ፈልግ

ዓመታዊ የካቶሊክ ሚዲያ ጉባኤ - ከሰኔ 9 እስከ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ዓመታዊ የካቶሊክ ሚዲያ ጉባኤ - ከሰኔ 9 እስከ 12 ቀን 2018 ዓ.ም.  

የአሜሪካ ካቶሊካዊያን ጋዜጠኞች ለዓመታዊ ጉባኤ በአትላንቲክ ሲቲ መሰብሰባቸው ተነገረ

የካቶሊክ ሚዲያ ባለሙያዎች በዩናይትድ ስቴትስ እየተካሄደ በሚገኘው የካቶሊክ ሚዲያ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ እንደሆኑ የተነገረ ሲሆን፥ ተሳታፊዎቹ አሁን ባለንበት ዘመን የመገናኛ ብዙኃን ስነ ምህዳር ውስጥ የሚታዩ የወንጌል ስርጭት ተግዳሮቶች እና እድሎችን አስመልክተው ውይይት እያደረጉ እንደሆነ ተገልጿል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በመላው ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ ጋዜጠኞች፣ አዘጋጆች፣ አሳታሚዎች እና የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች ከሰኔ 9 እስከ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ በካቶሊክ ሚዲያ ማህበር በተዘጋጀው ዓመታዊ የካቶሊክ ሚዲያ ጉባኤ ላይ ለመካፈል በኒው ጀርሲ ግዛት፣ በአትላንቲክ ሲቲ ከተማ መሰብሰባቸው ተነግሯል።

በሃራህ ሪዞርት “ፈጠራን ማዕከል ያደረገ ተልዕኮ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው ይህ ጉባኤ ከጊዜ ወደ ጊዜ ውስብስብ እየሆነ በመጣው የሚዲያ ሥነ ምህዳር ውስጥ ጋዜጠኝነትን፣ ስብከተ ወንጌልን እና የዲጂታል ግንኙነቶችን የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች እና እድሎችን አስመልክቶ ለመወያየት በርካታ ካቶሊካዊያን የሚድያ ባለሙያዎችን አንድ ላይ ማሰባሰቡ ተገልጿል።

የጉባኤው መርሃ ግብር የተጀመረው በቶለንቲው ቅዱስ ኒኮላስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በተካሄደ መስዋዕተ ቅዳሴ ሲሆን፥ በማስከተልም ጉባኤተኞቹ በአትላንቲክ ሲቲ ባህር ዳርቻ ላይ በሚገኝ ማዕከል ውስጥ መሰባሰባቸው ተነግሯል።

ተሳታፊዎቹ በቆይታቸው ውስጥ የተለያዩ አውደ ጥናቶች እና በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረጉ ውይይቶች እንዲሁም በካቶሊክ ግንኙነቶች የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ያተኮሩ ቁልፍ የሆኑ ገለጻዎች ላይ እንደሚሳተፉ የተገለጸ ሲሆን፥ ከዋና ዋናዎቹ ጉዳዮች መካከል አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ወይም ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የካቶሊክ ኮሚዩኒኬሽንን አስመልክቶ ከማይክሮሶፍት ኩባኒያ የመጣው ቴይለር ብላክ እና የአሜሪካ የካቶሊክ ዩንቨርስቲ የሚያቀርቡት የመክፈቻ ንግግር አንዱ እንደሆነ ተገልጿል።

ከዚህም ባሻገር የተሳሳቱ መረጃዎች እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በተስፋፉበት በዚህ ዘመን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ለኮሚዩኒኬሽን ያላቸው ራዕይን በማስመልከት የፓናል ውይይት የሚደረግ ሲሆን፥ ከጉባኤው በተጨማሪም የተለያዩ ጥናታዊ ፊልሞች ለአብነትም በዘመናዊው ማህበረሰብ ውስጥ የሚታየውን ጽንፈኝነትን እና እርቅን የሚዳስሰው ሐውልቶችን እና ቅዱሳንን በሚመለከት የተደረጉ ውይይቶች የሚያሳየው ፊልምን ጨምሮ፥ የመጀመሪያው አሜሪካዊ ካህን እና ሰማዕት የሆኑት አባ ስታንሌይ ሕይወት እና ምስክርነትን የሚተርከው ጥናታዊ ፊልምም እንደሚታዩ ተገልጿል።

በጉባኤው ላይ ከተሳተፉት ሰዎች መካከል የቅድስት መንበር የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስተዳዳሪ የሆኑት ዶክተር ፓኦሎ ሩፊኒ፥ እንዲሁም ከሚቀጥለው ጥቅምት 22 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ የቅድስት መንበር መገናኛ ጽሕፈት ቤት ዋና አስተዳዳሪ ሆነው የሚያገለግሉት ማሪያ ሞንትሴራት አልቫራዶ ይገኙበታል ተብሏል።

19 Jun 2026, 15:02