ምድራዊ ተልዕኮውን በተመለከተ በኢየሱስ ክርስቶ ስና በመንፈስ ቅዱስ መካከል ያለው ግንኙነት ምንድ ነው ? ምድራዊ ተልዕኮውን በተመለከተ በኢየሱስ ክርስቶ ስና በመንፈስ ቅዱስ መካከል ያለው ግንኙነት ምንድ ነው ? 

ምድራዊ ተልዕኮውን በተመለከተ በኢየሱስ ክርስቶ ስና በመንፈስ ቅዱስ መካከል ያለው ግንኙነት ምንድ ነው

ሥጋ ከለበሰበት ጊዜ ጀምሮ የእግዚአብሔር ልጅ በሰብአዊነቱ መሲህ ሆኖ የተቀደሰው በመንፈስ ቅዱስ በመቀባት ነው። እርሱ መንፈስ ቅዱስን በትምህርቱ ገለጸ፣ ለአበው የተገባውን የተስፋ ቃል ፈጸመ፣ ከትንሣኤው በኋላ በሐዋርያቱ ላይ እፍ ባለ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ገና ለተወለደችው ቤተክርስቲያን ሰጠ።

በጴንጤ ቆስጤ ዕለት ምን ሆነ?

ከትንሣኤው በኋላ በሃምሳኛው ቀን በጴንጤቆሰጤ ዕለት የከበረው ኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስን በሙላት አፈሰሰ፣

ቅድስት ሥላሴ ሙሉ በሙሉ ይገለጥ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ አካል መሆኑንም ገለጸ። የክርስቶስና የመንፈስ ቅዱስ ተልእኮ የቅድስት ሥላሴን የአንድነት ምስጢር እንድትሰብክና እንድታስፋፋ የተላከችው የቤተክርስቲያን ተልእኮ ሆነ። “እውነተኛውን ብርሃን አይተናል፣ ሰማያዊውን መንፈስ ተቀብለናል፣ እውነተኛውን እምንት አግኝተናል፤ የማይነጣጠለውን መድኃኒታችንን ሥላሴን እናመልካለን” (የቢንዛንታይን ሥርዓተ አምልኮ፣ የጰንጤቆስጤ ዕለት የምሽት ጸሎት )

በቤተክርስቲያን ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ምንድ ነው ?

መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያንን ይገነባል፣ ይቀሰቅሳል፣ ይቀድሳል። የፍቅር መንፈስ እንደመሆኑ መጠን በኃጢአት

ምክንያት የጠፋውን መለኮታዊ አምሳል ለተጠመቁት መልሶ ይሰጣቸዋል፣ በክርስቶስ በኩል የቅድስት ሥላሴን ሕይወት እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል። የክርስቶስን እውነት እንዲመሰክሩ ይልካቸዋል፣ ሁሉም “የመንፈስ ፍሬ” (ገላ. 5፡22) ያፈሩ ዘንድ በየሥራቸው ያደራጃቸዋል።

ክርስቶስና መንፈሱ በምእመናን ልብ ውስጥ እንዴት ይሠራሉ ?

ክርስቶስ በቅዱሳት ምሥጢራት አማካይነት መንፈሱንና የእግዚአብሔርን ጸጋ ለቤተክርስቲያን አባላት በሙሉ ያስተላልፋል፣ እነርሱም የአዲስ ሕይወት መንፈሳዊ ፍሬ ያፈራሉ። መንፈስ ቅዱስ የጸሎት ጌታም ነው።

“በቅድስት ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አምናለሁ” ቤተክርስቲያን በእግዚአብሐር ዕቅድ ውስጥ

ቤተክርስቲያን የሚለው ቃል ትርጉሙ ምንድ ነው ?

ቤተክርስቲያን የሚለው ቃል እግዚአብሔር ከዓለም ሁሉ የጠራቸውና በአንድነት የሰበሰባቸውን ሰዎች ያመለክታል። እነርሱም በእምነትና በጥምቀት የእግዚአብሔር ልጆች፣ የክርስቶስ የአካል ክፍሎች እና የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያዎች የሆኑ ሰዎች ጉባኤ ይመሠርታሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ቤተ ክርስቲያን የሚናገራቸው ሌሎች ስሞችና ምሳሌዎች አሉ ?

ስለቤተክርስቲያን ምስጢር የተለያዩ ተደጋጋፊ ገጽታዎች የሚናገሩ ብዙ ምሳሌዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛሉ። ብሉይ ኪዳን ከሕዝበ እግዚአብሔር ጋር የተያያዙ ምሳሌዎችን ይመርጣል። አዲስ ኪዳን ደግሞ አካሉ የሆነው የዚህ ሕዝብ ራስ ከሆነው ክርስቶስ ጋር የተያያዙ ምሳሌዎችን ያቀርባል። ሌሎቹ ምሳሌዎች ከከብት እርባታ (የበግ መንጋ፣ በጎች)፣ ከግብርና (እርሻ፣ የወይራ ዛፍ፣ የወይን እርሻ) ከግንባታ (መኖሪያ ቦታ፣ ድንጋይ፣ ቤተመቅደስ) እና ከቤተሰብ (እጮኛ፣ እናት፣ ቤተሰብ) የተወሰዱ ናቸው።

የቤተ ክርስቲያን መነሻና ፍጻሜ ምንድ ነው ?

