይህንን ሐረግ ተናግሯል። ደግሞም ኢየሱስ “እናንተ ግን አንድ ሰው አባቱን ወይም እናቱን፣ ‘ከእኔ ማግኘት የሚገባችሁን ርዳታ ሁሉ ቍርባን ይኸውም መባ አድርጌአለሁ ቢላቸው፣ እናንተም ይህ ሰው ለአባቱም ሆነ ለእናቱ ከዚህ በኋላ ምንም ነገር እንዲያደርግ አትፈቅዱለትም። ስለዚህ ለትውልድ በምታስተላልፉት ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤ ይህን የመሰለም ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ” (ማርቆስ 7፡ 8-13) በማለት የህግ መምህራንን ገስጾዋቸው ነበር! ለኢየሱስ የምናሳየው እውነተኛ ፍቅር እውነተኛ የቤተሰብ ፍቅርን ይጠይቃል፣ ነገር ግን በቅድሚያ የቤተሰብን ፍላጎት ለሟሟላት የምንፈልግ ከሆነ ይህ ሁል ጊዜ በተሳሳተ ጎዳና ይመራናል።



ከዛም በኋላ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ “መስቀሉን ተሸክሞ የማይከተለኝ ለእኔ የተገባ አይደለም” (ማቴ 10፡ 38) በማለት ይናገራል። አቋራጭ መንገዶችን ሳትፈልግ እሱ ራሱ በተከተለው መንገድ ላይ የመጓዝ ጥያቄ ነው። ያለ መስቀል እውነተኛ ፍቅር የለም ፣ ማለትም በግለሰብ ደረጃ ፍቅር የሚናገኘው ዋጋ ስንከፍል ብቻ ነው። ይህንን ብዙ እናቶች እና አባቶች የሚናገሩት ነገር ሲሆን ልጆቻቸውን ለማሳደግ እና ለማብቃት ሲሉ ብዙ መስዋዕትነት እንደ ሚከፍሉ ይታወቃል፣ ይህንንም የሚያደርጉት ልጆቻቸውን ስለሚወዱ ነው።  ከኢየሱስ ጋር የምንሸከመው መስቀል አስፈሪ መስቀል አይደለም፣ ምክንያቱም እሱ እጅግ ከባድ በሆነ ፈተና ሰዓት ጥንካሬን እና ድፍረትን ለመስጠት ሁል ጊዜም ከጎናችን ነውና። በፍርሀት እና በራስ ወዳድነት ስሜት ሕይወትዎን እንኳን ለማስደሰት አይቻልም። ኢየሱስ እንዲህ ሲል ያስጠነቅቃል: - “ሕይወቱን ሊያድን የሚፈልግ ያጠፋታል፤ ሕይወቱን ስለ እኔ አሳልፎ የሚሰጥ ግን ያገኛታል” (ማቴ 10፡39)። ይህም በቅዱስ ወንጌል ውስጥ የምናገኘው ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። ነገር ግን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይደረሰውና ብዙ ምሳሌዎችን እናያለን። በነዚህ ወቅቶችም ውስጥ እየተመለከትነው እነገኛለን። ስንት ሰዎች ናቸው ሌሎችን ለመርዳት መስቀሎቻችቸውን የተሸከሙት! በዚህ አሁን ባለንበት በጦርነት፣ በርሃብ፣ በመከራ እና በጭንቀት ወስጥ የሚገኙ ሰዎችን ለመርዳት ራሳቸውን መስዋዕት ያደረጉ ብዙ ሰዎች አሉ። ሁልጊዜ ከኢየሱስ ጋር ሊከናወን ይችላል። የህይወት ሙላት እና ደስታ የሚገኘው ራስን ለቅዱስ ወንጌል በመስጠት እና እንዲሁም ለወንድም እህቶቻችን ራሳችንን ክፍት በማድረግ ስንቀበላቸው እና የደግነት ተግባር ስንፈጽም ብቻ ነው።

