ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ብርሃነኢየሱስ  

ር.ሊ.ጳ ሊዮ የብፁዕ አቡነ ብርሃነኢየሱስ ለቅድስት መንበር ያቀረቡትን ከኃላፊነት የመነሳት ጥያቄ ተቀበሉ

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ እና የአዲስ አበባ ሀገረሰብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ብርሃነኢየሱስ በጡረታ ምክንያት ሐዋርያዊ ኃላፊነታቸውን አሰረከቡ።

ለቅድስት መንበር ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ በዛሬው ዕለት ጥያቄያቸውን መቀበላቸውን በቅድስት መንበር ልዪ መልዕክተኛ ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ አማካይነት ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ይፋ ተደርጓል።

የብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ ተተኪ በመሆን የአዲስ አበባ ረዳት ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ተስፋስላሴ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ ሆነው ተሹመዋል።

የዚህ ዜና ምንጭ፤ የኢትዮጲያ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ የፌስቡክ ገጽ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

12 Jun 2026, 16:06