የቤተክርስቲያን መነሻና ፍጻሜ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዕቅድ ነው። የወደፊት የአሕዛብ መሰባሰብ ምልክት በሆነው በእራስኤላውያን መመረጥ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ለቤተክርስቲያን ዝግጅት ተደረገላት። በኢየሱስ ክርስቶስ ቃልና ሥራዎች ላይ የተመሠረተችውና በአዳኝ ሞቱና ትንሣኤው የተፈጸመችው ቤተክርስቲያን በጴንጤቆስጤ ዕለት በወረደው መንፈስ ቅዱስ የደኅንነት ምስጢርነትዋ ተገለጠ። እርስዋም በምድር ላይ የዳኑ ሰዎች ሁሉ ጉባኤ ሆና በሰማያዊው ክብር ፍጽምናዋን ታገኛለች።

የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ምንድ ነው ?

የቤተክርስቲያን ተልእኮ በኢየሱስ ክርስቶስ የተጀመረውን የእግዚአብሔር መንግሥት በሰዎች ሁሉ መካከል መስበክና መመሥረት ነው። ቤተክርስቲያን በምድር ላይ የዚህ አዳኝ መንግሥት ዘርና መጀመሪያ ናት።

ቤተ ክርስቲያን ምስጢር የሆነችው በምን ዐይነት መንገድ ነው ?

በገሃድ በሚታየው እውነታ ውስጥ በእምነት ዐይኖች ብቻ ሊታይ የሚችለው መለኮታዊ የሆነ መንፈሳዊ እውነት

እስካለና እስከሠራ ድረስ ቤተክርስቲያን ምስጢር ናት።

ቤተ ክርስቲያን ኩላዊት የደኅንነት ምስጢር ናት ሲባል ምን ማለት ነው ?

ቤተክርስቲያን የሰው ዘር በሙሉ ከእግዚአብሔር ጋር ለሚኖረው ዕርቅና ሱታፌ እንዲሁም ለመላው የሰው ዘር

አንድነት ምልክት መሣሪያ ናት ማለት ነው።

ቤተ ክርስቲያን ሕዝበ እግዚአብሔር ፣ የክርስቶስ አካል፣ የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ ስለመሆኗ

ቤተ ክርስቲያን ሕዝበ እግዚአብሔር የሆነችው ለምንድ ነው ?

ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ሕዝብ ናት፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሰዎችን ሊቀድሳቸውና ሊያድናቸው የወደደው በተናጠል ሳይሆን በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ አንድነት የተሰባሰቡ አንድ ሕዝብ እንዲሆኑ በማድረግ ነውና።

የሕዝበ እግዚአብሔር ባህርያት ምንድ ናቸው ?

አንድ ሰው የዚህ ሕዝብ አባል የሚሆነው በክርስቶስ በማመንና በጥምቀት አማካይነት ነው። የዚህ ሕዝብ ምንጩ

እግዚአብሔር አብ ነው፤ ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ መለዮው የእግዚአብሔር ልጆች ክብርና ነፃነት ነው፤ ሕጉ አዲሱ የፍቅር ትእዛዝ ነው፤ ተልእኮው የምድር ጨውና የዓለም ብርሃን መሆን ነው፤ መድረሻ ግቡ ከአሁኑ በምድር ላይ የተጀመረው የእግዚአብሔር መንግሥት ነው።

የእግዚአብሔር ሕዝብ ካህን፣ ነቢይና ንጉሥ በሆ ነው በክርስቶስ ሶስቱ ተግባራት የሚሳተፉት እንዴት ነው ?

የተጠመቁ ሰዎች መንፈሳዊ መሥዋዕቶችን ለማቅረብ በመንፈስ ቅዱስ የተቀደሱ እንደመሆናቸው መጠን ሕዝበ

እግዚአብሔር በክርስቶስ ካህናዊ ሥራ ይሳተፋሉ። በክርስቶስ ነቢያዊ ሥራ የሚሳተፉት በላቀ የእምነት ስሜት

እምነታቸውን ያለመታከት አጥብቀው ሲይዙና ስለ እምነታቸውም ያላቸውን ግንዛቤና ምስክርነት ሲያጠናክሩ ነው። የእግዚአብሔር ሕዝብ በንጉሣዊ ሥራው የሚሳተፉት በአገልግሎት፣ ይኸውም በዓለም ንጉሥ ሆኖ ሳለ ራሱን የሁሉ ሰው በተለይም የድሆችና የምስኪኖች አገልጋይ የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን አብነት በመከተል ነው።

ምንጭ፡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዩሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ካጸደቁት፣ በአጭሩ ከተጻፈው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ከዋናው ከላቲን ቅጂ ከተተረጎመው መጽሐፍ ከአንቀጽ 143-155 ላይ የተወሰደ ነው።

18 Jun 2026, 15:36