ይህን ስናደርግ  የእግዚአብሔርን ልግስና እና ምስጋና ማየት እንችላለን። ኢየሱስ ስለዚህ ያስታውሰናል-“እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል [...] ስለዚህ እውነት እላችኋለሁ፣ ማንም ሰው ከእነዚህ ከታናናሾች ለአንዱ ደቀ መዝሙሬ በመሆኑ አንድ ጽዋ ቀዝቃዛ ውሃ ቢሰጠው ዋጋውን አያጣም” (ማቴ 10፡40፣ 41)። የእግዚአብሔር አብ ልግስና ምስጋና ለወንድሞች የሚደረገውን አነስተኛውን የፍቅር እና የአገልግሎት መግለጫውን እንኳን ግምት ውስጥ ያስገባል። አንድ ቀን አንድ ልጅ ወደ ቤተክርስቲያን መጥቶ ወደ አንድ ቄስ ቀርቦ የተናገረውን ልብ የሚነካ ንግግር ሰማሁ “አባቴ!  እነዚህ እኔ የቆጠብኳቸው ትንሽ ስንቲሞች ናቸው፣ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች፣ በዚህ በመከራ፣ በርሃብ፣ በጦርነት እና በጭንቀት ምክንያት ድሃ ለሆኑ ሰዎች ይስጡልኝ” በማለት እንደ ተናገረ ሰምቻለሁ። ትንሽ ነገር፣ ነገር ግን ትልቅ ነገር! ይህም በሁላችን ውስጥ በመረርሽኝ መልክ ሊፈጠር የሚገባው የልግስና ተግባር ነው፣ አንድ ሰው አገልግሎት ሲሰጠን ፣ ሁሉም ነገር በእኛ በኩል ነው ብለን ማሰብ የለብንም። የለም ብዙ አገልግሎቶች በነፃ ይሰጣሉ። የበጎ ፈቃድ ስራን ያስቡ። በነጻ የበጎ ሥራ የሚያከናውኑ ብዙ ሰዎች ሕይወታቸውን ለእግዚአብሔር ሰአጥተዋል! ይህንን ያከናወኑት ለፍቅር ሲሉ ነው።  በምስጋና አገልግሎት መስጠት የጥሩ የስርዓተ ትምህር ውጤት ነው። የጥሩ ክርስትና ምልክት ነው። ቀላል እና እውነተኛ የእግዚአብሔር መንግሥት ምልክት ነው ፣ እርሱም የማይለወጡ እና አመስጋኝ የሆነ የመንግሥተ ሰማይ ምልክት ነው።

በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ በሁለተኛ ደረጃ የተጠቀሰው ዋና ነገር ኢየሱስ “ነቢይን ነቢይ ስለ ሆነ የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል” (ማቴ 10፡41) በማለት የተናገረው ቃል ነው። ስለ ነቢይ ይናገራል፥ ነገር ግን ነቢይ ማነው? ስለ ወደፊቱ ጊዜ የሚተነብዩ እንደ ጠንቋይ የሚገምቱ ሰዎች አሉ፥ ይህ አጉል እምነት ነው፥ እናም ክርስቲያን እንደ አስማተኛ፣ የኮከብ ቆጠራ ወይም ተመሳሳይ ነገሮች ባሉ አጉል እምነቶች አያምንም። ሌሎች ደግሞ ነብይን የሚገልጹት ከክርስቶስ ልደት በፊት ስለ ክርስቶስ መምጣት አስቀድመው ሲተነብዩ የነበሩ ሰዎች እንደሆኑ አድርገው ይቆጥራሉ። ሆኖም ኢየሱስ ራሱ ዛሬ ነብያትን ስለመቀበል አስፈላጊነት ተናግሯል፣ ስለዚህ አሁንም አሉ፣ ነገር ግን እነዚህ ነብያት እነማን ናቸው?

ወንድሞቼ እና እህቶቼ እያንዳንዳችን ነብይ ነን፣ በእርግጥም በጥምቀት ሁላችንም የነብይነትን ተልእኮ ተቀብለናል (የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቁ.1268)። ነብይ በጥምቀት አማካኝነት ሌሎች በመንፈስ ቅዱስ ተግባር የአሁኑን ጊዜ እንዲያነቡ፣ የእግዚአብሔርን እቅዶች እንዲረዱ እና ከእርሱ ጋር እንዲዛመድ የሚረዳ ነው። በሌላ አነጋገር ኢየሱስን ለሌሎች የገለጸ፣ ስለእርሱ የሚመሰክር፣ ዛሬን ለመኖር እና ነገን በእቅዱ መሰረት ለመገንባት የሚረዳ እሱ ነብይ ነው። ስለዚህ እኛ ሁላችንም ነብያት፣ የኢየሱስ ምስክሮች ነን “ስለዚህ የወንጌል ኃይል በእለት ተዕለት ማህበራዊ እና በቤተሰባዊ ሕይወት ውስጥ እንዲበራ” (ሉመን ጀነሲውም (የአሕዛብ ብርሃን) አንቀጽ 35) በማለት የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ቀኖናዊ ሕገ ደንብ ሰንነድ ይናገራል። ነቢይ እግዚአብሔርን ለሌሎች የሚያመለክት  ሕያው ምልክት ነው፣ ክርስቶስ በወንድሞቹ እና እህቶቹ ጎዳና ላይ ያለው ብርሃን ነጸብራቅ ነው። እናም እራሳችንን እንጠይቅ ይሆናል፡- እኔ በጥምቀት “የተመረጥኩ ነቢይ” እናገራለሁ እና ከሁሉም በላይ የኢየሱስ ምስክር ሆኜ እኖራለሁ ወይ? በአንድ ሰው ሕይወት ውስጥ የእሱን ብርሃን ትንሽ እንዲታይ አደርጋለሁኝ ወይ? በዚህ ላይ ራሴን እፈትሻለሁ ወይ? እናተን እተይቃችሁአለሁ፥ ምስክርነታችን፣ ትንቢታችን እንዴት ነው?

በወንጌልም ጌታ ነቢያትን እንድንቀበል ይጠይቀናል፣ ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር መልእክት ተሸካሚ፣ እያንዳንዱ እንደየ ግዛቱ ወይም እንደ ጥሪው፣ እኛም በምንኖርበት አካባቢ፣ በቤተሰብ፣ በቤተክርስቲያን፣ በሃይማኖታዊ ማኅበረሰቦች መካከል እንደ እግዚአብሔር መልእክት ተሸካሚዎች መሆናችንን መቀበል አስፈላጊ ነው። በሌሎች የቤተክርስቲያኒቷ እና የህብረተሰቡ አካባቢዎች ጭምር ማለት ነው። መንፈሱ የትንቢትን ስጦታ በቅዱሳን የእግዚአብሔር ሰዎች ላይ አሰራጭቷል፣ ስለዚህ ሁሉንም ማዳመጥ ጥሩ ነው። ለምሳሌ አንድ አስፈላጊ ውሳኔ መደረግ ሲገባው፣ በመጀመሪያ መጸለይ፣ መንፈስን መጥራት፣ ነገር ግን ማዳመጥ እና መነጋገር ጥሩ ነው፣ ሁሉም ሰው፣ ትንሹም ቢሆን፣ የሚናገረው ጠቃሚ ነገር እንዳለው በመተማመን፣ ለመካፈል ትንቢታዊ ስጦታ ያስፈልጋል። በዚህ መንገድ እውነትን በመፈለግ አምላክን እንዲሁም ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን የምንሰማበት ሁኔታን እናስፋፋለን፤ በዚህ ጊዜ ሰዎች የምንወደውን ነገር ሲናገሩ ብቻ ተቀባይነት አይኖራቸውም፥ ነገር ግን ለእነሱ እንደ ስጦታ ተደርጎ እንደሚቆጠር የሚሰማቸው ሰዎች አሉ።

በዚህ መንገድ ምን ያህል ግጭቶችን ማስወገድ እና መፍታት እንደሚቻል አስቡ፥ እርስ በርስ ለመረዳዳት ከልብ በመፈለግ ሌሎችን በማዳመጥ! በመጨረሻም ራሳችንን እንጠይቅ፥ ወንድሞችንና እህቶችን እንደ ትንቢታዊ ስጦታዎች እንዴት መቀበል እንዳለብኝ አውቃለሁ ወይ? እንደምፈልጋቸው አምናለሁ ወይ? ለመማር ባለው ፍላጎት፣ በአክብሮት አዳምጣቸዋለሁ ወይ? ምክንያቱም እያንዳንዳችን ከሌሎች የምንማረው ነገር አለን።

ኢየሱስን ከህይወቷ የበለጠ የምትወደው እና እስከ መስቀሉ ሥር የተከተለች እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም ሁል ጊዜ እራሳችንን በተከፈተ ልብ በእግዚአብሔር ፊት አስቀድመን እንድናስቀምጥ፣ የእርሱ ቃል ባህሪያችን እና ምርጫዎቻችን እንዲማራ ትረዳን ዘንድ አማላጅነቷን ልንማጸን ይገባናል።

የእዚህ ዝግጅት አዘጋጅ እና አቅራቢ አባ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ (ላዛሪስት) - ቫቲካን

11 Jul 2026, 17:13